Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, December 15, 2014

ምርጫ ቦርድ የበጀት እጥረት እንዳጋጠመው ተሰማ

ምርጫ ቦርድ የበጀት እጥረት እንዳጋጠመው ተሰማ
• ለጋሾች ይሰጣሉ ተብሎ የነበረው 7.1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር አልተገኘም
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በቀጣይ ግንቦት 2007 ዓ.ም ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው 5ተኛው አገራዊ ምርጫ ማስፈጸሚያ የበጀት እጥረት እንዳጋጠመው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የአንድ ለጋሽ ድርጅት ተወካይ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጀት ከለጋሾች በተለይም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሪግራም (UNDP) ከመሳሰሉ ለጋሾች ከሚገኝ እርዳታ የሚመነጭ ቢሆንም ለ2007 ዓ.ም ምርጫ ለጋሾች ለምርጫ ቦርድ እርዳታ ባለመስጠታቸው ቦርዱ የበጀት እጥረት እንዳጋጠመው ለማወቅ ተችሏል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሪግራም (UNDP) የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ከተለያዩ ለጋሾች 7.1 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማሰባሰብ አቅዶ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ምንም አይነት ድጋፍ እንዳላገኘ ተወካዩ ገልጸዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በተለይ በምርጫ ወቅት በጀቱን ያሳውቅ የነበር ቢሆንም የዘንድሮውን አመት በጀት ይፋ እንዳላደረገ የተገለጸ ሲሆን ይህም ከለጋሽ አገራትና ድርጅቶች ይሰበሰባል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው ገንዘብ ባለመሰብሰቡ እንደሆነ ተገምቷል፡፡
የአውሮፓ ህብረትን ጨምሮ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የልማት ፕሪግራም (UNDP) ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገንዘብ የሚያሰባስብባቸው እና ከአሁን ቀደም ምርጫ የታዘቡ አካላት በዘንድሮው ምርጫ በታዛቢነት እንደማይቀርቡ መገለጹ ይታወሳል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials