Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, February 25, 2017

ኢህአዴግ አባላቱን ሳይቀር እየሰበሰበ በማሰር ላይ ነው


 ኢሳት ዜና :- በሰሜን ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ የኢህአዴግ አባላት ሳይቀር የጦር መሳሪያ ሽጣችሁዋል በሚል እየታሰሩ ነው። በሚሊሺያ ስም ያስታጠቃቸውን አባሎቹን ሳይቀር እያሰረ የሚገኘው አገዛዙ፣ በአካባቢው የተሰማሩት ወታደሮች የነጻነት ሃይሎችን ትደግፋላችሁ በሚል በጅምላ እየቀጡዋቸው ነው።
አፈናው መሮት ለትግል ጫካ የገባ አንድ ታጋይ እንደገለጸው፣ በአሁኑ ሰአት አገዛዙን በክርክር ማሳመን ስለማይቻል፣ ህዝቡ አንድ ነገር ሊፈጠር መሆኑን ሲያይ ወደ ጫካ መግባትን እየመረጠ መሆኑን ገልጿል።
በጭልጋ ወረዳ ጫቆ ቀበሌ ላይ ደግሞ የኮምንድ ፖስት አባላት ህወሃት/ኢህአዴግ አገሪቷን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ከክልል ምክር ቤት እስከ ቀበሌ አስተዳደር ሲሰራ የነበረውን ቀለብ ቸኮል የሚባለውን ሰው ቤት ፣ የተወሰኑ የነጻነት ታጋዮችን ከአገዛዙ ጋር ለማስታረቅ እንቅስቃሴ እያደረገ ባለበት ሰአት አፍነው በመውሰዳቸው፣ ከእርሱ ጋር በአገር ሽማግሌነት የተመረጡት ሰዎች፣ “ የአገር ሽማግሌ የማክበር ከሆነ ከእንግዲህ አንሰራም “ በማለታቸው ወታደሮችን አስገብተው የራሱን የቀለብ ቸኮልን ፣ የአቶ ምሳሌ ዳኘውን፣ የአስቀኜ ዳኘውን፣ የመሰንበት ዳኘውንና የባዩ ተገኝ ቤቶችን ዘርፈው በርካታ ንብረት ወስደዋል። ሰዎቹም ከአካባቢው ጠፍተዋል። ኢህአዴግን ለ11 አመታት በወታደርነት አገልግሎ በቦርድ የተሰናበተው መቶ አለቃ ዋናውም እንዲሁ የነጻነት ታጋዮችን ትደግፋለን ተብሎ ትናንት ታፍኖ ተወስዷል።
የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ይህ ሁሉ ሲፈጸም እንዴት እንደ ሰው አያዩንም በማለት የሚጠይቁት እነዚሁ ግለሰቦች፣ ኢትዮጵያዊ ነን ብለን ለመናገር የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል ይላሉ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials