በሰመራ ከፍተኛ ተቃውሞ ተካሄደ
ኢሳት ዜና :-በአፋር ክልል መስተዳደር መቀመጫ ሰመራ ዛሬ በተካሄደው የተማሪዎች ተቃውሞ የልዩ ሃይል አባላት በተማሪዎች ላይ ድበደባ ፈጽመዋል። ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ተማሪዎች ተደብድበው ሆስፒታል ሲገቡ በርካታ ቁጥር ያላቸው ደግሞ ታስረዋል።
የኮሌጅና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ጧት ላይ መኪኖችን አግደው ከዋሉ በሁዋላ ልዩ ሃይል በወሰደው እርምጃ እገታውን ቆሟል።
ተማሪዎች ከሰአት በሁዋላ ወደ ክልሉ ጽህፈት ቤት በመሄድ ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ ውለዋል። ተማሪዎች ግድያው እንዲቆምና የሰብአዊ መብታቸው እንዲከበሩ የሚጠይቁ መፈክሮችን አሰምተዋል።
በተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኘውን አንድ ተማሪ በቀጥታ አግኝተን አነጋገርነዋል። የፍትህ ቢሮ ሃላፊው ተማሪዎች ተወካዮችን መርጠው እንዲልኩ ለማግባባት ቢሞክሩም ተማሪዎች ግን የሃላፊውን ምክር ለመቀበል ፈቃደኞች ሆነው አልተገኙም።
ተቃውሞው ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ እንደቀጠለ ነው
ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ በአፋር ክልል የተነሳው ተቃውሞ እየተጠናከረ መምጣቱን ነዋሪዎች ይናገራሉ። የፌደራል ፖሊስ ከ8 እስከ 12 የሚደርሱ የአፋር ተወላጆችን መግደሉን መዘገባችን ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment