ፓኪስታናዊቷ ማላላ ዩሳፍዛይ የኖቤል ሽልማቷን ተረከበች
በህፃናት መብት ዙሪያ ጠንካራ ተሳትፎ የነበራት የ17 ዓመቷ ፓኪስታናዊት ወጣት ማላላ ዩሳፍዛይ የኖቤል ሽልማቷን ተረከበች።
ከህንዳዊው ካሊሻ ሳትያሪቲ ጋር በመሆን የኖቤል ሽልማቱን ተጋርታለች።
ሁለቱ በህፃናት መብት ዙሪያ ባበረከቱት አስተዋፅኦ ነው ለሽልማት የበቁት።
የ17 ዓመቷ ማላላ ሽልማቱ ከፍተኛ ደስታን ፈጥሮብኛል በቀጣይም በህፃናት መብት ዙሪያ ጠንካራ ሆኜ እንድሰራ የሚያነሳሳኝ ነው ብላለች፡፡
እ.ኤ.አ 2012 ወርሀ ጥቅምት ላይ ማላላ ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታቸው በመሄድ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እየቀሰቀሰች በነበረችበት ወቅት በታሊባን ታጣቂዎች በተተኮሰባት ጥይት ጭንቅላቷ ላይ መመታቷ የሚታወስ ነው፡፡
ማላላ በኖቤል የሰላም ሽልማት ታሪክ በእድሜ የምንጊዜም አነስተኛዋ ተሸላሚ ሆናለች፡፡
የኖቤል አሸናፊዎቹ ሽልማታቸውን የኖርዌይ ንጉስ ሃራልድ አምስተኛ በታደሙበት ከኖርዌይ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ ሰብሳቢ እጅ ተረክበዋል።
በኦስሎ በተካሄደው በዚህ የሽልማት ስነስርዓት ሜዳለያና 1.4 ሚሊዮን ዶላር ለአሸናፊዎቹ ተበርክቷል።
They can shoot my body but the cannot shoot my dream is her popular saying
No comments:
Post a Comment