Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, December 13, 2014

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ለአዲስ አበባ እና ለአከባቢዋ ነዋሪዎች በሙሉ

በሀገራችን ነፃ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ታአማንነት ያለው ምርጫ እውን ለማድረግና የምርጫ ሜዳውን ለሁሉም እኩል
የተመቻቸ እንዲሆን ለማድረግ እንዲቻል የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በተደጋጋሚ ላቀረበለት ሰላማዊና
ሕጋዊ ጥያቄ የኢህአዴግ አገዛዝ እየሰጠ ያለውን የአሻፈረኝ ምላሽና በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ እያካሄደ የሚገኘውን
እስራትና ወከባ ለመቃወም መድረክ ለአዲስ አበባና ለአከባቢዋ ነዋሪዎች ታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓ ም የሚካሄድ የተቃውሞ
ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡
ሰላማዊ ሰልፉ ከግንፍሌ ወንዝ ድልድይ በመነሳት በቀበና ወንዝ ድልድይና በባልደራስ በኩል አድርጎ ወረዳ 8 ኳስ ሜዳ
ድርስ ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት እስከ ከቀኑ 7፡00 ሰአት ድረስ ይካሄዳል፡፡ ስለዚህም የአዲስ አበባና አከባቢዋ ነዋሪዎች
በሙሉ በዚሁ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲሳተፉና በሰላማዊ ትግሉ ድርሻቸውን እንዲያበረክቱ መድረክ ከታላቅ አክብሮት ጋር
ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ድል ለሰላማዊና ሕዝባዊ ትግላችን!!!
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ
Medrek

No comments:

Post a Comment

wanted officials