Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, April 4, 2014

European Union confirms violation of Human rights in Ethiopia የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ውይይት አደረገ

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ ውይይት አደረገ
መጋቢት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-” ኢትዮጵያ መረጃ የሚያወጡትና ጋዜጠኞችን ስሚ” በሚል ርእስ የአውሮፓ ህብረት ሶሻሊስቶችና ዲሞክራቶች ከአለም የጋዜጠኞች መብት ተቆርቋሪ ከሆነው ሲፒጄ ጋር በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ በቃሊቲ እስር ቤት ከአንድ አመት በላይ ታስሮ የተለቀቀው ስዊድናዊው ጋዜጠኛ ማርቲን ሽብየና በኦጋዴን የተካሄደውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት የሚያጋልጥ መረጃ ይዞ የወጣው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን፣ የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባልና የ1997 የኢትዮጵያ ምርጫ የአውሮፓ ህበረት ታዛቢ ሃላፊ፣ የሲፒጄ ጂን ፓወል ማርቶዝ እና የሂውማን ራይትስ ወች ተወካይ የሆኑት ሌስሌ ሌፍኮው ተገኝተው በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ንግግር አድረገዋል።
ወ/ሮ አና ጎሜዝ የአውሮፓ ህብረት በኢህአዴግ መንግስት ላይ ስለሚከተለው ፖሊስ ከፍተኛ ትችት አቅርበዋል። የአውሮፓ ህብረት የአውሮፓ ተወላጆች የሆኑትን ማርቲን ሽቢየንና ዮሃን ፔርሹንን ጫና አድርገው ከቃሊቲ እንዲወጡ ሲያደርጉ፣ እስክንድር ነጋ፣ ርእዮት አለሙና ሌሎች በርካታ ዜጎች በእስር ሲማቀቁ ህብረቱ ለማስፈታት ሙከራ አለማድረጉን ተችተዋል።
ወጣት አብዱላሂ ሁሴን በድብጽ ያወጣውን ቪዲዮ ለተሳታፊዎች ያቀረበ ሲሆን፣ ሌስሊ ሌፍኮው ደግሞ ሂማን ራይትስ ወች በቅርቡ ያወጣው የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎቹን ለመሰለል ስለሚጠቀምበት ዘዴ ገለጻ አድርገዋል።
በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያውያንና ጋዜጠኞች ተገኝተዋል። ወጣት አብዱላሂ ውይይቱ በወያኔ አፈና ላለው ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የምስራች ነው ብሎአል።


See full size image

No comments:

Post a Comment

wanted officials