በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ
ሰማያዊ ፓርቲ በ19/2006 ዓ.ም ለሚደረገው ሰላማዊ ሰልፉ ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ በአስሩም ክፍለ ከተሞች ቅስቀሳ የጀመረ ሲሆን በአብዛኛዎቹ ክፍለ ከተሞች ቅስቀሳው እየተካሄደ እንደሚገኝ ከሰልፉ አስተባባሪዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይሁንና በአንዳንድ አካባቢዎች ፖሊስና ደህንነቶች ቅስቀሳውን ለማስቆም የሞከሩ ሲሆን በካሳንችስ፣ አቧሬና አራት ኪሎ መስመር ሲቀሰቅሱ የነበሩ 6 አባላትና ደጋፊዎች በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ካሳንችስ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደሚገኙም ለማውቅ ተችሏል፡፡
እንዲሁም በስድስት ኪሎ መነን፣ ሽሮ ሜዳ መስመር ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩት ሌሎች 6 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መነን አካባቢ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በፖሊስ ተይዘዋል፡፡ አባላቱ ለፖሊስ ሰላማዊ ሰልፉን ማሳወቃቸውን ገልጸው የሰላማዊ ሰልፍና ህዝባዊ ስብሰባማሳወቂያ ክፍል ፈርሞ የተቀበለው ደብዳቤ ቢያሳዩዋቸውም ‹‹ልናነጋርራችሁ እንፈልጋለን!›› በሚል ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደዋቸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት መነን ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ፡፡
በሌላ በኩል ከሁለቱ መስመሮች ውጭ በሌሎች አካባቢዎች ሲቀሰቅሱ የነበሩ አባላት ስራቸውን አከናውነው ተመልሰዋል፡፡
ተጨመሪ መረጃዎችን እየተከታተልን እናሳውቃለን!

No comments:
Post a Comment