Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, February 8, 2017

በባህር ዳር አንድ ባለትዳር ወጣት በቤተሰቡ ፊት ተገደለ | ባለቤቱም ክፉኛ ተደብድባ ሆስፒታል ትገኛለች







በዘርይሁን ሹመቴ


አገዛዙ በባህር ዳር በሚገኙ ነዋሪዎች ተቀባይነትንሳይሆን ቂምና በቀልን በየቀኑ በሚያደርጋቸው ኢሰብአዊ ድርጊቶቹ እየዘራ እንደሚገኝ እየተገለጸ ነው ።

የባህር ዳር ነዋሪ የሆነ ስኬታማ ወጣት በቤተሰቦቹ ፊት በሚያሳዝን ሁኔታ በወያኔ ካድሬዎች ተደብድቦ መገደሉን ተሰምቷል።

ነዋሪነቱ በከተማው ቀበሌ 12 የሆነው ባለትዳር ወጣት የአገዛዙ አገልጋዮች የሆኑ ሰዎች መኖሪያ ቤቱ ድረስ በመምጣት ያለ ርህራሄ ክፉኛ ደብድበው እንደገደሉት ነዋሪዎች ለተለያዩ ምንጮች ገልጸዋል።


ባለቤቷ በወያኔ ካድሬዎች እየተጎነጨ ያለውን ግፍ ለመጋራት የቆረጠችው የትዳርና የህይወት አጋሩም ከፍተኛ ድብደባ ተፈጸሞባት ክፉኛ በመጎዳቷ በሆስፒታል እንደምትኝም መረዳት ተችሏል።

በግፍ የተገደለው ይህ ወጣት ተናኜ ነጮ በመባል የሚታወቅ ሲሆን በስራውና በህይወቱ ስኬታማ እንደነበረም ለማወቅ ተችሏል።
በባህር ዳር የአገዛዙ ካድሬዎች በግለሰቦች ላይ የሚፈጸሙት እንደዚህ አይነቱ የአደባባይ ላይ የበቀል እርምጃ ህዝቡ ለአገዛዙ ያለውን ጥላቻና የአልገዛም ባይነት ስሜትን ከመስበር ይልቅ ሊያባብሰው እንደሚችል እየተገለጸ ይገኛል።
ስርአቱን የማይደግፉ ንጹሃን ሰዎችን በቤተሰብ ፊት የመግደል እንደዚህ አይነት አዲስ የማስፈራሪያና የብቀላ እርምጃ ከሳምንታት በፊትም በዚሁ ከተማ በተመሳሳይ ቀበሌ ነዋሪ በሆነ ግለሰብ ላይም እንደተፈጸመ የአማራ ሪዲዮ ጠቅሷል።


ወጣት ተናኜ ነጮ እና አህመድ ወሎ በባህር ዳር በቀበሌ 12 ነዋሪ የነበሩ ሲሆኑ እነዚህ ሁለት ንጽሃን ጭካኔ በተሞላበት ተመሳሳይ ሁኔታ በወያኔ ካድሬዎች ተደብደበው እዛው ቤተሰቦቻቸው ፊት እንደተገደሉም ተዘግቧል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials