Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, December 31, 2014

የኦሮምያ ክልል የአድማ ብተና ዋና አዛዥ እስከ ጠባቂዎቻቸው አረፉ

ታኀሳስ ፳፩(ሃያ አንድቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል  በተለይም በአምቦ፣ በአለማያና በሌሎችም ዩኒቨርስቲዎች ለተፈጸሙ ግድያዎችና  በሌሎች  አካባቢዎች ለደረሱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂ የሆኑት ኮማንደር ፣ ታህሳስ 17 ቀን 2007 ዓም ሲያሽከረክሩት የነበረው መኪና ተገልብጦ ከ3 ጠባቂዎቻቸው ጋር በሂርናና አሰበ ተፈሪ መካከል በሚገኝ አንድ ገደላማ ቦታ ላይ ገብተው ህይወታቸው ወዲያውኑ አልፎአል።
ኮማንደሩ የተሳፈሩበት ዘመናዊ ላንድ ክሩዘር  ወደ ኢትዮጵያ ከገባ የአንድ ወር እድሜ ብቻ የነበረው መሆኑን የሚናገሩት ምንጮች፣ አደጋው ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ይሁን አይሁን ለማወቅ እንዳልቻሉ ገልጸዋል። ኢህአዴግ በኦሮምያ ክልል ውስጥ አለኝ ብሎ የሚያስበው ቁልፍ የደህንነት ሰው እንደነበር የሚናገሩት ምንጮች፣ ግለሰቡ በቀጥታ ከህወሃት ባለስልጣናት ጋር እየተገናኘ የደህንነት ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ በክልሉ ሲቪል ባለስልጣኖች ዘንድ እንዲፈራ አድርጎታል።
ኮማንደሩ ከቁልቢ ገብርኤል በአል ጋር በተያያዘ የጸጥታውን ሁኔታ ለመቃኘት ወደ አካባቢው መንቀሳቀሱን ለማወቅ ተችሎአል። ኮማንደር ጌትነት በ1995 እና 96 በክልሉ ተሰማርተው ነበሩ አድማ በታኝ ፖሊሶችን ማሰልጠኑን፣ በሂደትም ባለው የፖለቲካ ታማኝነት የክልሉ አድማ በታኝ አዛዥ ሆነ ለመሾም መብቃቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
 Foto facebook

No comments:

Post a Comment

wanted officials