Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 27, 2016

በሆላንድ ነዋሪ ለሆናችሁ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣

በሆላንድ ነዋሪ ለሆናችሁ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣

ለኢትዮጵያውያን የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣
የአገሪቱን ዜጎች በእኩልነት ተጠቃሚ ለሚያደርግና
የሕግ የበላይነት የሰፈነበት ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትን ለመፍጠር ለምትታገሉ ድርጅቶች አመራርና አባላት በሙሉ፤
በአገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት በስልጣን ላይ የተቀመጠው ወያኔ መራሹ የኢሕአዴግ መንግስት፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ቋንቋን መሰረት ባደረገ የይስሙላ ፌደሬሽን ከፋፍሎ፤ በመንግስት ስም በመላው የአገሪቱ ሕዝብ ላይ እጅግ አሰቃቂና ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ረገጣ የፈፀመና በማድረስ ላይ መሆኑ የሚታወቅ ነው።
ይህ በደል ከራሱ አልፎ ፣ዜጎችዋን ለባዕዳን ጥቃት አሳልፎ በመስጠት፤ ትውልድ ይቅር የማይለው ግፍና በዚህ በ21ኛው ዘመን ሕዝባችን ለውርደትና ለባርነት አገሪቱን ለውድቀት፣ እየዳረገ ይገኛል።
ይህን ቅጥ የለሽና አስነዋሪ ድርግቲ የሰለጠነው ዓለም ባዕዳን ሳይቀሩ እያወገዙትና እየታዘቡት ነው። ለናሙናም ያህል ባለፈው ሳምንት ሜይ 18 ቀን 2016 በኔዘርላንድ 2 የቴሌቪዥን ስርጭት ላይ ኖቫ ዜምብላ በተሠኘው ፕሮግራም፣ በዝዋይ ሐይቅ አጠገብ Sher Ethiopia የተሰኘ የጽጌ ረዳ አበባ አምራች የግል ካምፓኒይ እየርፈፀመ ያለውን ነውርና ግፍ ለሕዝብ አጋልጧል። ብዙዎቻችሁ ይህን ስርጭት እንደተከታተላችሁ የተሰማችሁን ብስጭት በመልክትና በስልክ በመግለጽ ፤ እኛስ ከዚህ ሕዝብ አብራክ የተገኘንና የዚች አገር ተወላጆች ፣ምላሻችን ምን መሆን አለበት የሚል መጠይቅ ማቅረባችሁ ይታወሳል።
ስለሆነም ይህን መሠል ግፍና በደል እያየንና እየሰማን በዝምታ ለማለፍ የምንሞክር ከሆነ፤ ጥቃቱን ከሚያደርሱትና ተጠቃሚዎች ከሆኑት ጋር ከማበር በስተቀር፤ በምንም መንገድ በሌላ መልክ ሊታይ የሚችል አይሆንም።
ስለዚህ አጠቃላይ የአገራችንና የሕዝቡን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በመወያየት፤ በሂደት ልናደርጋቸው የሚገቡንን ተግባራት ላይ በጋራ ለመመካከርና ለማቀድ እንድንችል ዕሑድ ጁን 05 ቀን 2016 ዓ ም ከቀኑ 14፡00 ሠዓት ጀምሮ በአምስተርዳም በምናደርገው አጠቃላይ ስብሰባ ላይ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
ቀን 05 Juni 2016
ሰዓት 14:00
ቦታ Amsterdam
አድራሻ Anna Spenglerstraat 75, 1054 NH Amsterdam
ከማክበር ሰላምታ ጋር
የኢማሆ ሥራ አመራር ኮሚቴ

No comments:

Post a Comment

wanted officials