የፌዴራልዋናኦዲተር በትምህርት ተቋማት፣ በውጭጉዳይና በመከላከያ ውስጥ ከፍተኛ የገንዘብ ጉድለት መኖሩን አመለከተ
ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመ/ቤቱዋናኦዲተርየሆኑትአቶገመቹዱቢሶየ2005 ዓ.ምየኦዲትሪፖርታቸውን ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት በ132 የመንግሥትመ/ቤቶችላይበተካሄደውኦዲትከፋይናንስሥርዓት፣ደንብናመመሪያጋር የሚጋጩበርካታግድፈቶችመታየታቸውንአመልክተዋል፡፡ የትምህርት ተቋማትና መከላከያ ከፍተኛ የገንዘብ ጉድለት ከተገኘባቸው መስሪያ ቤቶች መካከል በቀዳሚነት ተጠቅሰዋል።
ዋናኦዲተሩባቀረቡትና 54 ያህል ገጾችንበያዘውበዚሁሪፖርታቸውሂሳብበወቅቱያለማወራረድችግር፣የተሟላየወጪማስረጃሳይቀርብበወጪ
ተመዝግቦመገኘት፣ደንብናመመሪያሳይከተሉግዥዎችንመፈጸም፣የጥሬገንዘብጉድለቶች፣በብልጫየተከፈሉ ሂሳቦች፣ቀረጥተከፍሎባቸውገቢለመሆናቸውማስረጃያልቀረበባቸውሂሳቦች፣ከበጀትበላይወጪማውጣትና የመሳሰሉየሂሳብአሠራርግድፈቶችበበርካታመ/ቤቶች ታይተዋል፡፡
የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ አያያዝና አጠባበቅ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፤ በ5 መ/ቤቶች ብር 1 ሚሊዮን ,272,ሺ 93ብር ከ33 ሳንቲም የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ሲገኝ፣ ጉድለት የተገኘባቸው ዩኒቨርስቲዎች ተብለው የተጠቀሱት ደግሞ ጂማ፣ ሰመራ፣ ወሎ፣ ባህርዳርና ጅጅጋ ናቸው፡
ተመዝግቦመገኘት፣ደንብናመመሪያሳይከተሉግዥዎችንመፈጸም፣የጥሬገንዘብጉድለቶች፣በብልጫየተከፈሉ ሂሳቦች፣ቀረጥተከፍሎባቸውገቢለመሆናቸውማስረጃያልቀረበባቸውሂሳቦች፣ከበጀትበላይወጪማውጣትና የመሳሰሉየሂሳብአሠራርግድፈቶችበበርካታመ/ቤቶች ታይተዋል፡፡
የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ አያያዝና አጠባበቅ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ኦዲት ሲደረግ፤ በ5 መ/ቤቶች ብር 1 ሚሊዮን ,272,ሺ 93ብር ከ33 ሳንቲም የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ሲገኝ፣ ጉድለት የተገኘባቸው ዩኒቨርስቲዎች ተብለው የተጠቀሱት ደግሞ ጂማ፣ ሰመራ፣ ወሎ፣ ባህርዳርና ጅጅጋ ናቸው፡
በጉድለት የታየው የጥሬ ገንዘብ ሂሳብ ተገቢው እርምጃ ተወስዶ እንዲተካ ለየመ/ቤቶቹ በተላከው የስራ አመራር ሪፖርት ማሳሰባቸውን ዋና ኦዲተሩ አመልክተዋል።
በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በሂሳብ መግለጫ ሪፖርት የተደረገውና በቆጠራ የተገኘው ጥሬ ገንዘብ መካከል በ3 መ/ቤቶች ማለትም በደብረ ማርቆስና ባህርዳር ዩኒቨርስቲዎች እና አላጌ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ቆጠራው በብር 997 ሺ,412 ከ79 ሳንቲምልዩነት በማነስ የታየ ሲሆን በአጠቃላይ በ24 መ/ቤተችም የተለያዩ የጥሬ ገንዘብናየባንክ ሂሳብ አያያዝ ድክመቶች እንደሚታዩ በኦዲቱ ተረጋግጧል፡፡
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ደንብ ቁጥር 190/2002 አንቀጽ 32 እስከ 35 በተደነገገው መሠረት የሰነድ ሂሳብ በወቅቱ መወራረዱ ሲጣራ በ77 መ/ቤቶች ብ 877 ሚሊዮን 45 ሺ 264 ብር ከ30 ሳንቲም በደንቡ መሠረት በወቅቱ ሳይወራረድ ገኝቷል፡፡
ከዚህ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት በግብርና ሚኒስቴር የግብርና ቴክኒክ ሙያና ትምህርት ስልጠና ማስተባበሪያ 173 ሚሊዮን 607 ሺ 265 ብር ከ52 ሳንቲም፤ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር 149 ሚሊዮን 427 ሺ 709 ብር ከ65 ሳንቲም ፤ የትምህርት ሚኒስቴር 100 ሚሊዮን 298 ሺ 362 ብር ከ09 ሳንቲም፤ የሀገር መከላከያ ሚ/ር 97 ሚሊዮን 146 ሺ 944 ብር ከ59 ሳንቲም፤ ግብርና ሚ/ር 77 ሚሊዮን 744 ሺ 994 ብር ከ72 ሳንቲም ፤ጎንደር ዩኒቨርስቲ 32 ሚ ሊዮን153, 328 ብር ከ69 ሳንቲም፤ ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ 26 ሚሊዮን 671 ሺ 151 ሺ 92 እና የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 22 ሚሊዮን 945 ሺ ,234 ብር ከ57 ሳንቲም ይገኙበታል፡፡
ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳቡ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት በወቅቱ ካልተወራረደ ወይም ካልተሰበሰበ በቆየ ቁጥር የመሰብሰብና ወደ ሀብትነት የመለወጥ እድሉ ተዳክሞ ለብክነት በር የሚከፍት በመሆኑ መ/ቤቶቹ የፋይናንስ ደንብና መመሪያዎችን ተከትለው ገንዘቡን እንዲሰበስቡ ወይም እንዲያወራርዱ ዋና ኦዲተሩ አሳስበዋል።
የዕቃና አገልግሎት ግዢ በመንግሥት ደንብና መመሪያ መሠረት የተፈፀመ መሆኑን ለማጣራት ኦዲት ሲደረግ፤ በ43መ/ቤቶች ብር 165 ሚሊዮን 892 ሺ 637 ብር ከ56 ሳንቲም የመንግሥትን የግዢ አዋጅ፤ ደንብና መመሪያ ያልተከተለ ግዢ ተፈፅሞተገኝቷል፡፡
ከግዥ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ ውጭ ግዥ የፈፀሙ መ/ቤቶች መካል፤ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ 32 ሚሊዮን 061 ሺ 100.ብር፤ጂማ ዩኒቨርስቲ 19 ሚሊዮን 117 ሺ 878 ብር ከ73 ሳንቲም፤ አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ 18 ሚሊዮን 344 ሺ 467 ብር ከ.23 ሳንቲም፤ ማዕድን ሚ/ር 16 ሚሊዮን 274, ሺ 515 ብር ከ25 ሳንቲም እና አክሱም ዩኒቨርስቲ 14 ሚሊዮን 168, ሺ 410 ከ69 ሳንቲም ይገኙበታል።
ካልተከተሏቸው የግዥ ደንብና መመሪያዎች ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ በማውጣት ሊፈፀሙ የሚገባቸውን ግዢዎችያለጨረታ ማስታወቂያ በመግዛት፤ በዋጋ ማወዳደሪያ መፈፀም ያለበትን ግዥ ውድድር ሳይደረግ መፈፀም እና የውስን ጨረታ የግዥ ዘዴ ተግባራዊ የሚሆነው ግልጽ ጨረታ ሁለት ጊዜ ወጥቶ እቃው በሚፈለገው ጥራትናመጠን ካልተገኘ ቢያንስ አምስት አቅራቢዎች በውስን ጨረታ መጋበዝ የሚለውን ሳያሟሉ ግልጽ ጨረታ ያላወጡና በውስን ጨረታው የግዥ ዘዴ በቂ አቅራቢዎች ሳይጋብዙ ግዥን ማከናወን የሚሉት ይገኙበታል፡፡
የግዢ መመሪያን ሳይከተሉ ግዢ መፈፀም ለምዝበራና ለጥራት መጓደል ጭምር የሚያጋልጥ በመሆኑ የመንግሥት ግዢደንብና መመሪያን አክብረው በማይሰሩ መ/ቤቶች ላይ የተጠናከረ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ብሎአል መስሪያ ቤቱ።
ኦዲት በተደረጉት መ/ቤቶች ደንብና መመሪያ ተጠብቆ ክፍያ መፈፀሙ ሲጣራ በ41 መ/ቤቶች 75 ሚሊዮን ,992 ሺ ,434. ብር ከ84 ሳንቲም ከደንብና መመሪያ ውጭ ተከፍሎ ተገኝቷል፡፡
በደንብና መመሪያ ውጪ አለአግባብ ክፍያ ከፈፀሙ መ/ቤቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ፣ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር 24 ሚሊዮን ብር፤ ጎንደር ዩኒቨርስቲ 10 ሚሊዮን,196, ሺ 507 ብር ከ81 ሳንቲም፤ ጅማ ዩኒቨርስቲ 8, ሚሊዮን 605 ሺ 050.ብር ከ51 ሳንቲም፤ መቀሌ ዩኒቨርስቲ 7,ሚሊዮን 190 ሺ ,691 ብር. ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 6, ሚሊዮን 62,ሺ 182.ብር ከ75 ሳንቲም እና ሚዛን -ቴፒ ዩኒቨርስቲ 4 ሚሊዮን 956 ሺ ,941 ብር ከ.47 ሳንቲም ነው።
ከምክንያቶቹም መካከል ከሚመለከተው አካል ሳይፈቀድ የትርፍ ሰዓት ክፍያ በመፈፀም፣ ሰራተኞች መስክ ሳይወጡ የውሎአበል በመክፈልና የአልጋና የምግብ ወጪያቸው በመ/ቤቱ ተሸፍኖ እያለ የውሎ
አበልበመክፈልና እና የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሳይፈቅድ የኃላፊነት አበልና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞችን ለዩኒቨርስቲ የስራአመራሮች ክፍያ መፈፀም፣ መ/ቤቱን ለለቀቁና ሥራ ላይ ለሌሉ ሰራተኞች ክፍያ መፈፀምና በመሳሰሉት ምክንያቶች ወጪ የተደረጉ መሆናቸው በኦዲቱ ተረጋግጧል፡፡
በመሆኑም ከደንብና መመሪያ ውጪ ያለአግባብ የተከፈለው ሂሳብ ተመላሽ እንዲሆንና ለወደፊቱም ደንብናመመሪያዎች ተከብረው መስራት እንዳለበት ኦዲት ለተደረጉት መ/ቤቶች ማሳሰቡን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።
No comments:
Post a Comment