የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እስር (ኤዶም ካሳዬም ታሰረች)
(ኢ.ኤም.ኤፍ) አርብ ሚያዝያ 17 ቀን 2006 አመሻሹ ላይ 11፡20 ገደማ ነበር ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከያሉበት ተይዘው የተወሰዱት። እነርሱም ናትናኤል ፈለቀ፣ በፍቃዱ ሀይሉ፣ አጥናፍ ብረሀነ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ ዘላለም ክብረት እና አቤል ዋበላ ናቸው፡፡ ጦማርያኑን ያሰሯቸው አካላት የማሰሪያና የመፈተሻ የፍርድ ቤት ፈቃድ የያዙ መሆናቸውን የ“ዞን 9” ብሎግ በመግለጫው አሳውቆ ጦማርያኑ በምንም አይነት ህገ ወጥ ተግባር ላይ ተሰማርተው እነዳልነበር ካረጋገጠ በኋላ የታሰሩ የዞኑ አባላትና ወዳጆች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቋል
ማምሻውን በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በቁጥጥር ስር ዋሉት 6 የዞን 9 አባላትና ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ማእከላዊ ምርመራ እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡ ታሳሪዎቹን ቤተሰብ ማየት የማይችል ሲሆን ስንቅ በማቀበል ብቻ ተመልሰዋል፡፡ በተያዙበት ሰአት ቤታቸውና ቢሯቸው የተፈተሸ ሲሆን መጽሃፍት ጋዜጦች እና ላፕቶፖቻቸውም ጭምር እንደተወሰዱ ለማወቅ ችለናል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሌላኛዋ የዞን ዘጠኝ ጦማሪት ኤዶም ካሳዬ በዛሬው እለት ቤቷ ተበርብሮ፤ እሷም ወደ እስር ቤት ተወስዳለች።

No comments:
Post a Comment