በፌዴራል መንግስቱ አስተዳደር ስር ካሉት 2 ከተሞች መካከል አንዷ በሆነችው ድሬደዋ ዛሬ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ስር ዓቱን ሲቃወም; የታሰሩት የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና በህዝብ ጫንቃ ላይ የነገሰው ሥርዓት እንዲለቅ ሕዝቡ ጥያቄውን አቀረበ::
ስርዓቱ ፍሪዳ ጥሎ በውስኪ እየተራጨ የግንቦት 20ን በዓል እያከበረ ባለበት በዛሬው ዕለት በድሬደዋ ሕዝቡ የስርዓቱን በደል ለመግለጽ ጆንያ ተሸክሞ በአደባባይ ተቃውሞውን ሲያሰማ እንደነበር በፎቶ ግራፍ ጭምር የተሰራጩ መረጃዎች ጠቁመዋል::
እነዚህን ሰልፈኞች ለመበተን የስር ዓቱ ወታደሮች የተሰማሩ ሲሆን በርካታ ወጣቶች እና ሴቶች የአጋዚ ዱላ ሰለባ በመሆን መቁሰላቸው ተገልጿል::
“እኔም በቀለ ገርባ ነኝ” ; “ስንገደል ስንቆስል የዓለም ሕዝብ የታለ?” “በሃገራችን ሰላም አጣን; መኖሪያ አጣን” “እየሞትንም ቢሆን ተቃውሟችንን ማሰማታችንን አናቆምም” የሚሉት እነዚሁ ሰልፈኞች ለአጋዚ ወታደሮች ራስ ምታት ሆነውባቸው እንደዋሉ ከስፍራው የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ::
በሌላ በኩል በምስራቅ ሐረርጌ እንዲሁም በሃሮማያ ዩኒቨርሲቲ አሁንም ውጥረቱ እንዳለ ሲሆን አካባቢዎቹ በአጋዚ ሰራዊት መከበባቸውም ታውቋል::
No comments:
Post a Comment