Etiopian patriotic front /EPPF and Amhara Democratic Force Movment united front to abolish TPLF junta rulers of Ethiopia
የአምባገነኑን የወያኔ ቡድን እድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሰራለን! የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የጋራ መግለጫ
የአምባገነኑን የወያኔ ቡድን እድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሰራለን!
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የጋራ መግለጫ
የስልጣን እድሜውን ለማራዘም የተለያዩ ምክንያቶችን እየፈጠረ እና በሱ ላይ የተነሱትን የተቃውሞ ሃይላት በ አሸባሪነት ከመፈረጅ አልፎም በመግደል በማሰር እና የተለያዩ ወከባዎችን በመፍጠር ከትግሉ ጎራ ጋሳቸውን እንዲያገሉ ማድረጉና እያደረገም መሆኑ ህዝብ የሚያውቀው ሃቅ ነው::
ይህን ተከትሎም በመሳሪያ ሃይል ስልጣን ላይ የወጣውን የወያኔን ቡድን ለስልጣን በበቃበት መንገድ ካልሆነ በስተቀር በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር እንደማያደርግ የተረዱ የተቃውሞ ሃይላት በተለያዩ ጎራ ተከፍለው የትጥቅ ትግል እያደረጉ መሆኑ ይታወቃል ::
የወያኔ አምባገነን ቡድን እድሜው ሊያጥር የሚችለው ኢትዮ0ያዊያን በአንድነት ሆነው መታገል ሲችሉና ህዝቡንም አንድ ማድረግ ሲችሉ ነው የሚለውን የመላው የኢትዮጵያዊ ጥያቄን ለመመለስ በሚል ከአሁን በፊት የተለያዩ የትብብር ሂደቶችን ቢኖሩም አመርቂ ስራ ሊሰሩም ሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ የዘወትር ጥያቄ ሊመልሱ አልታደሉም::
በመሆኑም ድርጅቶች አንድ ሆነው ህዝቡን አንድ አድርገው ትግሉ ሊፋጠን የሚችለው እየተባበርን ነው ብሎ ለህዝብ ማወጅ ሳይሆን የተባበረ ሃይል የሰራውን ስራ ለህዝብ ይፋ ማድረግና በቀጣይ የሚኖረው የትግል ሂደት ድርጅቶችም ሆኑ ህዝቡ በአንድነት በመታገሉ ሂደት በጠራ መንገድ እንዲጓዝ እገዛ ያደርጋል ::
በዚህም መሰረት እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ቁም ነገሮች መቅደም አለባቸው በሚል መርህ ጥልቀት ያለቅ ውይይት በማድረግ በሚስጥር ወታደራዊ ግንባር የፈጠሩት የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና የአማራ ዲሞ ክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ በመጀመርያ እኛ ግንባር መፍጠራችንን ለህዝብ ይፋ ከማድረጋችን በፊት የጋራ ግንባሩ ህዝብ ሊያየው የሚችል በጋራ መስዋእትነት የመክፈል ሂደት መኖር አለበት የሚል የጋራ ግንባሩ ስምምነት በመኖሩና ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ከሁለቱ ድርጅቶች የተውጣጣ ሰራዊት ሰሞኑን በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች የተገለጸውን ስራ እንዲሰሩ ሆኗል ::
ግቡን በአንድነት ተዋህዶ ለመስራት የተነሳው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ባለፈው ሳምንት ማለትም መጋቢት 12/2006 ዓ/ም በጠገዴ ወረዳ ግጨው በተባለ አካባቢ ከወያኔ ሚሊሻ ታጣ ቂሃይል ጋር ባደረጉት ውጊያ ሶስት የሚልሻ አመራሮች ሲማርክ 17 ገድሎ 14 ማቁሰሉን እና የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ከመሰል ጥይቶቻቸው እንዲሁምሁለት (2) ሽጉጥ መማረኩንና የተማረኩትንም የሚልሽያ አመራሮች ስለ ድርጅቶቹ አላማና ፕሮግራም በማሳወቅ በሰላም ወደቀያቸው ተዘኝተዋል ::
ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ማዳን አድርገን የተነሳነው የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የጀመርነው ተግባራዊ እንቅስቃሴ በአንድነት መስመር ጥላ ስር መሆኑ ለህዝቡተስፋ ከመሆን አልፎ በተናጠል እየተጓዙ ላሉ ድርጅቶችም አብነት ይሆናል የሚል እምነት በማሳደር ወደ ውህደት የምንመጣበትን ሂደት እያመቻቸን መሆኑን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመግለጽ እንወዳለን ::
በመሆኑም አምባገነኑ የወያኔ ቡድን እድሜው ሊያጥር የሚችለው የኤትዮጵያዊያን በተናጠል ሳይሆ ን በአንድነት ስንታገል መሆኑ ታምኖበት መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ድርጅቶች ወደ አንድነቱ መስመር እንዲመጡ ግፊት በማድረጉ ረገድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪ እያደረግን በተለያየ ጎራ ተከፋፍለው የሚታገሉ የወያኔ ተቃዋሚሃይሎችም እኛ የጀመርነውን አብሮ መስዋእትነት የመክፈል ሂደት በመከተል ሃገራችንንና ህዝባችንን ልናድን የምንችልበትን መንገድ እናመቻች ስንል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ::

No comments:
Post a Comment