Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, April 11, 2014

Kenyan police beats Ethiopiam refugees more why?

የኬኒያ ፖሊስ ምን እየሰራ ነው… ?
ሰሞኑን በናይሮቢ የሚገኙ ስደተኛ ወገኖቻችን በኬኒያ ፖሊስ ቁም ስቅላቸውን እያዩ ነው። ነገረየው አዲስ አይደለም። በኬኒያ ኮሽ ባለ ቁጥር ስደተኛውን ክሽክሽ ማድረግ ዋና ስራቸው የሚመስላቸው የኬኒያ ፖሊሶች ሁሌም የሚያደረጉት ነው። በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ላይ የኬኒያ ፖሊሶች ለምን እነደሚጨክኑ ግራ ነው የሚገባኝ።
በናይሮቢ ከተለያየ የሀገራችን ከፍሎች በተለያዩ ምክንያቶች የስደት ህይወትን የተቀላቀሉ ወገኖቻችን ይገኛሉ። እኒህ ወገኖች ወይ እንደኛ በለስ ቀንቷቸው ከማይደበደቡበት ሀገር እስኪደርሱ፤ ወይም የመጣው ይምጣ ብለው እነ አባ ዱላ እና አባ ከላሽ ከሚያስተዳድሯት ሀገራቸው እስኪመልሱ ሸሽተው የመጡት መከራ ናይሮቢ ላይም የሚቀር ባይሆንም፤ እንዲህ አይነቱ ሀጋዊ ሀገወጥ ተግባር ሲፈጸምባችው ማየቱ ግን ህመም ነው።
የኬኒያን ፖሊስ ተግባር Human Right Watchን ጨምሮ የተለያዩ የአለም ሚዲያዎች ”ውጉዝ ከማሪዮስ” ብለው ቢያወግዙትም፤ እኛ ግን ለዘለቄታ የሚሆነን መፍትሄ ያሻናል… ሲመረን ሸሽተን የምንናመልጠውን ያህል በጣም ሲመረን ደግሞ ”መቼስ ማል ጎደኒ” ብለን የምንመለስበት ሀገር ያስፈልገናል… ይሄንን ለማግኘት ምን ማድረግ አለበን…!? እስቲ ሃሳብ እናዋጣ…

No comments:

Post a Comment

wanted officials