Oromos fight to be called neggele boren or simply borena
በጉጅና በቦረናዎች መካከል ግጭት ማገርሸቱ ተሰማ
ሚያዚያ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ግርማየ ፣ ቦቢላ ፣ መደር እና ቦኪዳዋ ቀበሌዎች ሚያዚያ 4 ቀን 2006 ዓም በተነሳ ግጭት ከ5 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ከአካካቢው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ውጥረቱ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው። በጉጂ የወረዳ ሹማምንት እርስ በርስ ግምገማ ላይ መቀመጣቸውም ተሰምቷል።
የኦሮምያ ክልል የጉጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገዳ ሮቤ ከስልጣን መነሳታቸው ችግሩን ያበርደዋል ተብሎ ቢጠበቅም እስካሁን ያመጣው ለውጥ የለም። በጉጂና በቦረና መካከል በተፈጠረው የጎሳ ግጭት ከ20 በላይ ሰዎች መሞታቸው መዘገቡ ይታወሳል። የግጭቱ ዋነኛ መንስኤ ከነገሌ ቦረና ስያሜ ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ አንዳንዶች ደግሞ ለዘመናት ተከባብረው የሚኖሩትን ጎሳዎች የሚያጋጩት ባለስልጣኖች ናቸው በማለት ወቀሳ ያሰማሉ።
በአካባቢው ስላለው ግጭት የዞኑን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደርግነው ሙከራ አልተሳካም።
No comments:
Post a Comment