ቋንቋችንን እንታዘበው (፩)፦ Independence, Freedom, Liberty (ነጻነት የቱ ነው? የቱስ አይደለም?)
"ነጻነት ውስብስብ ነው" ብዬ ልጀምር። ‘ነጻነት’ የሚለውን የአማርኛ ቃል በተለምዶ ከላይ የዘረዘርኳቸውን ሦስቱንም የእንግሊዝኛ ቃላት ለመተርጎም እንጠቀምበታለን። ትርጉሙ ግን ሁሌም አጥጋቢ አይሆንም።
ቃላት ባብዛኛው ደረቅ አይደሉም ፅንሰ-ሐሳብ (concept) ያዝላሉ። የሆነ ፅንሰ-ሐሳብን የሚወክሉ ቃላቶች በሆነ ቋንቋ ውስጥ የሉም ማለት የዚያ ፅንሰ-ሐሳብ በቋንቋው ተናጋሪው ማኅበረሰብ ዘንድ እምብዛም አይታወቅም እንደ ማለት ነው። ፅንሰ-ሐሳቡን በቃላት ቀንብቦ ማስቀመጥ መቻልና ብዙኃን በየ’ለት ንግራቸው እንዲጠቀሙበት ማድረግ መቻል ቃሉን ከነፅንሰ-ሐሳቡ በማኅበረሰቡ ውስጥ ማስረፅ ማለት ነው። ይህንን ለማስረዳት ቀላሉ መንገድ የአየር ሁኔታን መግለጽ ነው። በረዶ (Ice) እና snow (የበረዶ ብናኝ እንበለው) ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው፤ በአማርኛ ግን የሚጠሩት በአንድ ሥም - በረዶ - ተብለው ነው። Frost (snow ወይም የበረዶ ብናኝ የለበሰ ተራራ) አመዳይ ይባላል። በአገራችን የሌለ በመሆኑ ሥሙ የውሰት እና እምብዛም የማይታወቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ (መዝ 147: 16) ከመገኘቱ በቀር ቃሉም፣ ሐሳቡም በማኅበረሰቦቻችን ዘንድ የሌለ ነገር ነው። Tornado የሚለው ቃል የአማርኛ አቻ የለውም፤ ምክንያቱም በሐሳብ ደረጃም እምብዛም አይታወቅም። ሩቅ ምስራቃውያን በየጊዜው ለሚያጠቃቸው የነፋስ እና የማዕበል ዓይነት (ነፋስን ከነፋስ፣ ማዕበልን ከማዕበል) የሚለዩባቸው እልፍ ቃላት አሏቸው። የቃላት እና ሐሳብ ቁርኝት እንዲህ ይገለጻል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ‘ነጻነት’ የሚለው ቃል እና ፅንሰ-ሐሳብ በአማርኛ ተናጋሪው ዘንድ እንዴት ነው እየታየ ያለው? መነባንቡ (rhetoric) ብቻ ነው ወይስ ግንዛቤውም አብሮት አለ? አብረን እንፈትሽ።
ምሳሌ ፩፦
A) Ethiopia is an independent country.
B) Zone 9 is an independent blogosphere.
C) She is an independent woman.
A) Ethiopia is an independent country.
B) Zone 9 is an independent blogosphere.
C) She is an independent woman.
በሚሉት ሦስት ዓ/ነገሮች ውስጥ ‘independent’ የሚለው ቃል ሦስት ተለምዷዊ ትርጉሞች አሉት፣
ሀ) ኢትዮጵያ "ነጻ" አገር ናት።
ለ) ዞን ፱ “ነጻ” የጡመራ መድረክ ነው።
ቨ) እሷ “ነጻ” ሴት ናት።
ሀ) ኢትዮጵያ "ነጻ" አገር ናት።
ለ) ዞን ፱ “ነጻ” የጡመራ መድረክ ነው።
ቨ) እሷ “ነጻ” ሴት ናት።
ሦስቱ ቃላቶች በዐውድ (context) የተለያዩ ቢመስሉም በመሠረታቸው አንድ ናቸው። ሁሉም፣ “ማንም ላይ ጥገኛ ያልሆነ/ች” ወይም “ራሱ/ሷን የቻለ/ች” የሚለውን ሐሳብ ያዘሉ ናቸው። ነገርዬው በራስ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ወይም በሌሎች ጉዳይ ላይ አቋም ለመያዝ የማንም ተፅዕኖ የሌለበት እንደማለት ነው። መቶ በመቶ ራስን መቻል ወይም ከሌሎች ተፅዕኖ መላቀቅ የሚባል ነገር አለ ብዬ ባላምንም የሌሎችን በራስ ጉዳይ ጣልቃ ገብነት በእጅጉ መቀነስ መቻልን «ራስን መቻል» ብለን ብንጠራው አይከፋኝም። በላይኞቹ ምሳሌዎች ላይ ‘independence’ ራስን መቻል ወይም ገለልተኛ የሚሉት ቃላቶች ሊተኩት ይችላሉ።
ምሳሌ ፪፦
Eritrea became an independent country since 1991.
Eritrea became an independent country since 1991.
