Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, December 26, 2014

የባህርዳሩን ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በአንድነት ፓርቲ አደራጅ ላይ ደህንነቶች ድብደባ ፈፀሙ


-------------------------------
የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና አደራጅ አቶ አዕምሮ አወቀ በመንግስት የደህንነት ሀይሎች ታፍነው ዝርፊያና ድብደባ እንደተፈፀመባቸው የፓርቲው ድርጅት ጉዳይ ለፍኖተ ነፃነት አስታወቀ፡፡

አቶ አዕምሮ ዝርፊያና ድብደባው የተፈፀመባቸው በትላንትናው ዕለት በግምት ከምሽቱ 12 ሰዓት ተኩል የፓርቲያቸውን ሰነድ እንደያዙ ከአንድ ኢንተርኔት ካፌ ሲወጡ አምስት የመንግስት የደህንነት አባላት ታርጋ በሌለው ሚኒባስ ውስጥ አስገድደው በማስጋት ከባህርዳር ከተማ በግምት የ35 ደቂቃ በመንዳት ለጊዜው ስፍራው ባልታወቀ ጫካ በማስገባት ድብደባና ዝርፊያ ፈፅመውባቸዋል፡፡ አቶ አዕምሮ ታፍነው ሲወሰዱ አይናቸው በጨርቅ ተሸፍኖና አፋቸው ውስጥም ጨርቅ ተጠቅጥቆ በሰደፍና በዱላ ከፍተኛ ድብደባ የተፈፀመባቸው ሲሆን፣ በእጃቸው የሚገኝ የፓርቲው ሰነድ፣ የባህርዳር ከተማ የአንድነት ጽ/ቤት ቁልፍ፣ ፓስፖርት ፣ሁለት የሞባይል ስልክ ፣ከ800 ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ፣ ለብሰውት የነበረ የቆዳጃ ኬትና ሸሚዝ በደህንነት ሀይሎቹ ተዘርፎ እራቁታቸውን ከምሽቱ 5 ሰዓት ከአርባ አምስት ላይ ጫካ ውስጥ ተጥለዋል፡፡ ዝርፊያና ድብደባ የፈፀሙት የመንግስት የደህንነት ሀይሎች አቶ አዕምሮን “የፓርቲውን የገንዘብ ምንጭ ተናገር፣ አርብ እለት ባህርዳር የተደረገውን ተቃውሞ ያስታበረው አንድነት ፓርቲ ነው” እያሉ ሲደበድቧበው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials