Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, April 14, 2014

አንድ ግለሰብ አማራ በመሆናቸው ብቻ በገጀራ ዘግናኝ ግድያ ተፈጸመባቸው

A man slaughtered 

አንድ ግለሰብ አማራ በመሆናቸው ብቻ በገጀራ ዘግናኝ ግድያ ተፈጸመባቸው። የተገደሉት አቶ ጌጡ ክብረት ይባላሉ የሰባት ልጆች አባት ናቸው ከተገደሉ በሁዋላ አይናቸውን አውጥተዋቸዋል። ሌላኛው አዛውንት እንደተናገሩት ደግሞ ብልታቸውን ሸንሽነዋቸዋል። ጎበዝ ኢትዮጲያችን ወዴት እየሔደች ነው? ወያኔ አሁኑኑ በቃህ ካልተባለ የሃገራችን እና የዜጎቿ ስቃይ ይቀጥላል።

ይህንን ምን እንበለው ? ኢህአዴግ ያለው ነገር የለም

አማርኛ ተናጋሪው ይህንን ምን እንበለው ? ኢህአዴግ ያለው ነገር የለም

አማርኛ ተናጋሪው በገጀራ ዘግናኝ ግድያ ተፈጸመባቸው

"መኖሬን ጠላሁት። ራሴን እንዳልገድል ወንጀል ነው። ሰው እንዳልገድል ወንጀል ነው" በሚል ግራ መጋባት አንድ አዛውንት ይናገራሉ። ተበዳዮች ከእርሻ ስራ በሁዋላ የሚይዙትን በትር ፖሊስ ሰበሰበ። ከዚያም እገበያ ቦታ ላይ ገጀራና ጦር የያዙ ጎረምሶች እየጮሁ ጥቃት መፈጸም ጀመሩ። 16 ሰዎች፣ 26 ናቸው የሚሉ አሉ ጉዳት ደረሰባቸው። አንደ ኢ ሰው ተገደሉ።

ይህ ዜና የተወሰደው ተበዳዬች ራሳቸው ባንደበታቸው ሲናገሩ ከሚታዩበት ቪዲዮ ነው። የተገደሉት አቶ ጌጡ ክብረት ይባላሉ። የሰባት ልጆች አባት ናቸው። የተገደሉት በገጀራ ነው። ከተገደሉ በሁዋላ አይናቸውን አውጥተዋቸዋል። አንደኛው ተናጋሪ አዛውንት እንደተናገሩት ደግሞ "ብልታቸውን ሸንሽነዋቸዋል"

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ለህክምና ሲሄዱ " ሂድና አገርህ ታከም። ይህ የእኛ ሃኪም ቤት ነው" እንደተባሉ ምስክሮቹ ይናገራሉ። ይህ ሁሉ የሚሆነው በምዕራብ ሸዋ ዞን ደኖ ወረዳ በሶስት ቀበሌ ገበሬ ማህበራት በሚኖሩ የአማርኛ ተናጋሪዎች ላይ ነው።

ሰዎቹ እንደገለጹት ከጎንደር ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ነው ወደ ስፍራው የገቡት። በህጋዊ ማመልከቻና በህጋዊ የአስተዳደር አካላት ውሳኔ ቀደም ሲል የዝንጀሮ መንጋ የሚኖርበትን ስፋራ እንዳለሙ ይናገራሉ። በዚህም ላይ ህጋዊ ግብር የሚከፍሉ ናቸው። አንድ እንድሜያቸው የገፋ ተናጋሪ በቪዲዮው ላይ እንደተናገሩት " አስተዳደሩ ቻፓ መቶ" አስረክቧቸዋል።

