ታዋቂው የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ እግር ኳስ ክለብአጥቂ ድዋይት ዮርክ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አጨቃጫቂውየኢምግሬሽን ፓሊሲ ሌላኛው ሰለባ መሆኑ ታወቀ ።
ከኳታር ወደ ሪፐብሊክ ኦፍ ትሪኒዳድ (Republic of Trinidad and Tobago) ለመብረር ማያሚ ላይ ግዴታትራንዚት ማድረግ ይገባው የነበረው የቀድሞው የማንችስተርዩናይትድ ኮከብ ድዋይት ዮርክ ወደ ማያሚ የሚበር አውሮፕላን ውስጥ እንዳይገባ መከልከሉ ታውቋል ።
ባሳለፍነው አርብ በፍሎሪዳ ሁለት የኢምግሬሽን ባለስልጣናት ድዋይት ዮርክ ወደ ማያሚ እንዳይገባ እንዳገዱት መረዳት ተችሏል ።
ከሁለት አመት በፊት በ2015እኤአ ድዋይት ዮርክ በኢራን ዋና ከተማ በሆነችው ቴራን ለስታዲየም ማስመረቂያ በተዘጋጀ የገቢ ማሰባሰቢያ የእግር ካስ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ በመጫወቱ ምክንያት ወደ ማያሚ በሚያቀናው አውሮፕላን እንዳይሳፈር መደረጉተዘግቧል ።
የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ ድዋይት ዮርክ ይህን በቴራን በ2015እኤአ የተካሄደውን የገቢ ማሰባሰቢያ ጨዋታካደረገ በሃላ እንኳን ኢራን አለማደሩን አሳውቋል ።
ይሁን እንጂ በአጨቃጫቂው የፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢምግሬሽን ፓሊሲ መሰረት ማያሚን ለትራንዚት መርገጥ እንደማይችልእንደተነገረው ድዋይት ዮርክ ገልጻል ።
“እየተከሰተ ያለውን ነገር ለማመን እጅግ ነበር የከበደኝ ። በቁጥር መግለጸ ከምችለው በላይ ወደ አሜሪካ ከዚህ በፊትተመላልሻለው። አገሪቷን እወዳታለው ። አሁን ግን እንደ ወንጀለኛ ነው የተቆጠርኩት።” በማለት ዮርክ በፍሎሪዳ ስለገጠመውእገዳ አስተያየቱን ሰጥቷል ።
ወደ ማያሚ በሚበረው አውሮፕላን ውስጥ ከገባ ወደ ኳታር በሃይል እንዲመለስ (deport) እንደሚደረግ ሁለት የኢምግሬሽንባለስልጣናት አስጥንቅቀው እንዳስገዱት ዮርክ በተጨማሪ ተናግሯል ።
ድዋይት ዮርክ ለሁለቱ የኢምግሬሽን ሰራተኞች በኳታር እንደማይኖር ለማስረዳት ቢሞክርም ባለስልጣናቱ ውሳኔያቸውን ለመቀየርእንዳልቻሉ ገልጻል ።
አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ
No comments:
Post a Comment