Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, February 7, 2017

በደቡብ ጎንደር ለሰአታት የቆየ የተኩስ እሩምታ ማምሻውን ተሰማ

በደቡብ ጎንደር ለሰአታት የቆየ የተኩስ እሩምታ ማምሻውን ተሰምቷል። የትግል ጥሪ መልክት የያዙ በራሪ ወረቀቶች ተበትነው አድረዋል
- February 6, 2017 አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ
በአማራው ክልል በአገዛዙ ላይ ህዝቡ ድጋሜ ለተቋውሞና ለትግል የሚያነሳሱ በራሪ ወረቀቶች መበተናቸው ተገለጸ።
የህዝባዊ እምቢተኝነቱ እንዲቀጥልና በትጥቅ ትግል ላይ የሚገኙትን የነጻነት አርበኞችን መደገፍ ከተቻለም መቀላቀል እንደሚያስፈልግ የሚገልጽ መልክት በበራሪ ወረቀቶች ተላልፋፏል።በደቡብ ጎንደርና በደሴ ሌሊቱን ተበትነው ያደሩት እነዚህ በራሪ ወረቀቶች ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ላለው የመብት ጥሰትና የዘር ማጥፋት ዋንኛ ተባባሪ ናቸው የሚባሉትን የብአዴን አመራሮችንና ካድሬዎችን ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም የሚያስጠነቅቅ መልክትም ይዘዋል።
እነዚህ በራሪ ወረቀቶች ተበትነው ባደሩበት በእሴቴ መካነ እየሱስ ወረዳም ለሰአታት የቆየ የተኩስ እሩምታ ሲስተጋባ እንደነበረም የአካባቢው ነዋሪዋች ገልጸዋል።
በጥር 26ቀን 2009ዓም ማማሻ በዚሁ ወረዳ ለሰአታት የቆየው የተኩስ ልውውጥ ህብረተሰቡን ለትግል የሚያነሳሱት በራሪ ወረቀቶች ከመበተናቸው ቀደም ብሎ እንደተሰማ እማኞች ገልጸዋል።

የትግል ጥሪ መልክት የያዙ እነዚህ በራሪ ወረቀቶች እንደሚበተኑ መረጃ ቀድሞ የደረሳቸው የወያኔ ወታደሮች በራሪ ወረቀቶቹን ለመበተን ሲዘጋጁ ከነበሩ ሃይሎች ጋር የከፈቱት የተኩስ ልውውጥ ሳይሆን እንደማይቀር ለአከባቢው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ግምታቸውን አስፍረዋል።
በተበተኑት በራሪ ወረቀቶች ላይም የብአዴን ካድሬዎች ወያኔን ከመርዳት እንዲቆጠቡ አለዚያ ግን የስም ዝርዝራቸውን ለህብረተሰቡ እንደሚገለጽ ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።
በእሴቴ መካነ እየሱስ ሌሊቱን የተበተኑት ወረቀቶች በጎልህ በህውሃት ዘረኛ አገዛዝ መገደል ይብቃ የሚል ርእስ ይዘው እንደነበረም ታውቋል።
በተጨማሪም በደሴ ከተማ ይድረስ ለሆድ አደር የብአዴን አመራሮችና ካድሬዎች በሚል ርእስ የታተሙ በራሪ ወረቀቶች ተበትነው አድረዋል።
ከበራሪ ወረቀቶቹ ከሰፈሩት መልእክቶች ውስጥ ከህውሃት ዘረኛ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት ሁላችንም በጋር እንነሳ ፣ መሳሪያ ያለህ በመሳሪያህ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ወያኔን ለመጣል ቆርጠህ ተነሳ ፣ እኛ የነጻነት ሃይሎችም ከአንተ ፊት ቀድመን የተሰለፍን መሆኑን እንገልጻለን ፣ ይህ ሁሉ ግፍና በደል በህውሃት ሲፈጸም በብአዴን አመራር ላይ ተቀምጠው በአማራ ህዝብ የሚነግዱ ካድሬዎች አለመጸጸታቸው ነገር ግን ህዝቡ የትግል ነጻነቱን በሚቀዳጅበት ወቅት እነዚህ በብአዴን አመራር ላይ የሚገኙ ሰዎች ከህግና ከታሪክ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ የሚያስጠነቅቁ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው።
እነዚህ በራሪ ወረቀቶች ለነጻነት የሚታገሉትን አርበኞችን በሚደግፍ ክንፍ የተዘጋጀ እንደሆነም ትንታኔም የሚሰጡ እየተበራከቱ ይገኛሉ።
ወያኔ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ወታደሮች በአማራ ክልል ቢያሰማራም እነዚህ ህብረተሰቡን ለትግልና ለአልገዛም ባይነት የሚቀሰቅሱ በራሪ ወረቀቶች እንዴት እንደታተሙና ሌሊቱ ሙሉ ሲበተኑ እንዳደሩ ለማወቅ ተስኖታል።
እነዚህን የቅስቀሳ በራሪ ወረቀቶችንም ሆነ የተኩስ እሩምታውን በተመለከተ ከመንግስት የተሰጠ መግለጫ የለም።

No comments:

Post a Comment

wanted officials