የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ስራ አስፈጻሚ በዛሬው ዕለት በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ‹‹በህገ ወጥ መንገድ የሚቀለበስ ሰላማዊ የትግል ስልት ባለመኖሩ የአዲስ አበባ ህዝብ ለቀረበለት የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ምላሹን እንዲሰጥ በአክብሮት እንጠይቃለን››ብሏል፡፡
የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ክፍል ህገ ወጥ ደብዳቤ በመጻፍ ሰልፉን ማከናወን አትችሉም ማለቱ ከህግ በላይ ነኝ የሚል መንፈስ እንዳለው እንደሚያሳይ የገለጸው ፓርቲው በአገሪቱ ህገ መንግስቱንና ሌሎች አዋጆችን የማስከበር ስራ የሚሰሩ ተቋማትም ለህግ መከበር ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያሳዩ ጠይቋል፡፡
‹‹የእሪታ ቀን›› በሚል መሪ ቃል መጋቢት 28 ቀን 2006 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንዲደረግ ቀጠሮ የተያዘለት ሰላማዊ ሰልፍ በተያዘለት ቀጠሮ መሰረት እንደሚደረግም ፓርቲው በመግለጫው አስታውቋል፡፡

አሁን የገጠመን የመሠረታዊ አገልግሎቶች ችግር የውሃ፣ የመብራት፣ የስልክ ችግር የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ህዝብ የገጠመውን ስቃይ እሪ በማለት እንዲያሰማ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) መድረኩን ያዘጋጀ ስለሆነ ጥያቄያችሁን ለመንግሥት እንድታስተላልፉ የአዲስ አበባ አንድነት ም/ቤት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ የሠላማዊ ሠልፍ ማሳወቂያ ክፍሉ ለሚቀርብለት የሠላማዊ ሠልፍ የእውቅና ጥያቄ ህገ መንገሥቱንና አዋጅን በሚቃረን መልኩ ምላሽ መስጠት የማይችል ቢሆንም በማን አለብኝነት አዋጁን በጣሰ መልኩ ምላሽ መስጠቱን አልተቀበልነውም፡፡
ህዝብን በተለይም ህገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎች እንዲያገለግል ኃላፊነት የተሰጠው አካል ህጋዊ እውቅና ካገኘ ተፎካካሪ ፓርቲ የሚቀርብለትን ደብዳቤ አልቀበልም ማለቱም ህገ ወጥ ተግባር በመሆኑ ግለሰቡ በመደበኛ ፍርድ ቤት ክስ እንዲመሰረትባቸው ወስነናል፡፡የሚሉ ት የፓርቲው መግለጫዎች ናቸው
በያያዘ ዜናም
የአዲስ አበባ የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ ስብሰባዎች ማሳወቂያ ክፍል ኦፊሰር የሆኑት አቶ ማርቆስ ብዙነህ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ላቀረበላቸው የሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ደብዳቤ ህገ ወጥ ምላሽ በመስጠታቸው ፓርቲው ደብዳቤውን የተቃወመበትን የህግ አግባብ በመጥቀስ ደብዳቤ ልኮላቸዋል ፡፡
አቶ ማርቆስ በጽ/ቤታቸው በአካል የተላከላቸውን ደብዳቤ ምስክሮች ባሉበት ‹‹አልቀበልም ብትፈልጉ ክሰሱኝ››በማለት በህጋዊ መንገድ የቀረበላቸውን ደብዳቤ አልቀበልም በማለት መልሰዋል፡፡አንድነት ፓርቲ ሰዎች ሁሉ በህግ ፊት እኩል መሆናቸውንና በመንግስት የሃላፊነት ቦታ ላይ የተቀመጡ ሰዎችም ህዝቡን ማገልገል ቅሬታውንም ማድመጥ ግዴታቸው ጭምር መሆኑን በማመን ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የቅሬታ ደብዳቤ አስገብቷል፡፡
No comments:
Post a Comment