በግብፅ የጅምላ ችሎት 683 የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ሙርሲ ደጋፊዎች በሞት እንዲቀጡ ተበየነ።
በግብፅ ታሪክ ውስጥ ዛሬ በተካሄደው ትልቁ የጅምላ ችሎት 683 የቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዚደንት ሙርሲ ደጋፊዎች በሞት እንዲቀጡ ተበየነ። በላዕላይ ግብፅ የምትገኘው የሚንያ ከተማ ፍርድ ቤት ተከሳሾቹን የሞት ፍርድ የበየነባቸው ግለሰቦቹ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት ፕሬዚደንት መሀመድ ሙርሲ በጦር ኃይሉ ከሥልጣን በተወገዱበት ድርጊት አንፃር እአአ ነሀሴ 14 ቀን፣ 2013 ዓም በምንያ ከተማ ኃይል የታከለበት ተቃውሞ ሰልፍ አካሂዳችኋል ፣ የነፍስ ግድያም ፈፅማችኋላ በሚል በተመሠረተባቸው ክስ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል በሚል ነው።
በሞት እንዲቀጡ ከተበየነባቸው መካከል የሙሥሊም ወንድማማችነት ማህበር መሪ መሀመድ ባድየ ይገኙባቸዋል። ባለፈው ወርም በዚችው የምንያ ከተማ 529 የሙሥሊም ወንድማማችነት ማህበር ደጋፊ የተባሉ ግለሰቦች በተመሳሳይ ክስ የሞት ቅጣት የተበየነባቸው ሲሆን፣ በወቅቱ ከነዚሁ 491 ወደ ቅጣታቸው ወደ ዕድሜ ልክ እስራት እንደተቀየረ ተገልጾዋል። ተከሳሾቹ በምንያ ከተማ አደባባይ በወጡበት ዕለትም ካይሮ ውስጥ ፕሬዚደንት ሙርሲ ከሥልጣን የተወገዱበትን ድርጊት በመቃወም አደባባይ በወጡ ሰልፈኞች እና በፀጥታ ኃይላት መካከል በተፈጠረ ግጭት ወደ 700 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ነው።
የሞቱ ቅጣት ከያቅጣጫው ወቀሳ ተፈራርቆበታል። የመብት ተሟጋቹ «ሂውመን ራይትስ ዎች» የግብፅ የሽግግር መንግሥት ተቀናቃኞቹን ለማስፈራራት እና ለማሸበር ያደረገው ነው ሲል ወቅሶዋል። ባጠቃላይ የሞቱን ቅጣት የማይደግፈው የጀርመን መንግሥትም ብይኑን ነቅፎዋል።
source: ዶይቸ ቬለ

No comments:
Post a Comment