Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 13, 2016

በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ የመን እየጎረፉ ነው ተባለ

በሺ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ የመን እየጎረፉ ነው ተባለ
ኢሳት (ግንቦት 2 ፥ 2008)
ባለፈው የፈረንጆች ወር ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጦርነት እልባት ወደ አላገኘበት የመን በስደት መግባታቸውን አንድ አለም አቀፍ ተቋም ገለጠ ።
በአፍሪካ ቀንድና የመን የስደተኞችን እንቅስቃሴ የሚከታተለው አህጉራዊ የስደተኞች ተቋም (ማይግሬሽን ሴክረታሪያት ) በመጋቢት ወር ብቻ አብዛኞቹ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ 10 ሺ 400 ስደተኞች ወደ የመን በመግባት የፖለቲካ ጥገኝነት ማቅረባቸውን አመልክቷል።
ከዚህ ከፍተኛ ቁጥር መካከልም ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ሶማሊያዊያን ሰደተኞች ወደ የመን እየገቡ መሆናቸውን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር የሚታተመው ኢሪን መጽሔት ባቀረበው ዘገባ አስፈሯል።
ከወራት በፊት በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከተሎ ከሀገሪቱ የሚሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን በስደተኛ ጉዳይ ዙሪያ የሚሰሩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው።
ባለፈው ወር ወደ የመን ከተሰደዱ ኢትዮጵያዊያን እና ሶማሊያውያን መካከልም 65 የሚሆኑት በጉዞ ላይ መሞታቸው ቢገለጽም የኢትዮጵያዊያኑን ቁጥር ግን በአግባቡ ለማወቅ አልተቻለም።
ወደ የመን የሚሰደዱ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገሪቱ ከደረሱ በኋላም በተለያዩ ታጣቂ አንጃዎች የተለያዩ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንደሚፈጸምባቸው የአለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም ድርጀት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ከሀገሪቱ የሚሰደዱ ወጣቶችን ለመግታት በድንበር ዙሪያ ቁጥጥርን ቢያደርግም የስደተኞች ፍልሰት ሊቆም አለመቻሉንም ለመረዳት ተችሏል።
ባለፈው የፈረንጆች አመት ብቻ ከ 70 ሺ የሚበልጡ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን መግባታቸውም ይታወሳል።


No comments:

Post a Comment

wanted officials