ዛሬ ጠዋት መስቀል አደባባይ ከተያዙት ባሻገር ከሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ወደ መስቀል አደባባይ ሲያመራ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው የሰማያዊና የሌሎች የ9ኙ ትብብር አባል ፓርቲ አማራሮች፣ አባላትና የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች በአሁኑ ወቅት ጨርቆስ ፖፖላሬ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የታፈሱት አመራሮች ማዕከላዊ አጠገብ ወደሚገኘው እስር ቤት ተዛወሩ
9ኙ ፓርቲዎች በጠሩት ሰላማዊ ሰልፍ የታፈሱትና ጨርቆስ ፖፖላሬ እስር ቤት ታስረው የነበሩት የፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና የሰላማዊ ሰልፍ ተሳታፊዎች ማዕካለዊ ጥግ ወደሚገኘውና በተለምዶ ሶስተኛ ተብሎ ወደሚጠራው እስር ቤት መዛወራቸው ታወቀ፡፡ታሳሪዎቹ ከጨርቆስ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ሶስተኛ የተዛወሩት ከምሽቱ አንድ ሰዓት በኋላ ሲሆን ሶስት ሰዓት ተኩል አካባቢ በሶስት መኪና የታጨቁ ታሳሪዎች ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መድረሳቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ በተመሳሳይ በሌላ አውቶቡስ የተጫኑ እስረኞች ወደ ሌላ እስር ቤት መዛወራቸው ታውቋል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ ለታሳሪዎች እራትና ልብስ ሊያድሱ ወደ እስር ቤት ያቀኑት ቤተሰቦችና የትግል አጋሮች ምግብ እንዳያስገቡ መከልከላቸውን ገልጸዋል፡፡ በሌላ ካሳንቺስ አካባቢ የሚገኘውና ስድስኛ ተብሎ በሚጠራው እስር ቤት አካባቢ ሌሎች ታሳሪዎች እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ጨርቆስ እስር ቤት ታስረው የነበሩት ሁሉም አመራሮች፣ አባላትና የሰልፉ ተሳታፊዎች ወደ ሶስተኛ ወይንም ሌላ እስር ቤት ይዛወሩ አይዛወሩ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም፡፡
የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና ተሳታፊዎች ከታፈሱበት ጊዜ ጀምሮ ሶስት ያህል እስር ቤቶች እንደተዛወሩ ለማወቅ ተችሏል፡
የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ አባላትና የሰላማዊ ሰልፍ ታሳታፊዎቹ ካሳንቺስ 6ኛ መምሪያ ተወስደው የነበር ሲሆን ጠያቂዎች በሄዱበት ወቅት ‹‹የሉም!›› እያሉ ሲመልሶ ቆይተዋል፡፡
ታሳሪዎቹ ወደ ጨርቆስ ከተዛወሩ በኋላ የአካባቢው ህዝብ ሱቅ እንዲዘጋና እንቅስቃሴውን እንዲቀንስ እንደተደረጉ ታሳሪዎቹን ለመጠየቅ ወደ ቦታው ያቀኑ የፓርቲዎቹ አባላት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ታሳሪዎቹን ለመጠየቅ የሄዱት ሰዎች ‹‹ምርመራ ላይ ስለሆንን አናሳይም፡፡›› እንዳሏቸው ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል ከሰማያዊ ጽ/ቤት ተነስቶ ወደ መስቀል አደባባይ ሊያቀና በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት የት እንዳሉ ለማወቅ አልተቻለም፡፡ በዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ ከ300 በላይ አመራሮችና አባላት እንደታሰሩ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፍዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከታሰሩት መካከል አብዛኛዎቹ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል
በሰልፉ ሰልፉ ወቅት ታፍሰው ከታሰሩት መካከል አብዛኛዎቹ እጅና እግራቸውን እንደተሰበረ እማኞች ገልጸዋል፡፡ ታሳዎቹ መጀመሪያ ከነበሩበት ጨርቆስ አካባቢ የሚገኝ እስር ቤት ምሽት ሶስት ሰዓት ላይ ሶስተኛ ወደተባለው እስር ቤት ሲዘዋወሩ እያነከሱና በሌሎች ታሳሪዎች ደግፈዋቸው ታይተዋል፡፡ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት እጁን እንደተሰበረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህም ባሻገር ብርሃኑ ተክለያሬድና ሌሎች በርካታ ታሳሪዎች በሌሎች ታሳሪዎች ተደግፈው ታይተዋል፡፡
No comments:
Post a Comment