Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, May 30, 2016

ባለፈው 15 ቀናት ብቻ 2 ሴቶችና 5 ወንዶች የግንቦት 7 እና ኦነግ አባል ናችሁ ተብለው በአ.አ ኤርፖርት ታስረዋል

የጆሐንስበርግ ዲያስፖራ በሽብርተኛነት ተወንጅሎ ተያዘ
 ከልዑል ዓለሜ
ዛሬ ኮሽታዎች ሁሉ ያስበረግጡታል! ከምንም በላይ በሰፊዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያደረሰዉ ወንጀል ነግ በምን አይነት መልኩ እንደሚከፈለዉ ሲገምት ሰላም ይነሳዋል፤ ከንፈር ያልነከሰበት ልቡ ያላቄመበት በእርሱ በግፍ ያልተነካካ ባለመኖሩ ሁሉንም እየነከሰ በማቁሰል ዉድቀቱን እያፋጠነ ይገኛል::
አዎ እራሱን ህወሃት እያለ የሚጠራዉ የክፉዎች ስብስብ የሆነዉ የህዝብ ጠላት ወያኔ የሚመራዉ የብሔራዊ መረጃ ከኢትዮጵያ ዉጭ ወደ ሐገር ቤት የሚገቡ ኢትዮጵያዊያንን በማንገላታት በማሰርና በማፈን በእጅጉ ተጠምዷል፡ በመሆኑም ከአሜሪካ፣ ከኖርዌይና፣ ከሲዉዲን እንዲሁም ከደቡብ አፍሪካ የሚገቡ ወገኖቻችን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ላይ በተቀመጠዉ የዚሁ የብሔራዊ መረጃ ቀኝ እጅ የሆነዉ እና በአንድ ብሔር ብቻ በተመሰረተዉ ኢሚግሬሽን ፖሊስ ቡድን ያለአግባብ እየተንገላቱ ይገኛሉ።

በዚህም የተነሳ በዚህ ባሳለፍነዉ 15 ቀናት ብቻ 2 ሴቶችና 5 ወንዶች የአርበኞች ግንቦት 7 እና የኦነግ አባል ናችሁ ተብለዉ ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ተጠልፈዉ በሽብር ወንጀል ተከሰዋል:: ከነዚህም መካከል ሙሉጌታ የተባለ ከየትኛዉም የፖለቲካ ድርጅት ጋር ግንኙነት የሌለዉ ነዋሪነቱ በደቡብ አፍሪካ የሆነና ጆሐንስበርግ ሞል በተባለ የንግድ መአከል ዉስጥ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ስራ ላይ የተሰማራ ግለሰብ በነዚሁ ወንጀለኛና የወያኔ ቡድኖች እጅ መዉደቁን ምንጮች ጠቁመዋል። 

ሙሌጌታ ከጆሓንስበርግ ኦሊቨር ታምቦ ኢንተርናሽናል ወደ አዲስ አበባ ከገባበት ወቅት አንስቶ የብሔራዊ መረጃ ቡድን አባላቶች ግለሰቡን ሲከታተሉት እንደነበረ ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን በተለይም በወያኔ ቀንደኛ ደጋፊዎች እና በትግራዩ ቡድን ኢንባሲ ደቡብ አፍሪካ አዲስ የተቋቋመዉ የዲያስፖራ ኢንጌጅመንት አሶሴሽን ደቡብ አፍሪካ ( Diaspora engagement association in south Africa ) የተባለ መሐበር ስለ ግለሰቡ ለወያኔ የብሔራዊ መረጃ የሰጠዉ የተሳሳተ ማንነት ምክንያት ግለሰቡ እንዲታፈንና በትናንትናዉ እለት የአርበኞች ግንቦት 7 አባል እንዲሁም ለደቡብ አፍሪካ አርበኞች የግንቦት 7 አባላቶች መልእክት ይዞ ሲሄድ ተያዘ በሚል የሐሰት ክስ በሽብር ወንጀል ተከሶ ዘብጥያ ተወርዉሯል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

No comments:

Post a Comment

wanted officials