Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, April 22, 2014

ወያኔዎች የፋሺስት ሙሶሎኒ ደቀ መዝሙሮች ናቸው- በዶክተር ጌታቸው ረዳ

ወያኔዎች የፋሺስት ሙሶሎኒ ደቀ መዝሙሮች ናቸው- በዶክተር ጌታቸው ረዳ

ገብረኪዳን ደስታ “እምቢ አንጻር ወረርቲ” (በወራሪዎች ላይ እምቢታ) ብሎ በጻፈው ምጽሐፍ ፈላጭ ቆራጭ በነበሩት ግፈኞቹ “የትግራይ መሳፍንት እና የጉልተኞች ዲሞክራሲ” ድንቅነት እና በጐነት ለማሳየት እና ለማስተዋወቅ በተጻፈው የውሸት ክምር ተመርኩዞ “ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም” አስተያየቱን አንዲሰጥ ተጠይቆ፤ ስለ አፄ ዮሐንስ እና ስለ ምኒሊክ፤ ስለ ‘አማራ’ ጻሀፊዎች ብዙ ዘላብዷል።አስቀድሜ አንደተናገርኩት ሙሉወርቅ ጎሰኛ እና አማራ የሚጠላ መሆኑን እኔን ለመቀበል የሚያዳግታቸው ሰዎች ስላሉ በሌላ ሰው አንደበት መረጃየን ላቅርብ። አብርሃ ደስታ ይባላል። አብዛኞዎቻችሁ ይህ ወጣት በመጥፎም በደግም ጽሑፉ የምታውቁት ነው። የጻፈ ሁሉ ደራሲ ነው? በሚል ርዕስ መጣጥፉ ስለ ሙሉወረቅ ኪዳነ መርያም እንዲህ ይላል። አዲስ አበባዎች ሰለማዊ ሰልፉ ሲቀውጡት እኔ ደግሞ ከጓደኞቼ ጋር … የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር በመቐለ ከተማ ቅርንጫፍ ስለመክፈቱ ተጋብዘን እየተነጋገርን ነበር። የአዲስ አበባ ሰልፍ በሰላም መጠናቀቁ ደስ ብሎኛል።
እኔ ግን ስለ ማህበሩ ዉሎ ትንሽ ላካፍላቹ። ምክንያቱም ካደረግነው ዉይይት አንድ ‘ደስ የሚል’ ነገር ስላገኘሁ ነው። የኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር በመቐለ ቅርንጫፍ የሚከፍትበት ዝግጅት ጥሩ ነበር። ብዙ ሙሁራን ደራሲያን ታድመው ንግግር አድርገዋል።
ግን በደራሲያኑና በሙሁራኑ ንግግር ቅር ያሰኘኝ ነገር ነበረ። ከክብር እንግዶቹ ሁሌ ‘ሊቃውንት’ ተብለው የሚቀርቡ ዶ/ር ሰለሞን ዕንቋይ፣ መምህር ገብረኪዳን ደስታና መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ነበሩ። ከኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር የተላኩ አራት ደራሲያንም ነበሩ።ንግግርአድርገዋል።
ከኢትዮዽያ ደራሲያን ማህበር የተወከሉ አማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው ግን ትግርኛም ይሰማሉ። የአብዛኞቹ ንግግር አልተመቸኝም። ሲበዛ ግብዝ ነበሩ። የሚናገሩት የልባቸው እንዳልሆነ በቀላሉ መገመት ይቻላል። ጥረታቸው ለግዜው እኛ የትግራይ ተወላጆችን ማስደሰት ነበር። በትክክል ግን ማስደሰት ሳይሆን መመፃደቅ ነበር። ትግራይ ሰማይ ሰቀሏት። ከነሱ አንድ ግን ጠንከር ያለ አስተያየት ሰጠና አስደሰተኝ። ሌሎቹ ግን ‘የእውነት ደራሲያን ናቸው?’ ብዬ ራሴ እንድጠይቅ አድርገውኛል። ግብዝ ደራሲ አልወድም። “የኛዎቹም ተናገሩ። ዶ/ር ሰለሞን ብዙ አላባላሹም። አጠር ያለ ግሩም አስተያየት ሰጡ። መምህር ሙሉወርቅ ለመጀመርያ ግዜ (እኔ እስከሰማሁት ድረስ) ‘አማርኛ ማወቅ ጥሩ ነው’ ብሎ ተናገረ። ገረመኝ፤ አናደደኝም። ግብዝ መሆኑ ነው። ‘አማርኛ ተናጋሪዎች ከመሃከላችን ስላሉና እነሱ ለማስደሰት ስለፈለገ ነው?’ ብዬ ታዘብኩት፤ ምክንያቱም አቋሙ ከዚህ በፊት አውቀዋለሁ። ትንሽ ቆይቶ ግን ወደ ተለመደው የፖለቲካ መዘባረቁ ገባ። ተረጋጋሁ። ምክንያቱም ወደ ትክክለኛ ማንነቱ ተመልሷል። እንደወትሮው ለሸዋ ታሪክ ፀሃፊዎች መውቀስ ጀመረ። » እኔ ደግሞ ግራ ሲገባኝ ‘ሁሉም ፀሓፊ ደራሲ ነው እንዴ? ለምንድነው የታሪክ ተመራማሪዎች እንደ ደራሲያን አድርገን የምንቆጥራቸው? ድርሰት እኮ ጥበብ ነው፣ መፃፍ መቻል ግን ክህሎት ነው።’ ብዬ ጠየቅኩ። (የጻፈ ሁሉ ደራሲ ነው? አብርሃ ደስታ) ከላይ በአበርሃ ደስታ አንደተገለጸው ሙሉ ወርቅ ኪዳነማርያም ማለት ይህ ነው።
ሙሉወርቅ የዚህ ትምክህተኛ ቡድን አገልጋይ ሆኖ ሳዳምጥ በጣም ነው የገረመኝ። ዮሐንስ አዳራሽ መኝታ ክፍላቸው ውስጥ በተደረገው የገብረኪዳን ደስታ መጽሐፍ ድጋፍ አንደለፈፈው ትግሬዎች በብዙ የታሪክ ሰነዶች ድሮም ይሁን አሁን እንኳ በቅርቡ በባድሜ ጦርነትም ይሁን በዓድዋ፤በማይጨው ጦረነቶች ሁሉ ትግሬዎች ባካባቢያቸው የተከሰቱ ጦርነቶች ብቻቸውን አልገጠሙዋቸውም። እንኳን እና ድሮ በርሃብ፤በተላላፊ በሽታ፤በወባ፤ እና ባስቸጋሪ ክረምት የሰው ሃይል እና የስንቅ ምንጭ በሚያስፈልግበት ወቅት ብቻቸውን ሊዋጉ ቀርቶ፤ አሁን ሁሉም በእጃቸው ባደረጉበት ጦሩም ፤ሃብቱም፤ስልጣኑም፤ አይሮፕላኑም፤ መድሃኒቱም፤ፋብሪካው እና ማጓጓዣው በቁጥጥራቸው ባደረጉበት ወቅት አንኳ ‘ሻዕቢያን’ ከባድመ፤ከዓሊተና፤ከዛላምበሳ.፤ከባዳ…. መግፋት አቅቷቸው ለሁለት ዓመት የትግራይ ድንበር ተወርሮ፤ ያካባቢው ድምበር ኗሪዎቹ ተፈናቅለው፤ መኖርያ ቤቶቻቸው እየተቃጠሉ ፤ኗሪዎች እየተገረፉ እና እየተጠለፉ፤ ጫካው እየተመነጠረ፤ ድንጋዩ እየተፈነቀለ “የሻዕቢያ” ምሽግ ማጠናከሪያ ሆኖ ሁለት አመት ሲቆይ “እርዱን” ተብሎ ነው የድሮ ሰራዊት ሳይቀር እየተለመነ ተመልሶ በመታጠቅ ‘ሻዕቢያን” ድባቅ የመታው እና እስከ ባረንቱ፤ ተሰነይ እና ሰንዓፈ ገብቶ ያራወጠው። ይህ የዓምና ታሪክ ነው፡ አንዴት ልንረሳው አንችላለን? ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ፡እነ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም “በሰሜን የተደረጉ ጦርነቶች በሙሉ በትግሬዎች የተካሄደ የትግሬዎች ጀግንነት ነው እያለ ሕዝቡን በጀብደኝነት ሲያሰክሩ ማድመጥ እህግ አስገራሚ ክሰተት ነው። አለማፈር! አታኽለቲ ሓጎስ በትግርኛ እንዲህ ይላል። “ተጋሩ ንኢትዮጵያ መስዋእቲ ዝኾ ኑንን ዘድሓንዋን እየ ገይረ ዝ ወ ስዳ። (ትግሬዎች ኢትዮጵያን ለማዳን ቤዛ የሆኑ ናቸው)።(ቃለ መጠይቅ – ውራይ መጽሄት)
አታኽልቲ ሐጎስ ማለት ‘ሃቅ ሃቁን ለህጻናት’ እና “ደቂቀ ምኒሊክ፤ አይንታሓማመ” እና የመሳሰሉ ጎሰኛ እና ዘረኛ መጽሐፍ የጻፈ የወያኔ ደራሲና ገጣሚ እንዲሁም ሰዓሊ ነው።” እሱም አብሮ አደጌ ነው። እኔ እስከማውቀው ድረስ ትግሬዎች (ወያኔን አይጨምርም) በማንኛወም ውግያ ሲሳተፉ በኢትዮጵያዊነታቸው እንጂ “ኢትዮጵያ የተባለች አገራቸው ከጠላት ለመከላከል ቤዛ የሆኑ አንጂ ‘ኢትዮጵያ የተባለች ባዕድ አገር’ ለማዳን የተሰው አይደሉም። የወያኔ ደራሲያን ችግር፤ “ትግራይ እና ኢትዮጵያ” ለያይተው የማየት በሸታቸው የጠነከረ ስለሆነ ማንኛውም ጦርነት ሲካሄድ “ኢትዮጵያ የምትባሉ ፍጡሮች ፈጣሪዎቻችሁም አዳኞቻችሁም እኛ ነን።” የሚል የትምክሕት አበዜ ሲያስተጋቡ ፣የስካራቸው ውሸት መጠን የለውም። ለዚህም ነው መላ ኢትዮጵያ እና መላው የኢትዮጵያ አካባቢሕዝብ የተካፈለበት የአክሱም ስልጣኔ የትግሬዎች ብቻ አድርገው በማጽፍ እና በመሳል በውሸት የሚስሉት፤፡ ይህንን የወያኔ ትግሬ ንብረትና ታሪክ አድርገው የሚያቀርቡት የሌሎችን አስተዋጽኦ እና ክብር የሚጋፋ አስጸያፊ ምሰል አንደናሙና ተመለክቱት። መምህር ገብረኪዳን ደስታ
“ሚኒልክ ወደ ትግራይ የመጣው “ትግሬ ከጠገበ እና አንድ ከሆነ አይገዛም፡ ወይም አይቻልም” የሚል እምነት ነበረዉ። በተጨማሪም የትግራይ ህዝብ “ብዙ ብር” አለው፤ተብሎ ስለሚታመን ገበሬውን “እየዘረፉ” ሃብት ማካበትና ሕዝቡን “ማደሕየትም” “እንደ ስልት” የተያዘ በመሆኑ አስፈላጊ ነበር። አጼ ምኒልክ ወደ ትግራይ ያደረጉት ዘመቻም እነዚህን “ሁለት ነጥቦች” ለማሳካትና ተግባራዊ ለማድረግ ነዉ” ምመህር ገብረኪዳን ደስታ (የትግራይ ሕዝብ እና የትምክሕተኞች ሴራ ከትናንት አስከ ዛሬ ገጽ 103) ምንጭ “ይድረስ ለጎጠኛው መምህር” ከሚል መጽሐፍ፤- ደራሲ ጌታቸው ረዳ። ይህ ፎቶግራፍ ወደ ግራ በኩል የሚታየው ሽማግሌው መምህር ገብረኪዳን ደስታ ነው። ወደ ቀኝ በኩል ያለው ወጣት “ዮሃንስ” (ጆን እያሉ ወያኔዎች የሚጠሩት) የተባለው የትግራይ ሰው ለወያኔ የቆመ ጋዜጠኛ ነው።
መቸም ሕሊና ላለው ሰው ምኒሊክ ወደ ትግራይ መጥተው የትግራይን ሕዝብ ከጠላት ወረራ እንዲያድኑት የተማጸነው ማን አንደሆነ የታሪክ ሰነዶች ያነበባችሁ የምትስቱት አይደለም። ሚኒሊክ ወደ ትግራይ ዓድዋ የዘመቱት ገብረኪዳን ደስታ እና የገብረኪዳን አስተማሪዎች የነበሩ በሚኒለክ ዘመን የኖሩ እነ ደብተራ ፍስሃ አብየ እዝጊ አንደሚሉት “ምኒልክ ወደ ትግራይ ያደረጉት ዘመቻ እነዚህን “ሁለት ነጥቦች” ለማሳካትና ተግባራዊ ለማድረግ ነዉ” የሚለው ውንጀላ ምንኛ እውነትን የሚረግጥ ክህደት መሆኑን ብዙ ትንተና የሚያስፈልገው ስላልሆነ ለናንተ ፍረድ እተወዋለሁ። ምኒልክ ጥሪውን ተቀብለው ጣልያን ባይመቱት፤ እናቶቻችን ብዙ የጣሊያን ዲቃላ ባፈሩልን ነበር።እናት አያቶቻችን በሰላቶ ጎረምሶች በተደፈሩ ነበር። ወንድ አያቶቻችንም የጣሊያን ጀርዲን (ጋርደን) ውሃ አጠጪ እና ዘበኛ፤ ወይንም እንቁላል ጠባሽ በሆኑ ነበር። በኤርትራ የደረሰ ውርደት ሁሉ በትግራይ ማሕበረሰብ በደረሰ ነበር። እድሜ ለምኒሊክ አንዳንል፤ ወያኔዎች ያ ሁሉ ውለታ እረስተው ‘ምኒሊክ ለብር ዘረፋ እና ትግራይን አደህይቶ ለመግዛት” አንዲያመቸው ነው ወደ ትግራይ ዓድዋ የመጣው ማለት ከባድ ወንጀል ነው። የሚኒልክ ደግነት እና በጎ ስራ ሰሪነት አንዲሁም የትግሬ መኳንንት ጎርበጣ ባሕሪ እና አርስ በርስ መጠላለፍ እና መገዳደል ባሕሪ የዘመኑ ምሁር የነበሩት የትግሬው ተወላጅ “ነጋድራስ ገ/ሕይውት ባይከዳኝ ” ስለ ምኒሊክ የጻፉትን በጎነት እና መልካም ስራ ማንበብ ነው። አሳዛኙ ግን ነጋድራስ ስለ ምኒሊክ ደካማ ጎን የጻፉትን እያጐሉ ፤ስለ በጎ ምግባራቸው እና ለትግራይ እና ስለ ኢትዮጵያ ያደረጉት አስተዋፅኦ የጻፉላቸውን እየደበቁ ወያኔዎች የገብረህይወት ባይከዳኝን ብዕር ሲያበላሹ ማየት በጣም ያሳዝናል። በዚህ ላይ ሌላ ቀን እመለስበታለሁ። እንደርታዊዉ ተወላጅ የወያኔው ዘፋኝ ኪዳነማርያም ረዳ
“ንአብነት ማይ ጨዉ ዓድዋ እንተዘከርና፤ ተምቤን ዓቢይ ዓዲ ሽረ እንዳባጉና፤ ኩይናት ምስ ገበሩ እቶም ወለድና፤ ጸላኢ ደምሲሶም ታሪኽ ሓደጉልና። ጨቆንትና አምሓሩ ምስ ታሪኽ ፀሓፍቶም ንዓና ዓብሊሎም ታሪኽና ጎቢጦም አለዉ ይምክሑ ብደም ወለድና፤ ንቃለስ ተጋሩ ክንመልስ ቅያና “
ትርጉም፦ ሓቀኛ ታሪክ ተደብቆ አይቀርም ለምሳሌ የማይጨዉን፤ የዓድዋን፤የሽረ የእንዳባጉናን ታሪክ ስንመረምር ወራሪዎችን ድባቅ በምመታት ትግሬ ወላጆቻችን አኩሪ ታሪክ ትተዉልን አልፈዋል። ይሁን እንጂ፤አባቶቻችን ብብዙ ዓዉደ ዉግያዎች ደማቸዉን አፍስሰዉ ያስመዘገቡትን ታሪክ “(ጨቆንትና አምሓሩ ምስታሪኽ ፀሓፍቶም”) “ጨቋኞቻችን አማሮች እና ታሪክ ጸሃፊዎቻቸዉ” በአሁኑ ወቅት እየተኮፈሱበት ነዉ። ታሪካችንን ቀብረዉ በአባቶቻችን ደም/ታሪክ እየተመኩበት ናቸዉ እና የትግራይ ተወላጆች የሆንን በሙላ ታሪካችነን ለማሳደስ በፅናት መታገል አለብን!” ይል ነበር፤ ተደርሶ የተሰጠው በረሃ ላይ እያለ የወያኔ ሙዚቀኛ የነበረው ዘፋኝ ኪዳነ ማርያም ረዳ። ምንጭ (ይድረስ ለጎጠኛው መምህር፤- ደራሲ ጌታቸው ረዳ።)
ይህ እጅግ ወደ ታች የዘቀጠ ዘረኛነት እና ውሸት ሰፊ ትንተና የሚያስፈልገው አይመስለኝም። እያንዳንዱ አንባቢ በቀላሉ የሚፈርደው ነው። ሆኖም ወላጆቻችን በጦርነት የመሸሽ ታሪክ፤ ምንም ወንጀል፤ ምንም የባንዳ ስራ እንዳልተሳተፉ አድርጎ የሚያቀርብ ጀብደኝነት የአማራ አዋቂዎች አንደሚሉት “አሳ ጐርጓሪ ዘንዶ ያወጣል…” ነው እና ይህንን ታሪክ አስኪ አብረን አንመልከት እና ፍርዱን ሰጥተን አንሰናበት።አቡነ ጴጥሮስ አገሬን እና ሃይማኖቴን ለፋሺስት ሕዝብ አጎንብሶ አንዲሰግድ አልፈቅድም ብለው፤የድለላ ገንዘብ እና ማዕረግ ይሰጠዎታል ቢባሉም “ግንባሬ ለጥየት” ብለው በአምላካቸው ጽናት ተሞርኩዘው መስዋዕት ሲሆኑ ወላጆቻችን ቀሳውስተ አክሱም እና ዓዲግራት እንዲሁም ዓድዋ… ዘምባባ እያውለበለቡ እንደክርስቶስ “ንሴብሖ” የሚለው ውደሳ እያስተጋቡ ለፋሺስቶች ሲሰግዱ ተመዝገቧል።
ይህ የወላጆቻችን ታሪክስ ለማን ልንሰጠው ነው? አማራዎች በኛ ታሪክ እየኮሩ በባዶ ታሪካቸው እየፎረከሩ ነው እየተባለ በአማራ ላይ የተዘፈነው ዘፈን ነውር አይደለም ወይ? ታሪክ እንፍራ አንጂ! አማራዎች እና ትግሬዎች እኮ ያንድ እናት እና ልጅ ወንድማማቾች ናቸው። ከሁለቱም አብራኮች የወጣን ትግሬዎች እኮ ነን። አስኪ ይህንን ቪዲዮ/ፊልም ተመልከቱት እና ራሳችንን እንፈትሽ። ሁሉም ጎሳ የራሱ መጥፎ ታሪክ እና ደካመ ጎን አስመዝግቧል። አንዴት እኛ ትግሬዎች ብቻ ጀግንነት ብቻ የሰራን እንጂ ደካመ ጎን የለንም ብለን ሌላውነ ከዳተኛ እያልን በድርቅና አንከሳለን። ገብረኪዳን ደስታ በትግርኛው ቃለ ጠይቁ “ትግራዋይ እማ ነፀላኢኡ አይነብርከኽን/አይሰግድን፤ንጥልያን፤ ንድረቡሽ ተምበርኪኺ አይፈልጥን” ሲለን (ትርጉሙ “ትግሬ በታሪኩ ለጠላት ተምበርክኮ ፤ተጎንብሶ ሰግዶ አያውቅም። ለማንኛውም ጣሊያን ይሁን ድርቡሽ ሰግዶ እጁን ሰጥቶ በታሪካችን የታየበት የተመዘገበበት ወቅት ከቶ የለም!” የተንበረከኩ የሰገዱ ሌሎች ናቸው። ሲለን ይህ ከዚህ በታች ያለው ፊልም እሰኪ ተመልከቱ እና የገብረኪዳን ውሸትና እውነት እናመሳክረው።
Tigray ([deleted]) Ethiopians WORSHIPING Italian Colonialist inhttp://youtu.be/_20tOa8C6VU