በተለምዶ ሲተረጎም፣
ኤርትራ ከ1983 ጀምሮ ነጻ ወጥታለች (ነጻ አገር ሆናለች)።
ኤርትራ ከ1983 ጀምሮ ነጻ ወጥታለች (ነጻ አገር ሆናለች)።
ከላይ ያለው አተረጓጎም አስተዳደራዊ መገንጠልን (secession) እንደ ነጻነት መቁጠር ነው። ጎረቤቶቻችንን እየወሰድን ብንነጋገር እንኳ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ እንደ «ራሱን የቻለ» አገር የደረሱበት ደረጃ ከነጻነት በስተቀር በሌላ ሥም ሊጠራ ይችላል። ነጻ ወጥቷል የሚለው ቃል independent የሚለውን ቃል አይገልጸውም ማለት ነው። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ ‘ኢንዲፔንደንት’ ሆና ቆይታ ሊሆን ይችላል። ይህንን ግን ‘ነጻ’ ቆይታ ነበር ብሎ መተርጎም አሳሳች ይሆናል፤ የነጻነት ትርጉም የተዛባ እንዲሆን ያደርግብናል።
ነጻነት (freedom) ~ “ ያለምንም ክልከላ ወይም ዕቀባ የሚፈልጉትን የማድረግ፣ የመናገር ሥልጣን ወይም መብት ነው።” Independence (“ራስን—መቻል”) ግን ለነጻነት ቅድመ ሁኔታ እንጂ ነጻነት ራሱ አይደለም። ኤርትራውያን የሪፈረንደሙ ጊዜ ‘ነጻነት’ ወይስ ‘ባርነት’ የሚል ምርጫ ነበር የተሰጣቸው። ትክክለኛው ምርጫ ‘መገንጠል’ ወይስ ‘አለመገንጠል’ ብቻ ነበር ~ ራሱን የቻለ የራስ ገዝ አስተዳደር መፍጠር ወይም አለመፍጠር።
በአማርኛችን በጣም የተበደለው እና በባሕላችን እምብዛም የማይታወቀው፣ ቢታወቅም በወግ አጥባቂነታችን ተቀባይነት የማያገኝ የሚመስለኝ ቃል ደግሞ liberty ነው።
የጉግል ተርጓሚ ሦስቱን ቃላቶች እንዲህ ይፈታቸዋል፦
Independence (ሦስት ተቀራራቢ ትርጉሞች አሉት) ~ the fact of being,
(1) free from outside control; not depending on another's authority. (ከውጭ አካል ቁጥጥር ነጻ መሆን፤ በሌሎች ትዕዛዝ ሥር አለመሆን፤ «ራስ-ገዝነት» እንበለው።)
(2) not depending on another for livelihood or subsistence. (ለኑሮ ሌሎች ላይ ጥገኛ አለመሆን፤ «ራስን-መቻል» እንበለው።)
(3) not connected with another or with each other; separate. (ከማንም ጋር ያልተነካካ፣ የተነጠለ፤ «ገለልተኝነት» እንበለው።) በዚህ መንገድ የቃላት አጠቃቀሙን ባበዛነው ቁጥር ፅንሰ-ሐሳቡን በውስጣችን የማስረፅ ዕድል ይኖረናል።
Independence (ሦስት ተቀራራቢ ትርጉሞች አሉት) ~ the fact of being,
(1) free from outside control; not depending on another's authority. (ከውጭ አካል ቁጥጥር ነጻ መሆን፤ በሌሎች ትዕዛዝ ሥር አለመሆን፤ «ራስ-ገዝነት» እንበለው።)
(2) not depending on another for livelihood or subsistence. (ለኑሮ ሌሎች ላይ ጥገኛ አለመሆን፤ «ራስን-መቻል» እንበለው።)
(3) not connected with another or with each other; separate. (ከማንም ጋር ያልተነካካ፣ የተነጠለ፤ «ገለልተኝነት» እንበለው።) በዚህ መንገድ የቃላት አጠቃቀሙን ባበዛነው ቁጥር ፅንሰ-ሐሳቡን በውስጣችን የማስረፅ ዕድል ይኖረናል።
Freedom ~ the power or right to act, speak, or think as one wants without hindrance or restraint. (ያለምንም ክልከላ ወይም ዕቀባ የሚፈልጉትን የማድረግ፣ የመናገር ሥልጣን ወይም መብት፤ «ነጻነት» እንበለው።)
Liberty ~ (1) the state of being free within society from oppressive restrictions imposed by authority on one's way of life, behavior, or political views. (በማኅበረሰቡ ውስጥ ሥልጣን ባለው አካል ተጭኖ በግለሰብ የኑሮ ዘዬ፣ ባሕሪ ወይም ፖለቲካዊ አመለካከት ላይ ተፅዕኖ ከሚያሳድሩዕቀባዎች ነጻ መሆን፤ «ግላዊ-ነጻነት» እንበለው።)
(2) the power or scope to act as one pleases. (የአንድ ሰው እንደፈለገው የመሆን ልክ፤ «ግለኝነት» እንበለው።)
(2) the power or scope to act as one pleases. (የአንድ ሰው እንደፈለገው የመሆን ልክ፤ «ግለኝነት» እንበለው።)
ሦስቱን የእንግሊዝኛ ቃላት በኦሮምኛ ከአማርኛ በተሻለ መረዳት ይቻል እንደሆነ ለማጣራት ሞክሬ ነበር። ነገር ግን ኦሮምኛችንም ልክ እንዳማርኛችን ነጻነትን የመረዳት ገደብ አለበት። ከነዚህ ትርጉም እጥረቶች የምንረዳው ነገር ቢኖር ብዙ ኢትዮጵያውያን ነጻነትን በቅጡ ተረድተነው የማናነበንበው መሆኑን ነው። እንዲሁ ሥሙ ደስ ስለሚል ብቻ ‘ነጻነት’-‘ነጻነት’ እንላለን።
No comments:
Post a Comment