Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, December 31, 2014

እንግሊዛዊው በኢትዮጵያ እስር ቤት የሚገኘው በሽብርተኝነት ተጠርጥሮ የሞት ቅጣት እንደሚጠብቀው ተሰማ


በሽብርተኝነት ተጠርጥሮ በኢትዮጵያ እስር ቤት የሚገኘው እንግሊዛዊው አሊ ኦዶረስ የሞት ቅጣት እንደሚጠብቀው ተሰማ፡፡ ኢንዲፔንደንት የተሰኘው የዜና ምንጭ እንዳስነበበው እንግሊዛዊ ዜግነት ያለው ይህ ግለሰብ በለንደን የደህንነት ባለሙያ ሲሆን በኢትዮጵያ ከተያዘ አንድ አመት ከስድስት ወራት ተቆጥረዋል፡፡ የሽብርተኝነት ውንጀላው የፈጠራ ነው ተብሏል፡፡ እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሀይ ኮሚሽን ገለፃ ተጠርጣሪው በእስር ቤት ቆይታው ከፍተኛ እንግልትና በደል እየደረሰበት ነው፡፡ በኤሌክትሪክ ማስያዝ እንዲሁም ድብደባ ደርሶበታል የሚል ቅሬታ ቀርቧል፡፡ ተጠርጣሪው በትውልድ ኢትዮጵያዊ ሲሆን ገና ልጅ እያለ ነበር ወደ እንግሊዝ የሄደው፡፡ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት የሆነው አሊ MI5 ተብሎ በሚታወቀው በእንግሊዙ የደህንነት አገልግሎት እና ሜትሮፖሊታን ፖሊስ አገልግሎት ከአክራሪ ቡድን ጋር ግንኙነት አለው በሚል መወንጀሉን አይቀበለውም፡፡ ባለቤቱ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት የተላለፈውን ውሳኔ ሚዛናዊ አይደለም ስትል ቅሬታዋን ታሰማለች፡፡ ፍርድ ቤቱ ህግን ያልተከተለ ውሳኔ ነው ያስተላለፈው ስትል መናገሯን ኢንዲፔንደንት አስነብቧል፡፡ ‹‹ምናልባትም የቃቤ ህግ ምስክሮች በግዴታ ወይም በመታለል በባለቤቴ ላይ የተሳሳተ ምስክርነት ሳይሰጡ አይቀሩም›› ስትል ትናገራለች፡፡ የዜና ምንጩ እንደገለጸው ከእንግሊዝ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ መንገስት የደረሰው ደብዳቤ በግለሰቡ ላይ እየደረሰ ያለው ነገር ከአለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ህግ ውጪ ነው ይላል፡፡ የአሊ አዶረስ የህግ ባለሙያ እንደሚለው በ 2013 በቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ መረጃ እንዲያወጣ ድብደባ እና ኤሌክትሪክ ንዝረት ደርሶበታል፡፡ ተጨማሪ ዝርዝሩን ያገኛሉ…...source,-http://www.diretube.com/

No comments:

Post a Comment

wanted officials