ኦሮምያ ክልል ከሶማሊ ክልል ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት እንዳልቻለ ገለጸ
ኀዳር ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ የጸጥታ ሃላፊ እንደገለጹት በደቡብ እና በቤንሻንጉል ክልሎች አጎራባች ወረዳዎች አሉ ችግሮችን ለመፍታት አንዳንድ ሙከራዎች ቢደረጉም፣ ከሶማሊ ክልል ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት አለመቻሉን ገልጸዋል።
በደቡብ ክልል በአንዳንድ ወረዳዎች የድንበር ችግር መኖሩን የገለጹት ሃላፊው፣ ችግሩን ለመፍታት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል። ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ጋር ያለውን የድንበር ውዝግብ ለመፍታት ተደጋጋሚ ሙከራ መደረጉን የገለጹት ሃላፊው ፣ ይሁን እንጅ መሳሳቦች በመኖራቸው ችግሩ እስካሁን ለመፍፋት አለመቻሉን ገልጸዋል።
ከፍተኛው የድንበር ውዝግብ ያጋጠመው ከሶማሊ ክልል ጋር መሆኑን በመጥቀስ፣ ጉዳዩ በፌደራል መንግስት ደረጃ እየታየ ቢሆንም እስካሁን አለመፈታቱን ገልጸዋል። የተለያዩ ክልሎች እርስበርስ ያላቸው ግንኙነት ጠንካራ አለመሆኑን በስብስባው ላይ ተናግረዋል።
መንግስት ብሄርን መሰረት ያደረገው ፌደራሊዝም ግጭቶችን አስወግዷል በሚል በአደባባይ ቢናገርም፣ የሁሉም ክልል መሪዎች ግጭቶች እየተባባሱ መሄዳቸውን ገልጸዋል። የአማራው ክልል ተወካይ የችግሩ ምንጭ የመልካም አስተዳደር እጦት የፈጠረው በመሆኑ ጸራ ሰላም ሃይሎች እንዳይጠቀሙበት ቶሎ መፍትሄ ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።
No comments:
Post a Comment