Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, December 5, 2014

ጠቅላይ ሚንስተር ሃይለማሪያም ደሳለኝ በበርሊን ጀርመን ታላቅ ተቃውሞ ገጠማቸው

ዋናው አጀንዳው ለህወሃት መራሹ የ ኢትዮጵያ መንግስት ላጋጠመው የገንዘብ እጥረት ከ ጀርመን ባንክ /ዶቼ ባንክ/ ገንዘብ ለመለመን ነበረ ጠቅላይ ምንስቴር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከኢትዮጵያ ጀርመን በርሊን የገቡት።በበርሊን የተገኙ ኢትዮጵያውያንም  በ አጭር ጊዜ ውስጥ በማዘጋጀት የሰልፉን አላማ
-በኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት የፖሊቲካ እስረኞች በጠቅላላ ባስቸኩዋይ እንዲፈቱ
-ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲቆም
-ኢትዮጵያውያንን የሚያፈናቅሉ የሸንኮራ አገዳ እርሻ እና መሬት ቦንድ በዶቸ ባንክ በኩል ለዉጭ ነጋደዎች በዶላር ሽያጭን በመቃወም የጀርመን መንግስት እንዲሁም ያገሩ ነጋዴዎች እና
ዶቸ ባንክ ጸረ ሰብአዊነት ወንጀል ላይ መካፈሉን እንዲያቆሙ
-የጀርመን መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን ላይ ላለው አምባገነን ስርአት የሚሰጠውን ድጋፍ እንዲያቆም በመጠየቅ
 ጥሪ አስተላልፈዋል። ከበርሊን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሰልፈኞች በተጨማሪ ከፍራንክፈርትና ከ ኑረምበርግ ከተሞች የተነሱ ሰልፈኞች ሌሊቱን ከ ሰባት ሰዓት በላይ በመጓዝ ተቀላቅለዋቸዋል።

በሃገረ ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ከተሞች ወደ ፍራንክፈርትና ኑረምበርግ ከተሞች በመጓዝ ለነሱ ወደተዘጋጁ አውቶብሶች በመግባት ለሊቱን ሲጓዙ አድረው በቀዝቃዛው ጧት ዴሴምበር 3 በርሊን ደርሰዋል። እነዙሁ ሰልፈኞች በ በርሊን ፖሊሶች መንገድ መሪነት ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ሰልፍ አስተባባሪነት  በዋና ዋና የበርሊን አውራ ጎዳናዎች  ፥በጀርመን ዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፊትለፊት በዋናው የጀርመን ባንክ ዶቼ ባንክ ፊትለፊት ቀጥሎም የእርዳታና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ጽቤት ፊትለፊት፥ የቻንስለሯ ኣምት ጽ/ቤት ቡንደሰታግ ፓርላማ ፊትለፊት እንዲሁም ሌሎች የውጭ ሃገር ጎብኚዎች በሚበዙበት የ ጀርመን ግንብ በር ፊትለፊት የተለያዩ መፈክሮችን መዝሙሮችን ኢትዮጵያውያኑ በ አማርኛ በ እንግሊዘኛና በጀርመንኛ ቋንቋዎች አሰምተዋል።



በተለይም ቻንስለር አንጌላ መርኬል ጽህፈት ቤት ፊትለፊት ለጠቅላይ ምንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በተደረገው በፖሊስ ማርሽ የታጀበው ኣቀባበል ፕሮግራም የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ሲዘመር ላይ ከፍተኛ የእሪታ የፊሽካ ድምጽ በማሰማት ሃይለማርያም ሌባ ዲክታተር አምባገነን ነው ገንዘቡ ኢትዮጵያውያንን ለማፈን ስለሚውል የገበሬውን መሬት ለማፈናቀል እንዳይሰጥ ሲሉ የ አቀባበል ፕሮግራሙ ላይ ጠሚሓይለማርያም እንዲያፍር አድርገውታል።
የባንዲራ መስቀል ስርዓቱ ወደሚካሄድበትና ጠቅላይ ሚንስትሩ ወደሚገኝበት ቦታ ኢትዮጵያውያኑ በሃይል ካመሩ በሚል ስጋት በሁለት እረድፍ የተሰለፉ የጀርመን ፖሊሶች ሰልፈኞቹን ከትረው ይዘው  ሰልፉ ከሰዓት ካለቀም በሁዋላ ፖሊሶቹ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሲያደርጉ ተስተውለዋል።



No comments:

Post a Comment

wanted officials