ካሜሮናዊቷ ግብ ጠባቂ ሜዳ ለመግባት እየተዘጋጀች ህይወቷ አለፈ
====================
ካሜሮናዊቷ ግብ ጠባቂ ቡድኗ ለሚያደርገው ጨዋታ ወደ ሜዳ ለመግባት ሰውነቷን በማሟሟቅ ላይ እያለች ወድቃ ህይወቷ ማለፉን የአገሪቱ እግር ኳስ ፌደሬሽን አስታወቀ፡፡
የ26 ዓመቷ ጄኒ ክሪስቴሌ ጆምናንግ በደቡባዊቷ ካሜሮን ባሳለፍነው እሁድ በሴቶች ሊግ እየተካፈለ ለሚገኘው ቡድኗ ለመሰለፍ ሰውነቷን በማሟሟቅ ላይ እንዳለች ድንገት በመውደቋ ወደ ሆስፒታል ብትወሰድም ሆስፒታል ከመድረሷ በፊት ህይወቷ ማለፏ ተነግሯል፡፡
ፌደሬሽኑ የመነሻ ሪፖርቶች ግብ ጠባቂዋ በልብ ህመም ማረፏን የሚገልጹ ቢሆንም ዋነኛውን የህክምና ሪፖርት እየተጠባበቀ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የግብ ጠባቂዋ ሞት በሮማኒያ የሚጫወተው ፓትሪክ ኢኬንግ በድንገት የመሞቱ ዜና ከተነገረ በቀናት ልዩነት ውስጥ መከሰቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል፡፡
ጆምናንግ ደረቷ አካባቢ ህመም እንደሚሰማት በመናገሯ ያውንዴ ወደሚገኝ ሆስፒታል መወሰዷን ነገር ግን ህክምና ከማግኘቷ በፊት እስትንፋሷ መቋረጡን ክለቧ አስታውቋል፡፡
ምንጭ ያውንዴ ኒውስ

No comments:
Post a Comment