Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, May 19, 2016

በደቡብ ኮሪያ ሲኦል ኢንቾን አየር መንገድ ላይ አራት ኢትዮጵያዊያን በቁጥጥር ስር ዋሉ።


ሶሱቱ እያንዳንዳቸዉ የአዉሮፓ እና የኢትዮጵያ የጉዞ ሰነድ የተገኘባቸዉ ሲሆን ፈትህ የሚባለዉ ግለሰብ በተለየ መልኩ ለብቻዉ በህገ ወጥ የሰዉ ዝዉዉር ወንጀል ተከሷል!
በደቡብ ኮሪያ ሲኦል ኢንቾን አየር መንገድ ላይ አራት ኢቶጵያዊያንን በቁጥጥር ስር ዋሉ።ቡብ ኮሪያ አለም አቀፍ አየር መንገድ ላይ በሀገ ወጥ መንገድ ሲሸጋገሩ ሰኞ ግንቦት 01/2008 በኮሪያ የጸጥታ ሐይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉት ኢትዮጵያዊያኑ ጉዟቸዉ ወደ አሜሪካ እንደነበረ እና እያንዳንዳቸዉ ለአሻጋሪዉ 300.000 በብር መክፈላቸዉን እንዲሁም ኢኳዶር ላይ አብሯቸዉ የሚጓዘዉ አሻጋሪ መንገድ በመቀየር ወደ ደቡብ ኮሪያ እንዳመጣቸዉ ለምንም ወደዚያ እንደመጡ እንደማያዉቁ ለደቡብ ኮሪያ ኢሚግሬሽን ፖሊስ ተናግረዋል።
የወያኔን ስርአት በመጥላት ሐገራቸዉን ጥለዉ የሚሰደዱ ወገኖቻችን በመላዉ አለም ላይ እየተንገላቱ በሚገኙበት በዚህ ወቅት ላይ ደቡብ ኮሪያም ኢትዮጵያዊያንን አስራለች!
ሁኔታዉን ሲከታተሉ የነበሩ አንድ ግለሰብ ጉዳዩ እንዳሳሰባቸዉ በመጠቆም አያይዘዉ በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል አለማየህ የተባለዉ ወገናችን ወደ ሐገሩ ለመመለስ ፍቃደኛ በመሆን የመመለሻ ስምምነት የፈረመ ሲሆን ሌሎቹ አሻፈረን በማለታቸዉ ምክንያት ሶስቱም በደቡብ በኮሪያ ኢሚግሬሽን ፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲገኙ በህገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ወንጀል የተከሰሰዉ ግለሰብ ወዳልታወቀ እስር ቤት ተዛዉሯል።
በተያዙበት ወቅት ከፍተኛ ድብደባና ወከባ እንደተፈጽመባቸዉ የሚገልጹት መረጃዎች አጣምረዉ ከ10_15 አመት እስራት ሊያስቀጣ በሚችል ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እየተገለጸ ያሉትን ወገኖቻችንን በደቡብ ኮሪያና አካባቢዉ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተቻላችሁ ትብብር በማድረግ ከጎናቸዉ እንድትቆሙ ጥብቅ መልእክት አስተላልፈዋል።
ስደት ይብቃ ኑ ሐገራችንን ነጻ እናውጥ!!
( ጉድሽ ወያኔ )

No comments:

Post a Comment

wanted officials