የወያኔ/ኢሕአዴግ የውስጥ መተራመስ ቀጥሏል:: በአዲስ አበባ ከወትሮው በተለየ መልኩ ውጥረት ነግሷል::
- የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ በዚህ ከቀጠለ ወያኔ እድሜ አይኖረውም::
- የያዝነው መስመር አያዋጣም:እስከመቼስ እንዲህ ይቀጥላል?” የሚሉ አመራሮች ተነስተዋል::
- ካድሬዎች ሕዝቡን እየዞሩ በመቀስቀስ ዳግም እንዲያደራጁ እየተደረገ ነው::
- የያዝነው መስመር አያዋጣም:እስከመቼስ እንዲህ ይቀጥላል?” የሚሉ አመራሮች ተነስተዋል::
- ካድሬዎች ሕዝቡን እየዞሩ በመቀስቀስ ዳግም እንዲያደራጁ እየተደረገ ነው::
ከምርጫው መምጣት ጋር በተያያዘ የወያኔው ጁንታ በህዝብ እና በተቃዋሚ ሃይሎች ላይ እየወሰደ የሚገኘውን እርምጃ ተከትሎ በወያኔ/ኢሕአዴግ ፓርቲ ውስጥ በአመራሮች ደረጃ የውስጥ መተራመሱ መቀጠሉ ታውቋል::ሕዝቡን ማዋከብ እና ተቃዋሚውን ማሰር እንዲሁም በየጊዜው የሚከሰተው የውጪ ሃይሎች ጫና አደጋ ውስጥ ይከተናል ልንጠነቀቅ ይገባል የያዝነው መስመር አያዋጣም በሚሉ እና በሕወሓት አመራሮች መካከል ከፍተኛ የሆነ ውዝግብ መከሰቱን ለፓርቲው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል::
የተወሰነን ከመተግበርና ከማስፈጸም ውጪ ምንም አስተያየት መስጠት አትችሉም የሚል የቁጣ ቃላቶች ከአቶ ደብረጽዮን የሚወርድባቸው የአቶ ሃይለማርያም የደቡብ ኢትዮጵያ ፓርቲ አመራሮች በማንኛውም የፓርቲ ስብሰባ ላይ የተባለውን ከመደገፍ ውጪ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ታዘዋል::በኢሕአዲግ ውስጥ እየተከሰተ ያለው የአካሄድ ልዩነት አመራሮቹን ከማተራመሱም በላይ በአሁን ወቅት እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ከምርጫ በኋላ ቢሆኑ ይሻላል የሚሉ አስተያየቶችና የምንከተለው መስመር አዋጪነቱ ምን ያህል ነው የሚሉ ጥያቄዎች በከፍተኛ አመራሩ መካከል ልዩነት መፍጠሩ ታውቋል::የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ መስመሩን ለማሳት አዳዲስ የተሳሳቱ መረጃዎች እና የቤት ስራዎች (በተለይ ለዲያስፖራው) እየተዘጋጁ መሆኑን የውስጥ ምንጮቹ ገልጸዋል::
ከአዲስ አበባ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ከተማዋ በውጥረት ውስጥ መሆኗ በገሃድ እየታይ ነው የሃገሪቱ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሕዝቡን ካለማስደሰቱም ውጪ ክፍተኛ የሆኑ የቢዝነስ ስራዎች ከቀድሞው በባሰ መልኩ ቀዝቅዘዋል::የገዢው ፓርቲ ተላላኪዎች በተለያዩ ቦታዎች በመዘዋወር ስለላ እያካሄዱ ሲሆን ሕዝቡም ያለውን ሁኔታ በንቃት እየተከታተለ መሆኑ ታውቋል:: የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ እንደጅምሩ ከቀጠለ ለውጥ እንደሚመጣ እና ወያኗም እድሜ እንደማይኖረው በሚነገርበት በአሁን ሰአት የወያኗ ጁንታ በምርጫው ለሚሳተፉ ተቃዋሚዎች ከፓርላማ 15% ወንበር እንዲመቻችላቸው ከምርጫ ቦርድ ጋር እየሰራ ሲሆን ፓርላማ መግባት ያለባቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦችን በመለየት እና በማዘጋጀት ላይ መሆኑ ታውቋል::
በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች የተከሰተውን ውጥረት ተከትሎ ካድሬ የመንግስት ሰራተኞች ውጡና ቀስቅሱ አደራጁ በማለት ፓርቲያቸው መከራ አብዝቶብናል ሲሉ ማማረራቸው ተሰምቷል::ዳግም በየመንደሩ እየዞሩ በማደራጀት እና በመቀስቀስ ላይ የተሰማሩት ካድሬዎች ወጣቶችን በመቀስቀስ በማደራጅት በመመልመል ዙሪያ አዳዲስ ውይይቶች በኢሕአዴግ አመራሮች ትእዛዝ እየተሰጠ መሆኑ ታውቋል::በዚህም መሰረት አዲስ አበባ ውስጥ በየቀጠናው ካድሬዎቹ የመንግስት ሰራተኞች ስራቸውን እየተዉ ቢሯቸውን ዘግተው ለዚሁ የአደረጃጀት የምልመላ እና ቅስቀሳ ጉዳይ መሰማራታቸው ሲታወቅ መረጃውን ያደረሱኝ ተቃዋሚዎች ወያኔ ያደራጀውን ሃይል ተጠቅመው የጀመሩትን የለውጥ ትግል ገፍተው መቀጠል አለባቸው ሲሉ አስገንዝበዋል::Minilik Salsawi
No comments:
Post a Comment