Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 6, 2016

ከጋምቤላ ታፍነው የተወሰዱ ከ100 በላይ ህጻናት ያሉበት ስፍራ ተለይቶ ታውቋል ሲል የደቡብ ሱዳን መንግስት ረቡዕ አስታወቀ

ከጋምቤላ ታፍነው የተወሰዱ ከ100 በላይ ህጻናት ያሉበት ስፍራ ተለይቶ ታውቋል ሲል የደቡብ ሱዳን መንግስት ረቡዕ አስታወቀ
ኢሳት (ሚያዚያ 27 ፥ 2016)
በቅርቡ በጋምቤላ ክልል በተፈጸመው ጥቃት ወደ ጎረቤት ደቡብ ሱዳን ታፍነው የተወሰዱ ከ100 በላይ ህጻናት ያሉበት ስፍራ ተለይቶ መታወቁን የደቡብ ሱዳን መንግስት ረቡዕ አስታወቀ።
እነዚሁ ህጻናት ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው በታጠቁ ሃይሎች ቁጥጥር ስር መሆናቸው እንደተረጋገጠ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ቃል አቀባይ የሆኑት አቴኒ ወክ-አቴኒ ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
ከ100 የሚበልጡት ኢትዮጵያውያን ህጻናቱ ከደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ 300 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የሙርሌ ጎሳ ማህበረሰብ መኖሪያ አካባቢ መገኘታቸውን ቃል አቀባዩ ይፋ አድርጓል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከሁለት ሳምንት በፊት ተመሳሳይ መረጃን ሰጥቶ የነበረ ሲሆን፣ የደቡብ ሱዳን መንግስት ይፋ ያደረገው ስፍራ ተመሳሳይ ይሁን አይሁን የታወቀ ነገር የለም።
የደቡብ ሱዳን መንግስት ታፍነው የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን ያሉበት ቦታ መታወቁን ቢገልጽም ህጻናቱን እንዴት ማስለቀቅ እንደታሰበ የሰጠው ዝርዝር መረጃ የሌለ ሲሆን፣ በአካባቢው የሚኖሩ የጎሳ ተወካዮች የህጻናቱን ጉዳይ ለመንግስት እንዳስታወቁም ብሉምበርግ ዘግቧል።
ባለፈው ሳምንት ታፍነው ከተወሰዱት ህጻናት መካከል 32 የሚሆኑት ተጥለው ተገኘተዋል ሲሉ የደቡብ ሱዳን የክልሉ ባለስልጣንት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ይሁንና፣ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተገኝተዋል ስለተባሉት ህጻናት ምንም አይነት መረጃ እንደሌላቸው ምላሽን የሰጡ ሲሆን፣ ያሉበት ስፍራ ታውቋል የተባለው ህጻናት በምን መልኩ እንደሚለቀቁ የታወቀ ነገር የለም።
የመንግስት ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ደቡብ ሱዳን ዘልቀው መግባታቸውን እና ልጆቹን የመታደግ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንደሆነ አስታውቀዋል።
መንግስት ከ100 የሚበልጡትን ህጻናትን ለማስለቀቅ የሃይል እርምጃን ይውሰድ አልያም ድርድርን ይከተል ቃል አቀባዩ የሰጡት ዝርዝር መረጃ የለም።
ከሁለት ሳምንት በፊት በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ከ200 የሚበልጡ ኢትዮጵያን ተገድለው ከ20ሺ የሚበልጡት ደግሞ ከቀያቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ መንግስት በጥቃቱ የደቡብ ሱዳን መንግስትም ሆነ የታጣቂ ሃይሎች እጃቸው የለበትም ሲል ቢያስተባብልም የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ አመራሮች በጥቃቱ ዙሪያ ውዝግብ ውስጥ መሆናቸውም ተገልጿል።
በጋምቤላው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ነዋሪዎችም ወደ ጎረቤት ደቡብ ሱዳን ተሰደው ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ማህበር ከቀናት በፊት ይፋ ማድረጉም ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials