Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 7, 2017

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ መከሰቱን ከባለስልጣናት ቢሮ የሚወጡ መረጃዎች ጠቆሙ




Minilik Salsawi –
በኢትዮጵያ የተከሰተው ሕዝባዊ ተቃውሞ በሕወሓት መራሹ አገዛዝ ላይ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ጫና የፈጠረ ብሆንም ሕወሓት በመሳሪያ ሀይል በመግደል በማሰርና በማሳደድ ያገገመ ለመምሰል ቢሞክርም ሊያቆመው የማይችል ከባድ የሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ መከሰቱት ባለስልጣናት የባንክ መረጃዎቻቸው በመጥቀስ ከፍተኛ የሆነ ስጋት ውስጥ እንዳሉ መረጃዎች ጠቁመዋል።ከሕዝባዊው ተቃውሞ እና ከዲያስፖራው ጫና በተጨማሪ አሜሪካን እና እንግሊዝ አገር በተለያዩ ዩንቨርስቲዎች የሚማሩ ኢኮኖሚስቶች ተማሪዎች Ernst & Young PLC በሚባል ድርጅት እየተመራ የመመራመሪያ ሙከራ የሆነው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተማሩና በሙያው አንቱ የተባሉ ሰዎችን ናፍቋል።


ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገር ቤት የሚልኩትን ገንዘብ ተገን በማድረግ ኢኮኖሚውን ደግፎ ያቆየወ ወያኔ ባለፈው አመት ብቻ የነዳጅ ዋጋ መቀነስና ዲያስፖራው ለቤተሰቡ ከሚልከው ገንዘብ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላሮችን በማፈስ ለሰብዓዊ መብት ጥሰት አውሎታል። ዲያስፖራው የሚልከውን ገንዘብ በማቆም\በመቀነስ ወያኔን ክፉኛ እየቀጣው መሆኑ ምን ያህል ባለጡንቻ ዲያስፖራ እንዳለን ያሳያልና መቀጠል አለብን በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ፍርፋሪ ዶላር በባንክ አንላክ።ሌላው የሃገር ውስጥ ታዋቂ ነጋዴዎችን ጨምሮ የወያኔ ባላባቶች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያሸሹ መሆኑ ነው፥፥የተረፈ ካለ ደሞ ወደ ባንክ ከመውሰድ ይልቅ ቤጅ መያዝ እየተመረጠ መቷል፥፥አገር ውስጥ ደሞ ከማስቀመጥ ይልቅ ውጪ አገር መላክ እየተለመደ መቷል፥አገር ውስጥ ባለው የውጭ ምንዛሪ ክምችት ላይ ተጨማሪ ጉልበት ሊፈጥር የሚገባው የውጭ ምንዛሪ ግኝትም ውጭ እንዲቀር እየተደረገ ነው፡፡ የገባ ካለም በጥቁር ገበያ እንደገና እንዲወጣ እየተደረገ በመሆኑ አገሪቱ ተጠቃሚ መሆን አልቻለችም፡፡ብለዋል ባለስልጣናት።

የተለያዩ ይውጪ ኢንቨስተሮች ድርጅቶች በልማት ባንክ በኩል ለሽያጭ በጨረታ እየቀረቡ ነው።እንደ ምንጮቹ ዘገባ ወያኔ የፋይናንስ ጥያቄውን ሊጨብጠው አይደለም ሊዳስሰው አልቻለም። በኢንቨስትመንት እንሰማራለን ብለው የመጡ የውጭው አለም ሰዎች በቢሮክራሲው መንተክተክ የተነሳ አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ትብብር ማግኘት አለመቻላቸውን፣ የውጪ ምንዛሬ ኣለመኖር ሙስናውን የግልጽ ገበያ ዘረፋውን ጨምሮ መስራት እንዳልቻሉከመናገራቸውም በላይ የጀመሩት ኢንቨስትመት እንደሚቋረጥ የወያነ ባለስልጣናት እንደሚያስቆሟቸው እና ለምን ሲሉ መልስ የሚሰጣቸው አከል እንደሌለ እና ጨረታ ካሸነፉ በኋላ እንደሚሰረዝ ለማን እንደሚሰጥ እንደማያውቁ አማረው እየተናገሩ ነው፥ኣገር ጥለው የተበደሩትን ሳይከፍሉ እየሸሹ ነው።በሃገር ውስጥ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ወያኔ እመራዋለሁ በሚለው የተጭበረበረ ኢኮኖሚ ላይነሳ መኮታኮቱን ምንጮች ይናገራሉ። # ምንሊክ ሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment

wanted officials