Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, December 15, 2014

የሰመራ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ዶርማቸው ቬንትሌተር/ማቀዝቀዣ ስላሌለው ደጅ እንደሚያድሩ ተናገሩ

የሰመራ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ዶርማቸው ቬንትሌተር/ማቀዝቀዣ ስላሌለው ደጅ እንደሚያድሩ ተናገሩ:: በአፋር ዋና ከተማ ሰመራ ውስጥ የሚገኘው የሰመራ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለማደሪያነት የተሰጠቸው ዶርሞች/የመኝታ ክፍሎች) ቬንትሌተር/ማቀዝቀዣ ስላልተገጠመለት የበረሃው ሙቀት ከልክ በላይ ስለሆነ ደጅ በመውጣት መሬት ላይ አንጥፈው እንደሚተኙ ተናግረዋል::(ፎቶውን ይመልከቱ)
አብዛኛው ተማሪ ወደ ሰመራ ዩንቨርስቲ ተመድቦ የመጣው ከብርዳማ የሃገሪቱ ደጋማ አከባቢዎች በመሆኑ የአክባቢውን ሙቀትና እንደ ወባ በሽታ ያሉ ችግሮችን መቋቋም እንዳልቻለ ሲታወቅ ቢያምለክቱ ስሚ ስላጡ ደጅ ፍራሾቹን ይዞ በመውጣት ፈርሸው እንደሚተኙ ታውቋል:: የባለስልጣናት ልጆች በሃገሪት ሃብት ፈረንጅ አገር እየተማሩ ባለበት በዚህ ወቅት የደሃው ልጅ በገዛ አገሩ በተለያየ ምክንያት ከትምህርቱ እንዲሰናከል አገልግሎቶችን በማሳጠር ተስፋ ለማስቆረጥ የሚደረግ ደባ ሲሆን የሃይለማርያም ደሳለኝ ልጅ ብጽት ሃይለማርያም ኒውዮርክ ከሚገኘውኮሎምቢያ ዩንቨርስቲ 62.000 የአሜሪካን ዶላር በአመት እየተከፈለላት ስትማር ይህ የአመት ክፍያዋ ለሙሉ የሰመራ ዩንቨርስቲ ዶርሞች ቬንትሬተር/ማቀዝቀዣ ለመግዛት ከበቂ በላይ መሆኑን Minilik Salsawi ይገልጻል::

No comments:

Post a Comment

wanted officials