Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, February 17, 2017

አንጋፋዉ የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት በዘጠና ዓመታቸው አረፉ



ኢትዮጵያ በፋሺስት ኢጣሊያ በተወረረችበት ወቅት ለኢትዮጵያ ነፃነት አበክረዉ ይታገሉ ከነበሩት ከብሪታንያዋ ዶክተር ከሲልቪያ ፓንከርስት የሚወለዱት ሪቻርድ ፓንክረስት እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ1956 ጀምሮ የሚኖሩት ኢትዮጵያ ዉስጥ ነበር።


ሪቻርድ ፓንክረስት አረፉ


አንጋፋዉ የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት ዘጠና ዓመታቸው አረፉ። የኢትዮጵያን ታሪክ በማጥናት አቻ የማይገኝላቸዉ ፓንክረስት፣ በኢትዮጵያ እና ሥለ ኢትዮጵያ ጉዳይ ብቻ ከ20 በላይ መፅሐፍት ያሳተሙ በሳል ምሑር፤ ኢትዮጵያን አፍቃሪና ለኢትዮጵያ ታላቅ ባለዉለታ ነበሩ። ፓንክረስት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በፕሬዝደትነት የመሩ እና የዩኒቨርስቲዉን የኢትዮጵያ ጥናት ተቋም የመሠረቱ ምሑርም ነበሩ። ኢትዮጵያ በፋሺስት ኢጣሊያ በተወረረችበት ወቅት ለኢትዮጵያ ነፃነት አበክረዉ ይታገሉ ከነበሩት ከብሪታንያዋ ዶክተር ከሲልቪያ ፓንከርስት የሚወለዱት ሪቻርድ ፓንክረስት እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ1956 ጀምሮ የሚኖሩት ኢትዮጵያ ዉስጥ ነበር። ፓንክረስት የአንዲት ሴት እና የአንድ ወንድ ልጅ አባት ነበሩ። ወንድ ልጃቸዉ ዶክተር አሉላ ፓንክረስት በኢትዮጵያዊዉ ጀግና ስም ከመሰየማቸዉም በላይ የአያት አባታቸዉን ፈለግ ተክትለዉ የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚያጠኑ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚያስተምሩና የሚኖሩ ምሑር ናቸዉ። እሸቴ በቀለ የፓንክረስትን የቀድሞ ባልደረባ ዶክተር ኤልሳቤጥ ወልደጊዮርጊስን በስልክ አነጋግሯቸዉ ነበር።


እሸቴ በቀለ


ነጋሽ መሐመ

No comments:

Post a Comment

wanted officials