ከሃያ ዓመታት በሁዋላ አሁን " አማርኛ ተናጋሪ ናችሁ። መሬቱን ለቃችሁ ውጡ" የተባሉት ሰዎች ለፌደራል ባለስልጣናት አቤቱታ ማቅረባቸው ይበልጥ ጉዳት አስከትሎባቸዋል። " እስኪ ምን ታመጣለህ" በሚል ያካባቢው አስተዳደር አካላት ቀልደውባቸዋል። ከሁሉም በላይ ግን ላለፉት ሃያ ዓመታት አብረዋቸው የኖሩ ሰዎች ዛሬ እንዴት ጨክነው ገጀራ አነሱ? የሚለው ጉዳይ ስጋት የሚጭር ሆኗል። በተለይም የፍትህ አካላትና ራሱ ኢህአዴግ፣ ብአዴን ሰው በገጀራ ሲገደል ዝም ማለታቸው ድርጊቱን አሳዛኝ ያደርገዋል።

በተለያዩ ክልሎች የተለያዩ ብሔረሰብ ተወላጆች አሉ። ተስማምተውና ተከባብረው ኖረዋል። አሁንም እየኖሩ ነው። ኦሮሚያ ውስጥ ከጥንት ጀምሮ ተዋልደው፣ ወልደውና ከብደው የኖሩ አማሮች ቁጥር ቀላል አይደለም። ኢህአዴግ አገር መግዛት ከጀመረ በሁዋላ ኦሮሚያ ላይ በኢንቨስትመንት ስም ሰፋፊ መሬትና የማዕድን ቦታ የያዙ አሉ። ህዝብ አነዚህ ኦሮሚያን እያለቡ ያሉትን ጠንቅቆ ያውቃቸዋል። በተለይም ንጹህ ህሊና ያላቸው ጉዳዩን ከነስሌቱ ይረዱታል። ከነዚህ "ባለጊዜዎች" ዝም ተብለው ምስኪ ጭሮ አዳሪዎች ላይ እንዲህ ያለው ተግባር መፈጸሙ ውሎ አድሮ ወዴት የሚያሰኝ ይሆናል። ነገም በስፋት በተለያዩ ስፋራዎች ድርጊቱ ስላለመቀጠሉ ዋስትና የለም። በሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች ላይ።

እነዚህ ከጎንደር እንደመጡና ላለፉት 20 ዓመታት በስፍራው ላይ በህጋዊነት የሰፈሩት ወገኖች እነሱ ካሉት ውጪ ቦታው ላይ መኖር የማይችሉበት ህጋዊ አግባብ ካለ፣ ህጋዊ ጥፋት ወይም የመረጃ ችግር ካለባቸው በህግ ከሶና አስወስኖ አስፈላጊውን ውሳኔ ማሳለፍ ይቻላል። ህግና ስርዓት ባለበት አገር በትር በመንጠቅ ምስኪኖቸን በገጀራ ማስደብደብና ማስገደል ዘግናኝ ነው። ሰዎቹ እንዳሉት ሶስት ገበሬ ማህበር የሚሆኑ ናቸው። አንድ ገበሬ ማህበር ውስጥ ባማካይ 600 አባወራ አለ። በሶስት ሲባዛ የአባወራዎቹ ቁጥር ከፍተኛ ይሆናል። አሁንም እንሱ እንደገለጹት እያንዳዳቸው ባማካይ ስድስትና ሰባት ቤተሰብ አላቸው። እናም ጉዳዩ በቀላል የሚታይ አይሆንም።

“ አማራ በሚለው ደማችንና አጥንታችን አትውቀሱን" አልናቸው በማለት ሰዎቹ እንደገለጹት፣ ጥቃቱ የሚደርስባቸው በዘር ነው። ይህ ደግሞ ኢህአዴግ በተለይም ህወሃት የተከለው አጀንዳ ነው። ህወሃት በፕሮግራም ደረጃ አማራን የማትፋት እቅድ ይዞ ሲታገል የኖረ፣ አሁን ደግሞ ብአዴን የሚባል ላንቲካ/ ሲምቦል ድርጅት አስቀምጦ ይህንኑ የበታችነት ስጋቱ የፈጠረበትን ስሜት እያስተገበረ ነው። ብአዴን ውስጥ ያሉ ወገኖች ግን እስከመቼ በዚህ ይቀጥላሉ?
- ቪዲዮውን ከዚህ በታች አድምጡት

No comments:

Post a Comment

wanted officials