Le bellezze di Axum, antica capitale etiopica. http://youtu.be/v3oBb0SAfqkLa popolazione indigena offre i propri servigi alle truppe colonialihttp://youtu.be/YEK5LexH1aE Il Vicerè Graziani in visita a Adigrat e Decamerè http://youtu.be/5Vn_ZLzhy_0
በሚቀጥለው ክፍል 2 ጽሑፌ ገብረ ኪዳን ደስታ አጼ ዮሐንስ ትግራይ ውስጥ ከዓፋር ማሕበረሰብ የነበራቸው ግንኙነት በሰላም በመከባበር አንደነበረ በውሸት የገለጸው፤የተዛባ ታሪክ በሰፊው እንተነትነዋለሁ። ሚኒልክ እና ቴዎድሮስ አንጂ ዮሐንስ በሃይል አላስገበሩም የሚለው ቅዠት፤ ከስሑል ሚካል ጀምሮ እስከ አጼ ዮሐንሰ ድረስ ከዓፋሮች ጋር የተደረገው ጦርነት፤ዝርፍያ የሴት ጥልፊያ (ዓፋሮች አንደሚከስሱት ከሆነ ንጉሱ ልጃቸው አርአያስላሴ የተወለደው ከሔርቶው የዓፋር ጎሳ መሪው ከ ‘ያኩሚ ሲረ ዓሊ’ ልጅ ከዴቶ ሲረ ዓሊ የተወለደው ልጅ አርአያስላሴ እናቱ ዴቶ አባቱ ደጃዝማች ካሳ (ዮሐንስ) በሽፍተነት ጊዜያቸው አንዴት በጉልበት አንደጠለፏት እና አርአያን አንዴት እንደወለዱት በዓፋሮች የተጻፈ ሙግት አቀርባለሁ። እንዲሁም በትግሬ ገዢዎች እና ዓፋር ባላባቶች የተደረገ ረዢም የደም መፋሰስ ውጊያ እስካሁን ድረስ መብረድ ለምን አንዳልቻለ እንመለከታለን። ወያኔዎች የራሳቸውን ነገሥታት ጛዳ እየደበቁ የሌሎቹን ጎሳዎች ነገሥታት እና መሳፍንቶች ወንጀል ሲቦረቡሩ “አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል…….” ነውና ሳንወድ የራሳችንን ጉድ ቦርቡሬ ማሳየት ሃላፊነት ስላለብኝ፤ በሚቀጥለው ክፍል ሁለት አንመለከታለን።
ወያኔዎች የፋሺስት ሃዋርያዎች ናቸው!
በመጨረሻም ወያኔ የፋሺስት ሐዋርያዎች/ደቀመዝሙሮች ናቸው ለምን ትላቸዋለህ;፡የወያኔ ስራ እና የሙሶሎኒ ስራ ይለያያል እያሉ ሲሞጉትኝ ለነበሩ ሰዎች በአንድ የማከብረው ውድ ወዳጄ የተላከልኝን ካነበበው መጽሐፍ አጭር መረጃ ላስነብባችሁ እና ልሰናበት። ከታች የምታዩት ሰነድ፤ንግግር፤ተግባር፤ፖሊሲ፤ትዕዛዝ እና ንገግር፤ መለስ ዜናዊ እና ግበረ አበሮቹ በኑሮ ምክንያት ከአማራ ቀዬአቸው ለቀው ወደ ደቡቡ አገራቸው በመጓዝ በሚኖሩ አማራዎች የወሰዱት እርምጃ ድሮ ሙሶሎኑ እና ረዳቶቹ የቀየሱት ፖሊሲ አንደነበረ እና ያ ስራ ወያኔዎች አንዴት ተግባራዊ አንዳደረጉት ለማነጻጸር ይረዳችሁ ዘንድ ይኼው አንብቡት።
ወያኔዎች የፋሺስት ሙሶሎኒ ደቀ መዝሙሮች ናቸው የምንለውም ለዚህ ነው።
በዶክተር ጌታቸው ረዳ

No comments:

Post a Comment

wanted officials