Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, April 2, 2014

በሐዋሳ ከተማ 2 ትምህርት ቤቶች በቋንቋ የተነሳ ብጥብጥ ተነስቶ ሰዎች ቆሰሉ

ከዳዊት ሰለሞን
በሀዋሳ ከተማ ታቦር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚማሩ የሲዳማ ተወላጆች የሚኒ ሚዲያ ፕሮግራም በሲዳመኛ ቋንቋ ይተላለፍ፣ ታቦር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚለውን ታፔላ በሲዳመኛ ቋንቋ ይጻፍ በሚል መነሻና ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ረብሻ ተፈጥሮ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ግቢው ሲጠጉ ተማሪዎቹ ድንጋይ በመወርወር በርካታ ፖሊሶች ቆስለዋል፡፡ ፖሊሶቹ በወሰዱት ርምጃ ብዙዎች ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡
በሐዋሳ ከተማ በሚገኙ ሁለት የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች እንደቀሰቀሱት በተገመተ ረብሻ ከፍተኛ ጉዳት በተማሪዎችና በአስተማሪዎች ላይ መድረሱ ተሰምቷል፡፡
የትምህርት ቤቱ የመማሪያ ቋንቋ እንዲለወጥ በጠየቁ የኦሮሞ ተወላጆችና በሲዳማ ተወላጆች መካከል ረብሻው መቀስቀሱን ከስፍራው ያናገርኳቸው ሰዎች በስልክ ገልጸውልኛል፡፡ ረብሻውን ለማብረድ ፖሊሶች መሳሪያ መተኮስ በመጀመራቸውም የተጎዱ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ሐዋሳ ውስጥ የተኩስ ድምጽ ያለ ማቋረጥ እንደሚሰማም ምንጮች ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials