Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, October 30, 2015

ፍርድ ቤቱ በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ


በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ከ2ኛ -5ኛ መዝገብ ለተከሰሱት አቶ አሸናፊ አካሉ (2ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ደናሁን ቤዛ (3ኛ ተከሳሽ)፣ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን (4ኛ ተከሳሽ) እና አቶ አንሙት የኔዋስ (5ኛ ተከሳሽ) በመከላከያ ምስክርነት ተጠቅሰው በነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛው ወንጀል ችሎት ለሶስት አካላት ትዕዛዝ እንዲሰጥ ተጠየቀ፡፡ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥቅምት 12/2008 ዓ.ም አቶ አንዳርጋቸው እሱ ጋር እንደሌሉ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛው ወንጀል ችሎት በላከው ደብዳቤ መግለፁ ይታወሳል፡፡
ከ6ኛ-9ኛ ያሉት ተከሳሾች ማረሚያ ቤቱ በፈጠረው ችግር የአቶ አንዳርጋቸውን ምስክርነት ለመስማት የፍርድ ሂደታቸው እየተጓተተባቸው በመሆኑ የአቶ አንዳርጋቸው ምስክርነት ቀርቶ ብይን እንዲሰጥላቸው ሲጠይቁ 4ኛ ተከሳሽ አቶ ምንዳዬ ጥላሁን ‹‹ከአንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተህ መመሪያ ተቀብለሃል ስለተባልኩ አቶ አንዳርጋቸው መጥቶ መመስከር አለበት›› ሲል አሁንም አቶ አንዳርጋቸው እንዲቀርቡለት ጥያቄውን አቅርቦ ነበር፡፡ ከአቶ ምንዳዬ ጥላሁን በተጨማሪ 3ኛ ተከሳሽ አቶ ደናሁን ቤዛም አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲመሰክሩለት በመፈለጉ፤ እና ፍርድ ቤቱም አቶ አንዳርጋቸው ይገኙበታል ተብሎ ለታሰበው ተቋም ትዕዛዝ ለመስጠት እንዲመቸው ተከሳሾቹ እንዲጠቁሙት በገለፀው መሰረት ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ ለሶስት ተቋማት ትዕዛዝ እንዲሰጥላቸው በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡
ሁለቱ ተከሳሾች ጥቅምት 15/2008 ዓ.ም ለፌደራል ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በፃፉት ደብዳቤ የፀረ ሽብር ግብረ ኃይል አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዙን በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንክ ኮርፖሬት መግለጫ መስጠቱን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ መስከረም ወር 2007 ዓ.ም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን መያዝ፣ የእድሜ ልክና የሞት ፍርደኛ መሆናቸውን በመግለፅ የኢትዮጵያ መንግስት ፍርዱን ተፈፃሚ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን አስታውሰዋል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ አቶ አንዳርጋቸው ዜግነታቸው እንግሊዛዊ የሆሉትን አቶ አንዳጋቸው ጉዳይ ላይ ክትትል እንደሚያደርግ በደብዳቤው አስታወስዋል፡፡
በመሆኑም ከእነዚህ ሶስት አካላት በላይ አንዳርጋቸው ፅጌ ስላሉበት ቦታ የሚያውቅ ስለሌለ ለሶስቱም አካላት አቶ አንዳርጋቸው የት እንዳሉ እንዲገልፁና አቶ አንዳርጋቸውም ምስክር እንዲሆኑላቸው ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡

Thursday, October 29, 2015

ሰበር ዜና – ፈቃድ የሌላቸው የኢ.ቢ.ኤስ ፕሮግራሞች በቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ተወሰነ፤ የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት ይጀመራል



  • በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ላይ የቀረቡ ማስረጃዎች የበለጠ ተጠናክረው አጀንዳው በልዩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲታይ ተወስኗልsynod tik2008 Edited
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ከማእከል የተሰጠ ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ(EBS) የቴሌቭዥን ጣቢያ፣ “ሃይማኖታዊ ትምህርት”የሚያስተላልፉ ፕሮግራሞች፣ የቤተ ክርስቲያንን ስም እንዳይጠቀሙ ወሰነ፡፡
ምልአተ ጉባኤው በዛሬ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ስድስተኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲኾን፤ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና ለኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቭዥን በደብዳቤ እንዲያውቁት ይደረግ ዘንድ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
ምልአተ ጉባኤው ከዚሁ ጋር በማያያዝ፤ በሊቃውንት ጉባኤ ሳይመረመሩ እና በማእከል ሳይፈቀዱ በግለሰቦች እየተዘጋጁ የቤተ ክርስቲያንን ስም ይዘው ስለሚወጡ የስብከት፣ የመዝሙር እና የመጻሕፍት ኅትመቶች እንዲኹም የአዳራሽ ጉባኤያት እና ስብሰባዎች ከተወያየ በኋላ ቀደም ሲል ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በማጽናት ተመሳሳይ ትእዛዝ መስጠቱ ታውቋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ “ስብከተ ወንጌል እና ሚዲያን በተመለከተ” በተራ ቁጥር ሦስት በያዘው አጀንዳ፤ ቤተ ክርስቲያን ማእከላዊነቱን ጠብቆ የራስዋን ድምፅ ለዓለም የምታሰማበት እና ስብከተ ወንጌልን የምታስፋፋበት የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት እንዲጀመርም ወስኗል፡፡
ምንጭ:

ፖሊስ መምህር ግርማ ወንድሙን በቁጥጥር ስር አዋለ

ዘገባው የፋና ብሮድካስቲንግ ነው።

ፖሊስ መምህር ግርማ ወንድሙን በቁጥጥር ስር አዋለ
አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ መምህር ግርማ ወንድሙን በቁጥጥር ስር አዋለ።
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምንጮች መምህር ግርማ ዛሬ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ተናግረዋል።
መምህር ግርማ በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በማስተማርና በማጥመቅ ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው።
ይሁን እንጂ መምህሩ በማጥመቅ እና በማስተማር በሃገር ውስጥም ይሁን በውጭ ሃገራት ቤተክርስቲያኒቱን ወክለው እንዳያገለግሉ እውቅና መነፈጋቸውን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነገጋረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ጠቅላይ ቤተክህነት አረጋግጧል።
የፋና ምንጮች መምህር ግርማ ከአገልግሎታቸው ጋር በተያያዘ በወንጀል ሳይጠረጠሩ እንዳልቀረ ነው የተናገሩት።
ጣቢያችን ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን እየተከታተለ ያቀርባል።
በጥላሁን ካሳ እና ብርሃኑ ወልደሰማያት
ምንጭ: http://www.fanabc.com/index.php/news/item/11255-ፖሊስ-መምህር-ግርማ-ወንድሙን-በቁጥጥር-ስር-አዋለ.html

"መታሰር፡ አይገባንም ነበር፡፡ " ከእስር የተለቀቁት የዞን 9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች



እናመሰግናለን

በድንገት ከያለንበት ተይዘን እንደታሰርነው አፈታታችንም ግራ የሚያጋባ ነበር፡፡ ተመሳሳይ ክሶች ቀርበውብን እያለ ግማሾቻችን ‹ክስ ተቋርጦላችኋል› ተብለን ተፈታን፣ ግማሾቻችን ደግሞ ‹ነፃ ናችሁ› (ከሳሽ በነፃነታችን ላይ ይግባኝ መጠየቁ እንዳለ ሁኖ) ተብለን ይሄው ወጥተናል፡፡ ቀሪ ክስ ይዘን በዋስ ወጥተን እየተከራከርንም ያለን አለን፡፡ በዚህ ሁሉ መሃል የሁላችንም ዕምነት ግን አንድም ቀን ሊያሳስረን የሚገባ ወንጀል አለመፈፃችን ማመናችን ነው፡፡ መፈታታችን ጥሩ ሁኖ፤ መታሰር በፍፁም የማይገባን ነበርን፡፡ መፃፋችን እና ሕግ እንዲከበር መጠየቃችን ሀገሪቱ አገራችን እንድትሻሻል እና ሁላችንም ዜጎች የተሻለ ህይወት አንዲኖራቸው ከመሻት ባለፈ ሌላ ነገር አልነበረውም/የለውም፡፡ ነገር ግን ይህን በማድረጋችን ተገርፈናል፣ ተዘልፈን-ተሰድበናል፣ ታስረናል ተሰደናልም፡፡ ይህ በፍጹም አይገባንም ነበር፡፡

የእኛ መታሰር ፖለቲካዊ ንቃት የፈጠረላቸው ሰዎች እንዳሉ ሲነግሩን ደስ ይለናል፡፡ በእኛ መታሰር ምክንያት ለመጠየቅና ለመፃፍ በጣም እንደሚፈሩ የሚነግሩን ሰዎች ስናገኝ ደግሞ እናዝናለን፡፡ የመታሰራችን ጉራማይሌ ስሜት እንደዚህ ነው፡፡ ሳይገባን በመታሰራችን የነቁ መኖራቸውን በማወቃችን የምነደሰተውን ያክል፤ ሳይገባን በመታሰራችን የተሰበሩና ከተዋስኦ መድረኩ የራቁ እንዳሉ ስናውቅ እጅግ እናዝናለን፡፡

መታሰር በደል ነው፡፡ ብዙ ነገር ያጎድላል፡፡ መታሰር መልካም ነው፡፡ ብዙ ነገር ያስተምራል፡፡ እኛ በመታሰራችን ሀገራችን የበለጠ እንድናውቃት ሁነናል፡፡ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ ነፃነት አሁንም ብዙ ዋጋ እንደሚያስከፍል ተረድተናል፡፡ ሕግን መከታ አድርገው የኖሩ ‹ስም የለሽ› ዜጎች ሕጉ ሲከዳቸውና እነሱ ላይ ‹በላ› ሲያመጣባቸው ታዝበናል፡፡ ከሁሉም በላይ ፍትህ የሌለባት ሀገር ለዜጎቿ የማትመችና አገር እንደሆነች አይተናል፡፡
በእስራችን ወቅት የተለያዩ በደሎች በተቋም ደረጃ ደርሰውብናል፡፡ ግን አገር ነውና ከይቅርታ የሚያልፍ አይደለም፡፡ ለበደላችሁን አካላት እናንተ ይቅርታ ባትጠይቁንም፤ እናንተ የፈለጋችሁትን ባለማድረጋችንና ሕግን መሰረት አድርገን በመኖራችን ስላስከፋናችሁ እባካችሁ ይቅር በሉን፡፡

በዚህ ሁሉ መሃል ግን እናንተ አላችሁ፡፡ ጓደኞቻችንም ናችሁ፤ ዘመቻ አድራጊዎችም ናችሁ፤ ቤተሰቦቻችንም ናችሁ፤ ጠያቂዎቻችንም ናችሁ፤ ጠበቆቻችንም ናችሁ፣ የመንፈስ አጋሮቻችንም ናችሁ ርቀት ሳይገድባች የጮሃችሁልን አለም አቀፍ የመብት ጠያቂዎችም ናችሁ … በመታሰራችን የተረዳነው አንዱ ትልቅ ነገር የናንተን መልካምነት፣ የናንተን አጋርነት እና የናንተን የማይሰለች ድካምና ፍቅር ነው፡፡ እናንተ ባትኖሩ ‹አጭሩ› የእስር ጊዜያችን ይረዝምብን ነበር፤ ‹ቀላሏ› እስር ትከብድብን ነበር፡፡ ምስጋና ለናንተ፤ እስራችን ‹አጭር› – ፈተናችን ‹ቀላል› እንዲሆን አድርጋችሁልናልና፡፡
እናንተ ወዳጆቻችን ለሁሉም ነገር – እልፍ ምስጋና

እናመሰግናለን!
የዞን9 ጦማርያን እና ጋዜጠኞች

Wednesday, October 28, 2015

Fighit in Tepi Ethiopia

ጥቅምት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ፣ "የአመጹ ወጣቶችን አጋልጡ" በሚል የመከላከያ ሰራዊት አባላት በግለሰቦች ቤት እየገቡ አዛውንቶችን፣ ወጣቶችንና ሴቶችን እየደበደቡ ሲያስሩ ከሰነበቱ በሁዋላ ትናንት ከምሽቱ ሶስት ሰአት ጀምሮ፣ ከጫካ በመጡ ወጣቶችና በመከላከያ ፖሊስ አባላት መካከል ለሰአታት የቆየ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። ኢሳት ከተለያዩ ነዋሪዎች ባደረገው ማጣራት ከቴፒ 7 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቆርጫ ህብረት ፍሬ ቀበሌ ማምሻውን ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል። አንድ የአይን እማኝ እንደተናገሩት ፣ ሰሞኑን እንደገና በብዛት የሰፈሩት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህብረት ፍሬ በሚባል ቀበሌ የሚገኙ ሴቶችን " ሽፍቶችን የምትቀልቡት እናንተ ናችሁ አውጡ" በማለት ሲደብድቧቸው ፣ መረጃ የደረሳቸው ወጣቶች ፈጥነው በመድረስ ባደረሱት ጥቃት 14 ወታደሮች መገደላቸውንና ከወጣቶች መካከልም 2ቱ መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት የወታደሮች አስከሬን ሌሊት ላይ በ4 መኪኖች ተጭነው ሲወሰዱ ፣ የወጣቶችን አስከሬን ግን ህዝቡ መቅበር እንዳልቻለ ገልጸዋል የወጣቶች አመራሮች ማምሻውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ 20 የልዩ ሃይል አባላትን መግደላቸውንና በእነሱ ወገን 2 ታጋዮች እንደተገደሉባቸው ገልጸዋል። የሞቱ የመንግስት ወታደሮች ሌሊት ሲጓጓዙ ማደራቸውን የሚገልጹት ወጣቶቹ፣ የተገደሉባቸውን ወታደሮች ስምም ይፋ አድርገዋል። አንደኛው ሟች ቀድሞ የፖሊስ አባል የነበረና በህዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል በመቃወም የወጣቶችን ትግል የተቀላቀለው ሳጅን አብርሃም ፈይሳ ሲሆን፣ ሌላው ሟች ደግሞ ዘሪሁን ባሳ የሚባል ነው። እኩለ ቀን ላይ በከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የሚገኙት የመንግስት ወታደሮች የሁለቱን ወጣቶች አስከሬን ከተማ ውስጥ መሬት ለመሬት ሲጎትቱት ታይተዋል። ኢሳት ሞቱ ስለተባሉት የመንግስት ወታደሮች ከመንግስት ወገን የሚሰጥ መረጃ ካለ ለማጣራት ቢሞክርም አልተሳካለትም። መንግስትም እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም። የወረዳውን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረግነው ሙከራም አልተሳካም። የአካባቢው ነዋሪዎች ምሽት ላይ ከባድ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበርና ተጨንቀው ማደራቸውን ገልጸዋል። አካባቢው በመከላከያ መወረሩንም ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎችም ከመንግስት ወታደሮች የሚደርሰውን ጥቃት በመሸሽ ወደ ጫካ መሄዳቸውን በአካባቢው ካሉ ምንጮቹ ለማረጋገጥ ችለናል። አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀ ነዋሪ ፣ "ቴፒ ከሞቃዲሾ በላይ ህዝብ የሚዋከብባት ከተማ ሆናለች" ብሎአል። በቅርቡ አንድ ወጣት በደረሰበት ድብደባ መሞቱን እንዲሁም ብዛት ያላቸው ወጣቶች በድብደባ ብዛት አካል ጉዳተኞች መሆናቸውን ገልጿል። ድብደባውን በመሸሽም ወጣቶቹ እየተሰደዱ ነው። የቴፒ ወጣቶች ቡድን ሰሞኑን ለኢሳት በላከው መግለጫ፣ መንግስት በህዝቡ ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት ካላቆመ ጠንካራ አጸፋ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቆ ነበር። ማስጠንቀቂያውን ተከትሎ እስከ ትናንት ድረስ በሄሊኮፐተር የታጀበ ወታደራዊ አሰሳ በጫካዎች አካባቢ ሲካሄድ ነበር። ወጣቶች ያሉበትን ቦታ ለማወቅ አለመቻሉ ፣ የመንግስት ወታደሮች ፊታቸውን በህዝቡ ላይ እንዲያዞሩ እንዳደረጋቸው የኢሳት ምንጮች ይገልጻሉ። ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ እንዳላቸው የሚገልጹት ወጣቶች ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ ለኢሳት በላኩት መግለጫ ጠቅሰዋል።

አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በጎንደር ከተማ 6 የፖሊስ አባላት ላይ ጥቃት ፈፀመ፡፡



ባለፈው አርብ ዕለት ጥቅምት 12 ቀን 2008 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጎንደር ከተማ ፖሊስ አባላት የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋይ የሆነውን አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክሩ አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በታጠቀው ኮልት ሽጉጥ ተኩስ ከፍቶ 6 ፖሊሶችን መትቶ መሬት ላይ አጋድሟቸዋል፡፡



ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ ከጎንደር ከተማ እምብርት ፒያሳ ጀምሮ እጁን ሊይዙ የተከታተሉትን ፖሊሶች ቀበሌ 6 ቂርቆስ አካባቢ እስኪደርስ “አትቅረቡኝ! ብትመለሱ ይሻላችኋል…” እያለ የለመናቸው ሲሆን ነገር ግን ፖሊሶቹ ከድርጊታቸው ሊታቀቡ ባለመቻላቸው ቆራጥ እና የማያዳግም እርምጃ ወስዷል፡፡

ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ በያዘው ኮልት ሽጉጥ አንዲት ጥይት ብቻ እስክትቀረው እጁን ሊይዙ ከተከታተሉት ፖሊሶች ስድስቱን እያለመ ከረፈረፋቸው በኋላ በመጨረሻዋ ጥይት ራሱን ገድሏል፡፡

እጁን ለጠላት አሳልፎ ላለመስጠት እሳት ጨልጦ የአርበኛ ሞት በሞተው ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ የኮልት ጥይት ሰለባ ከሆኑት 6 የፖሊስ አባላት ሦስቱ ወዲያውኑ ሲሞቱ ቀሪዎቹ ሦስቱ ደግሞ በጠና ቆስለው በሞትና በህይወት መካከል ሆነው ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡ ቆስለው በህክምና ላይ የሚገኙት ፖሊሶች የደረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ከሞት ሊተርፉ እደማይችሉ እየተገለፀ ነው፡፡
ጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመን በህይወት ለመያዝ ሳይሳካላቸው የቀሩት የጎንደር ከተማ ጥቂት የህወሓት ተላላኪ ፖሊሶችና ደህንነቶች እንዲሁም የመስተዳደሩ አገልጋይ ባለስልጣናት አስከሬኑን በቁጥጥር ስር በማዋል “አንሰጥም” ብለው የነበረ ሲሆን በመጨረሻም በአካባቢው ህዝብ ግፊት የጀግናው አርበኛ ታጋይ አምሳሉ ተሾመ አስከሬን ለቤተሰቡ ተሰጥቶ ስርዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል፡፡

በተመሳሳይም ሳጅን ወለላው ዋናይሁን የተባለው የመተማ ወረዳ ፖሊስ የአመራር አባል እንደዚሁ አንድ በወወንጀል የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል ሲሞክር ከነተከታዮቹ ተገድሏል፡፡

Source: (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ)

Ethiopia: Sisay Lemma beats Kenyan duo to Frankfurt title






FRANKFURT, October 25- Ethiopia’s Sisay Lemma won the Frankfurt marathon’s men’s race on Sunday, while local fans were given something to cheer about as Arne Gabius broke the German record in finishing fourth.


Having begun 2015 by running a new personal best in finishing fifth at the Dubai marathon in January, Lemma won the Vienna marathon in April and has now added the Frankfurt title in an official winning time of two hours, six minutes and 26 seconds.Kenyan pair Lani Rutto, at eight seconds back, and Alfers Lagat, at 22secs, claimed third and fourth respectively while Hamburg-born Gabius broke the 27-year-old German marathon record with a time of 2:08.33 over the 42 kilometres.

The 34-year-old shaved 14 seconds off the previous record set by Joerg Peter in Tokyo in February 1988.


“I’m just happy the record has fallen,” Gabius said, who ran the last 12 kilometres with stomach pain.“It was painful, but hey that’s competitive sports, you have to go to your limits.”

There was a clean sweep of Ethiopian athletes in the women’s race as Gulume Tollesa won in 2:23:12, beating Dinknesh Mekash on the finish line while Koren Jelela was third 40 seconds back.

5 ብሔር ተኮር ነፃ አውጪ ግምባሮች በጋራ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መሠረቱ



(ዘ-ሐበሻ) በኦስሎ ኖርዌይ ከኦክቶበር 22 እስከ ኦክቶበር 23, 2015 ዓ.ም በተደረገ የጋራ ጉባኤ 5 የኢትዮጵያ የብሄር ድርጅቶች በጋራ ለመታገል አዲስ ንቅናቄ መመስረታቸውን ለዘ-ሐበሻ በላኩት መግለጫ አስታወቁ::

ጥምረቱን የመሰረቱት የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የጋምቤላ ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግምባር; የኦሮሞ ነፃነት ግምባርና የሲዳማ ብሔራዊ ነፃነት ግምባር ሲሆኑ የኢትዮጵያ ያለውን ስርዓት በጋራ ጥለው የሁሉንም ብሄሮች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚያከብርና የአንድን ቡድን የበላይነት እንዲያበቃ የሚያደርግ ስርዓት ለመፍጠር እንደሚታገሉ በመስራች ጉባኤያቸው መጨረሻ ላይ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል::



ሃገሪቱን ወደ ተሻለ የፖለቲካ ሽግግር ቀርጸው ለመንቀሳቀስ የተሰማሙት እነዚሁ 5 ድርጅቶች የአዲሱ ጥምረታቸው መጠሪያ የሕዝቦች ጥምረት ለነፃነትና ለዴሞክራሲ (Peoples Alliance for Freedom and Democracy (PAFD) ተብሎ ተሰይሟል::

(በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተሰጠውን መግለጫውን ለማንብብ እዚህ ይጫኑ)

አርበኞች ግንቦት በቅርቡ ከአማራው ንቅናቋ; ከአፋር ንቅናቄና ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጋር በጋራ ለመታገል ጥምረት መፍጠሩ ይታወሳል:: ትናንት በኖርዌይ ጥምረታቸውን ያወጁት የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የጋምቤላ ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግምባር; የኦሮሞ ነፃነት ግምባርና የሲዳማ ብሔራዊ ነፃነት ግምባር ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ወደፊት ስለሚፈጥሩት የጋራ ጥምረት ወይም ግንኙነት ይኑራቸው አይኑራቸው የተገለጸ ነገር ባይኖርም በቅርቡ ወደ ሚኒሶታ የመጡት የንቅናቄው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ነአምን ዘለቀ “ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንዳለች እስካመኑ ድረስ ከሁሉም ጋር በጋራ ለመስራት እንችላለን::” ማለታቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

Thursday, October 22, 2015

ድፍን የአዲስ አበባን ህዝብን ያስለቀሰ የመኪና አደጋ – ልትወልድ ቀናት የቀሯት ወጣት ሕይወቷ ተቀጠፈ






በኢትዮጵያ እየወጡ መቅረት የተለመደ ሆኗል – በተለይ በመኪና አደጋ:: ከ ዕለት ወደ እለት በሃገሪቱ በሚደርሰው የመኪና አደጋዎች በርካቶች ሕይወታቸው እያለፈ ነው::

ከላይ በፎቶ ግራፍ የምትመለከቷቸው ሁለት ጥንዶች ዳንኤልና የወብዳር ይባላሉ።ከ8 ወር በፊት እጅግ ደማቅ በሆነ ሁኔታ የሰርግ ስነስርአታቸውን አክብረዋል።
ዮብዳር በአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኛ ነች ። በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪዋን በማታው የትምህርት ዘርፍ በመከታተል ላይ ነበረች ።
ወጣቷ ልጅ ወልዶ የመሳም ጽኑ ምኛት ነበራት ይህንንም ለማሳካት ጥቂት ቀናት ነበር የቀራት ሆንም ግን በትናንትናው እለት ቀትር ላይ ኦሎምፒያ ሸዋ ዳቦ አካባቢ በደረሰባት አሳቃቂ የመኪና አደጋ ህይወቷ አልፏል ።
የቀብር ስነስርአቷም በዛሬው እለት በቀጨኔ መድሀኒያለም ቤተክስቲያን 9 ሰአት ላይ ይፈጸማል።

በኢትዮጵያ እየደረሰ ያለው የመኪና አደጋ እጅግ አሰቃቂ ነው:: ሰው አምኖ ለመንዳትም ሆነ ለመሳፈር እየተቸገረ ያለበት ሁኔታ ብቻ ሳይሆን በመንገድ ላይ መሄድ የሚያስፈራበት ደረጃ ላይ ተደረሷል:: በቀጣይ የምትመለከቱት ፎቶ ግራፍ በቅርቡ አገልግሎት መስጠት የመጀመረው ባቡር መንገድ ላይ የገባውን አውቶቡስ ነው::



Abraham

ኤርትራዊው ወጣት እስራኤል ውስጥ “በሰህተት እና በግፍ “መገደሉ ታላቅ ቁጣ አስነሳ





ከታምሩ ገዳ

“ይህ አይነቱ አረመኔያዊ ግድያ ድብቅ እንጂ አዲስ ነገር አይደለም ።” የ ኤርትራ ማስታወቂያ ሚ/ር

ከዛሬ አራት አመት በፊት ከትውልድ አገሩ ኤርትራ ባሕር እና የብስ አቋርጦ ወደ “ተሰፋይቱ ምድር” እስራኤል ለተሻለ ኑሮ ሲል የተሰደደው የ29 አመቱ ሃብቶም ዘረሁን በቀጣሪዎቹ ዘንድ “ተግባቢ ፣ ለመሻሻል የሚጥር እና በጣም ተወዳጅ ወጣት ነበር ።” እንደ አሱሶትድ ፕሬስ ዘገባ ሃብቶም የሰራ ቪዛውን ካሳደሰ በሁዋላ እስራኤል ውስጥ ያጠራቀማው ገንዘቡን ይዞ በኤርትራ የሚገኙ ቤተሰቦቹን በቅርቡ ለመጠየቅ እቅድ ነበርው ።

ይሁንና ሰው ያስባል አግዚአብሔር ይፈጽማል እንዲሉ ባለፈው እሁድ ጥቅምት 18 2015 እኤእ አመሻሹ ላይ እስራኤል (ቤርሳባ ውስጥ) አንደ ፈለሰጤማዊ እስራኤል በአንድ አውቶቡስ ማቆሚያ አካባቢ አንድ የእስራኤል ወታደር መሳሪያውን ነጥቆ እና ተኩሶ ገደሎ ፣ 10 አቁሰሎ እራሱ (ገዳዩም) በጸጥታ ሃይሎች የተገደለበት ገጠምኝን /ግጭትን በአቅራቢያ የታዘበው ወጣቱ ሃብቶም ከግርግሩ ለማምለጥ ሲጣጣር የተመለከተው አንድ የእስራኤል የጥበቃ ሰራተኛ ሃብቶምን “ከአሸባሪዎች አንዱ ይሆናል “በማለት በጥይት ተኩሶ የዘርረዋል።ከደረሰበት ጉዳት ሳቢያ ሰውነቱ በደም የታጠበው ሃብቶም አስቸኳይ የህክምና እርዳታ ሊሰጠው ሲገባ (በትንሹ አንድ ፖሊስን ጨምሮ) በሰፍራው የነበሩ የተወሰኑ ሰዎች የጥላቻ ቃላት በመጠቀም ፣ በመተፋት እና ከአካባቢው የነበሩ ቁሳቁስ(ወንበር ሳይቀር) በማነስት የደበድቡታል። በጸታ ሃይሎች እና በሰላም ወዳዶች ጣልቃገብነት ከሰፈራው የተወሰድው ምስኪኑ ሃብቶም ሃኪም ቤት እንደደረሰም ብዙ ሳይቆይ እሰከ ወዲያኛው አሸልቧል።

ያ እሩቅ እላሚው እና የ 29 አመቱ ሃብቶም በድንገት መሞት የአስራኢል፣የኤርትራ እና የፍልስጤም ፖልቲከኞችን አናቁሯል ። የሰብእዊ መብት ተሟጋቾችንም በእጅጉ ኣሳዝኗል። የእስራኤል ጠ/ሚ/ር ቢኒያም ናቲናያሁ በደረሰው ደንገተኛ አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ለሟች ቤተሰቦች በላኩት መልክት የገለጹ ሲሆን “አገራችን እስራኤል በሕግ የበላይነት ታምናለች።” ያሉት ጠ/ሚ/ሩ ድርጊቱንም የፈጸሙ ወገኖች በአስቸኳይ ለፍርድ እንደሚቀርቡ ቃል ገብተዋል። የወንጀለኞቹ ማንንነትን ለማጣራት የቪዲዮ ምስል ምርመራ በመካሄድ ላይ ሲሆን እስከ እሁን ድረስ ግን አንድም ተጠረጣሪ አልተያዘም ተብሏል።

የፈልስጤም ራስ ገዝ ከፍተኛ ባለሰልጣን የሆኑት ሃና አሽራዊ “የእስራኤል ባለሰልጣናት ሕዝቡን ጥላቻ እና ወንጀል እየመገቡት ለእንደዚህ አይነቱ ድርጊት ደረሰዋል” በማለት ሃላፊነቱ የባለሰልጣናቱ መሆኑን ተናግረዋል።የኤርትራ ማሰታወቂያ ሚ/ር በበኩሉ ሰኞ ጥቅምት 19 /2015 አኤአ ባወጣው መግለጫው “ ይሂ ጭካኔ እና ዘግናኝነት የተሞላበት የግደያ ድርጊት በእስራኤል በሚገኙ 10ሺዎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ ከህዝብ እይታ ውጪ እለት ተእለት የሚፈጸምባቸው እርምጃ አንዱ አካል ነው።ኤርትራዊያን ዜጎች ካለፉት ጥቂት አመታት ወዲህ በሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች እየተወናበዱ ለፖሊቲካ ፍጆታ እና ለእስራኤል ርካሽ የጉልበት ሰራተኛነት ተዳርገዋል።” በማለት የተላቪቭ መንግስትን ኮንኗል።

የመብት ተሟጋቹ ሁማን ራይት ዎች አንዲሁ “ ሃብቶም ጥገኝነት ፈለጋ ወደ እስራኢል ተሰዶ በእስራኢል ደህነቶች እና በጋጠወጦች መገደሉ ተቀባይነት የለውም ።” ሲል ተቃውሞውን አሰምቷል ። አሚንስቲ ኢንተርናሽናልም “ሃብቶም የሞተው ቆዳው በመጥቆሩ ብቻ ነው፣ገዳዮቹም ባስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ ።” ብሏል ።በዛሬይቱ እስራኤል ወስጥ ከ 34ሺህ በላይ ኤርትራዊያን እንደሚኖሩ ዘገባዎች ይገልጻሉ ። በሰሞኑ የእስራኤሎች እና የፈልስጤሞች ግጭት ከ 44 በላይ ፈልስጤሞች ሲገደሉ ከ 9 በላይ እስራኤሎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል። ሁኔታው ያሰጋቸው የተመድ ዋና ጸሃፊ ባን ኪ ሙንም ውጥረቱን ለመዳኘት ወደ ሰፍራው ለማቅናት ተዘጋጅተዋል።

የተቃዋሚው አኦፈር ሻለህ ሊቀመንበር የሆኑት ያሽ አቲድ”ተጠርጣሪ ግልሰብ በጸጥታ ሃይል ተመቶ ከቆሰለ በሁዋላ አደገኛነቱ አናስተኛ መሆኑ እየታወቀ አንድን ግለሰብ(ሃብቶምን) ከወደቀበት እያቃሳተ ሳለ ለሞት እስኪያበቃው ድረስ በቡድን መደብደብ ፍጹም ተቀባይነት የለውም ፣ይህንንም ህግ ማንኛውም የእስራኤል ወታደር ጠንቅቆ ያውቀዋል።”ብለዋል።

መርቲዝ የተባለው ፓርቲ ዋና ጸሃፊት የሆኑት ዚሃቫ ጋለን “የመከላከያ ሚ/ሩ በቅርቡ ሲቪሎች ሁሉ የጦር መሳሪያ ይታጠቁ ማለታቸውእና የትምህርት ሚ/ሩ ደግሞ (እንደ ካው ቦይ) ሸጉጥ ታጥቀው ፎቶ መነሳታቸው ምን ያህል ከእውነታው እርቀን በ እብደት አለም ውስጥ እንዳለን ያመላክታል።”በማለት የወቅቱ ፖለቲከኞችን በጽኑ ኮንነዋል።የጺዮናዊነት ሕብርት የተሰኘው ቡድን የሚወክሉት ማክ ናችማን ሻይ በበኩላቸው “ይህ እረዳት የሌለው ፍጡር (ሃብቶም) ከመሬት ላይ ተንጋሎ ሳለ ደብደቦ መግደል ሰበዊነት አይደለም ፣የ አይሁዳዊያን ባሕሪም አይደለም ።” በማለት የአገሪቱ ዋናው አቃቢ ህጉ በግድያው ዙርያ ልዩ ማጣራት አንዲያካሁዱ በደብዳቤ ጠይቀዋል።እለታዊው የእስራኤል ጋዜጣ ዮዲት “ሃብቶም የተገደለው ያለ አንዳች ጥርጥር በቆዳው ቀለም ልዩነት ሳቢያ ነው። “ሲል አስነብቧል።

ደርጊቱን ፈጽመዋል ተብለው ከተጠረጠሩት መካከል አንዱ እንደሆነ አና “ዱዱ”በሚል ሰም አንዲጠራ የጠየቅው ግለሰብ ለእስራኤል ጦር ሃይል ራዲዮ በሰጠው እማኘነት “ግለሰቡ(ሃብቶም) አሸባሪ አለመሆኑን ባውቅ ኖሮ ጫፉን አልነካውም ነበር። አሁን ግን በእጃችን ህይወቱ ያለፈው ግለሰብ(ሃብቶም) ነጹህ ሰው መሆኑን ከተረዳሁ በሁዋላ እንቅልፍ መተኛት ተሰኖኛል” በማለት መጸጸቱን ተናግሯል።

ሃብቶምን ከወርበሎች ለመታደግ ጥረት አድርጎ እንደነበር የሚናገርው መርሰኮ የተባለ መንገደኛ በበኩሉ ለቻናል 10 ቴሊቪዥን በሰጠው አስተያየት “ቁም ነገሩ ግለሰቡ (ሃብቶም) አሸባሪ ይሁን አይሁን አይደለም ግለሰቡ መንቀሳቀስ አቅቶት ተኝቶ እየተዪ በሰሜታዊነት ተደብድቦ መሞቱን በአይኔ በመመልከቴ ውስጤ ተጎድቷል ፣እንቅልፍም እርቆኛል።” በማለት በሁኔታው የሰነልቦና መታወክ እንደገጠምው ገልጿል።

የሟች ሃብቶም አለቃ የሆኑት ሳጂ ማላቺ እንዲሁ በበኩላቸው ሃብቶም ወደ ደቡባዊ እስራኤል (ቤርሳባህ )የተጓዘው የሰራ ፈቃዱን ለማስደስ አንደ ነብር አወስተው “ ”ጭምት እና ሃላፊነቱን ዘወትር ለመወጣት የሚጥር ታታሪ ሰራተኛ ነበር። ሃብቶም በማያወቀው ሰፍራ እና ባለጠበቀው ሰአት ሀይወቱ እንደቀላል ነገር በማለፉ ልቤን ክፉኛ ነክቶታል ።”ሩቅ አልሞ በ ጽጥታ ሃሎች ተተኩሶበት እና በወርበላዎች ተደብደቦ በአጭሩ ለቀረው ሰራተኛቸው እና ወዳጃቸው ለነበረው ሃብቶም ያላቸውን ፍቅር እና ሃዘናቸውን ገልጸዋል።
ፈጣሪ ነፍሱን ይማረው !!!!።

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47553#sthash.7Nt2uh41.dpuf

Wednesday, October 21, 2015

While drought and famine menaces Ethiopia, journalists are not allowed outside the capital Addis Ababa to report


Climate Disaster Hammers Ethiopia
by Thomas C. Mountain
(Sri Lanka Guardian) This year the rains failed in southern Ethiopia and some 25% of a country of 90 million people are facing acute food shortages in the coming months. This climate disaster, brought on mainly by western industries damage to the environment, has left the Ethiopian government quietly begging the international community for a preliminary food aid package worth $500 million, desperately need to start feeding over 7 million people. In the real Ethiopia journalists are not allowed outside the capital Addis Ababa. If they try to sneak into the rest of the country they are shot and wounded, thrown into a dungeon and then convicted on terrorism charges.
In the real Ethiopia journalists are not allowed outside the capital Addis Ababa. If they try to sneak into the rest of the country they are shot and wounded, thrown into a dungeon and then convicted on terrorism charges.
Wait a minute. Didn’t the World Bank just anoint Ethiopia with the title of the world’s fastest growing economy and not just for 2015, but for 2016 and 2017 as well? Get this now, Ethiopia is the world’s fastest growing economy yet it needs half a billion dollar$ in emergency food aid to keep millions of its people from starving?
When you fight your way through all the smokescreens thrown up in self-defense by the international financial banksters you finally find that Ethiopia is expecting a total net export income of $3 billion this
year, depending much on the price of coffee, for the sacred brew and cut flowers make up most of Ethiopian export income.
$3 billion dollars a year is all that Ethiopia actually creates, and this to run a country of 90 million?
The bottom line is Ethiopia’s “wealth” is almost entirely in the form of foreign aid/investments, something that can disappear even faster than it arrived.
On top of all this Ethiopia has the largest best equipped army in Africa including advanced missile systems which it used to attack the Eritrean town of Dekamhare early this year.
Ethiopia has hundreds of thousands of troops on the Eritrean border including occupying Eritrean territory. Ethiopia also has tens of thousands of troops on the border with Somalia or in Somalia itself.
Ethiopia is fighting an insurgency in the south east, the Ogaden. Ethiopia carries out counterinsurgency activities in the west in Gambella, home to some 1 billion barrels of oil reserves. And of course, Ethiopia is fighting a large well-armed guerilla army in the regimes ethic homeland of Tigray based on the Eritrean border, an army now directed by the leadership council of the newly united major Ethiopian opposition groups such as Ginbot, the real winners of the 2005 “election”.
All of this funded by a total of some $3 billion actually generated by the country? In reality it takes another $13 billion a year to fund the Ethiopian “miracle”, with the tab having been picked up until recently mainly by the western banksters and governments.
With the appearance of China in a major way Ethiopia has been a subject for concern by the western warlords, with Barack Obama spending several hours reassuring Ethiopian P.M. Desalegne during a
first ever visit to the country by a sitting US President during Obama’s recent trip to Africa.
Ethiopia is the only country in the world to be allowed to expel both the Red Cross and Doctors Without Borders (MSF) from an entire region/nation, the Ogaden. And this during the worst climate disaster droughts in history. Even North Korea allows the Red Cross.
When you get past all the smoke and mirrors Ethiopia is the policeman on the beat in East Africa for the USA, part of Pax Americana’s policy of using local gendarmes to do its dirty work.
And now China is jumping into the mix with a major economic infusion, building a $3 billion railroad from Ethiopia’s capital Addis Ababa to its only port, Djibouti amongst many billion$ of capital projects in the country.
The capital of Ethiopia, Addis Ababa, is the most visible sign of this investment, taking on a boom town look, with Africa’s only urban electric train and double decker freeways running through the city. It’s only when you leave Addis Ababa and the freeway turns into a dirt road does the real Ethiopia come into play.
In the real Ethiopia journalists are not allowed outside the capital Addis Ababa. If they try to sneak into the rest of the country they are shot and wounded, thrown into a dungeon and then convicted on terrorism charges. I met one of the Swedish reporters I am referring to who have written a book about their ordeal and are on a speaking tour which includes the USA.
A good representation of what life is like for most Ethiopians can be found in the film “Lamb” making the rounds of the international film festivals. Living in a one room hut, no electricity, carrying drinking water on donkeys for long distances, few schools, fewer medical clinics and now at the mercy of climate disaster and famine.
Yet this is the fastest growing economy in the world for years to come according to the financial terrorists at the World Bank.
The bizarre side of all this is that as scenes of millions of starving Ethiopians once again blight the TV screens of the world, the banksters through the western media will keep telling us how fast the Ethiopian economy is growing, one of Africa’s success stories.
The problem is climate disaster doesn’t care about all the propaganda, it just goes about its deadly task of reaping what you sow, as in the western industrialists destruction of the environment and African people starving to death as a result.

Thomas C. Mountain is an independent journalist living and reporting from Eritrea since 2006. He can be reached via twitter @thomascmountain, on facebook at thomascmountain or thomascmountain at g mail dot com

Tuesday, October 20, 2015

አራቱ የዞን ዘጠኝ አባላት ከተከሰሱበት ወንጀል ነፃ ተባሉ


• በፍቃዱ ሀይሉ በወንጀለኛ ህጉ እንዲከላከል ተብሏል
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሰው አንድ አመት ከአምስት ወር በላይ ፍርድ ቤት ሲመላለሱ የቆዩት የዞን ዘጠኝ አባላት ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ተወስኗል፡፡ የልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ጥቅምት 5/2008 በዋለው ችሎት ከዞን ዘጠኝ አባላት መካከል 1ኛ ተከሳሽ ሶልያና ሽመልስ፣ 3ኛ ተከሳሽ ናትናኤል ፈለቀ፣ 5ኛ ተከሳሽ አጥናፍ ብርሃኔና 7ኛ ተከሳሽ አቤል ዋበላን መከላከል ሳያስፈልጋቸው ተከሰውበት ከነበረው የሽብር ወንጀል ነፃ በመሆናቸው ከእስር እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡
በሌላ በኩል 2ኛ ተከሳሽ በፍቃዱ ሀይሉ በብሎግ ወጥተው በማስረጃነት ከቀረቡበት የፅሁፍ ማስረጃዎች መካከል አመፅ ቀስቃሽ ናቸው በተባሉት ፅሁፎች ከሽብርተኛ ወንጀል ወጥቶ በወንጀለኛ መቅጫ ህግ 557/ሀ እንዲከላከል ተወስኗል፡፡ በፍቃዱ ሀይሉ በዋስ እንዲወጣ ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን የዋስትናውን ጉዳይ ለማየት ለጥቅምት 10/2008 ዓ.ም ተቀጥረሯል፡፡
የዞን ዘጠኝ አባላት ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ ለአንድ አመት ከአምስት ወር ያህል ብይን ሲጠባበቁ የቆዩ ሲሆን ለብይን 5 ጊዜ እንዲሁም በአጠቃላይ ለ38 ጊዜ ፍርድ ቤት ተመላልሰዋል፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባሉበት አርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት አሰመረቀ


ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባሉበት አርበኞች ግንቦት 7  ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት አሰመረቀ






አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለሁለተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት አስመረቀ፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 በሁለት ድርጅቶች ማለትም በኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር እና በግንቦት 7 ንቅናቄ ውህደት ጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም ከተመሰረተ በኋላ ከትናትና በፊት እሁድ ዕለት ጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓም ለሁለተኛ ጊዜ ብዛት ያላቸውን አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ወራት አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡
እነዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሁለተኛ ዙር ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች ለሦስት ተከታታይ ወራት የተሰጣቸውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊ እና ሌሎች ተያያዥ የሆኑ የመረጃና ደህንነት ትምህርቶችን በሚገባ ወስደው በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ ነው ሊመረቁ የቻሉት፡፡
እጅግ በጣም ደማቅ በሆነ ስነ-ስርዓት በተከናወነው የምረቃ በዓል ላይ ከተለያዩ ቦታዎች ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች የታደሙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር አርበኛ ታጋይ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የድርጅቱ የትምህርትና ስልጠና መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኝ ንግግር በማሰማት ለተመራቂ አርበኛ ታጋዮች መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከውህደቱ ኋላ የመጀመሪያውን ዙር ሰልጣኞች ያስመረቀው ግንቦት 2 ቀን 2007 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል፡፡



ምንጭ: የአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ

በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ መምህራን ማህበር የተዘጋጀ ጸረ-ተሃድሶ የሀይማኖት ጉባኤ በፖሊስ ታገደ ::


በኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ መምህራን ማህበር የተዘጋጀ ጸረ-ተሃድሶ የሀይማኖት ጉባኤ በፖሊስ አገደ ::
ዛሬ እሁድ በ7/2/2008 በአዲስ አበባ ታላቅ ስብሰባ የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ መምህራን ማህበር የተዘጋጀ የተሀድሶ እንቅስቃሴን ሰፊ መረጃ ለህዝብ ለማድረስ በተደረገው ጥረት ስብሰብውን ለመካፈል ሰው በግዜ ነበር ወደ ቦታው የደረሰው የህዝብ ብዛት የአዳራሽ ጥበት ቢያጋጥመውም በስብስብ ላይ የተዋሕዶ ካህናት መምህራን ዘማሪያን እና ምእመናን በቦታው ተገኝተው ስብሰባው ተጀምሮ ሳለ ይህን ጉባኤ ለመረበሽ ተመሳስለው የገቡ ማንነታቸው የማይታውቅ ጉባኤውን በጥብጠው ጉባኤውን ሊቋረጥ ችሏል: ብጥብጡን የሰማው ፓሊስ በቦታው ደርሶ መጥቶ ጉባኤውን ማስቆሙን ተሰምቷል::
በስፍራው የተገኙ የስብሰባው ተካፋዮች ይህን ጉባኤ በቀጣይ ከዚህ በበለጠ ለማድረግ የተሻለ መንገድ መከፈቱን በቦታው የነበሩ ለቤተክርስንያን ተቆርቆሪ የሆኑ ምዕመናን ቁጭታቸውን ገልፅዋል::ይሄን የተሀድሶ እንቅስቃሴ ምን ያህል ስር እንደሰደደና በቀጣይ ቤተክርስትያኒቱ ላይ ከፍተኛ ችግር መጋረጡን ሳይጠቁመ አላለፉሁም ሁሉም ለሀይማኖቱ ተቆርቆሪ የሆነ ሰዋች ነቅተው መጠበቅ እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል ።ይህንን መልእክት በአለም ላይ ያሉ የኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ላልሰማ በማሰማን ሁሉም ከተኩላዋች መጠበቅ አለበት ብለዋል

የአርበኞች ግንቦት 7 ሪከርድ የሰበረ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሚኒሶታ * ነአምን ዘለቀ አርበኞች ግንቦት 7 መንፈስ ነው አሉ


የአርበኞች ግንቦት 7 ሪከርድ የሰበረ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት በሚኒሶታ * ነአምን ዘለቀ አርበኞች ግንቦት 7 መንፈስ ነው አሉ (ሪፖርታዥ)


“የኤርትራ መንግስት ከራሷ ጋር የታረቀች ጠንካራ ኢትዮጵያ እንድትመሰረት ይፈልጋል”
“ሁሉንም ፖለቲካ ሃይሎች ያካተተ የሽግግር ሂደት ይኖራል”
“የወደብ ጥያቄን በተመለከተም ወደፊት በድርድር/በሰጥቶ መቀበል የሚፈታ ይሆናል እንጂ አሁን የትግሉ አጀንዳ መሆን የለበትም”
“የመረጃ ትንሽ የለውም… መረጃ አይናቅም”



(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ ትናንት ማምሻውን ለአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ የተደረገው ዝግጅት በታሪካዊነቱ እንደሚቀመጥ የሚኒሶታ ነዋሪዎች አስታወቁ:: በሚኒሶታ ታሪክ ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት በአንድ ቀን 78 ሺህ ዶላር በላይ ሲሰበሰብ የትናንቱ የመጀመሪያው ነበር::



ከ200 በላይ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በተሰባሰቡበት በዚሁ ታሪካዊ የአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ ነአምን ዘለቀ እና ወጣት ሚካኤል ከላስቬጋስ ነበሩ:: ይህ የገቢ ማሰባሰብ ዝግጅት የተከፈተው የንቅናቄው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ከአስመራ በቭዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት ነበር::



ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በመልዕክታቸው እየተደረገ ያለው ትግል አንድን አምባገነን ጥሎ ሌላ አምባገንን ለመተካት ሳይሆን የተሻለች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት እንደሆነ አስምረውበታል:: ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋርም በኢትዮጵያ አንድነት በመተማመን በመነጋገር ላይ መሆናቸውን እና ጥሩ ነገር እንደሚሰማም የገለጹት ፕሮፌሰሩ በቶሎ ትግሉ እንደሚጀመር አስታውቀዋል::

በዕለቱ በአዳራሹ በክብር እንግድነት የተገኙት የንቅናቄው የውጭ ጉዳይ ሃላፊ አቶ ነአምን ዘለቀ ባሰሙት ንግግር “አርበኞች ግንቦት 7 መንፈስ ነው” ብለዋል:: ይህን ሲያብራሩም “የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋናዩም ተመልካቹም ሕዝቡ ነው:: ንቅናቄው ዘረኝነትን በተንገሸገሸ – እኩልነት; ፍትህ እና ሰላም በተጠማው የኢትዮጵያ ተማሪ… ወጣት… ገበሬ.. ሴት… ወንድ ውስጥ ያለ ሕዝባዊ ትግል ነው:: ይህም ማለት በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ውስጥ ንቅናቄው አለ ማለት ነው:: ይህ መንፈስ ሥር እየሰደደ ሄዷል:: አሁን ባለው ዘረኛው ስርዓት ብዙዎች ተገድለዋል… በግፍ ታስረዋል በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተንገላተዋል:: እነዚህ ሁሉ ሚሊዮኖች በውስጣቸው የአርበኞች ግንቦት 7 መንፈስ አላቸው::”

አቶ ነአምን ንግግራቸውን ቀጥለው “የወያኔ ፋሽስታዊ አገዛዝ በግፍ ብዙዎችን ከመሬታቸው ፎቅ ካልሰራችሁ እየተባሉ እንዲገፉ አድርጓል:: ቦታቸው ተቸብችቧል:: እነዚህ ዜጎች መሥእረታዊ የዜግነት መብታቸውን ተነጥቀዋል:: በጋምቤላ በደቡብ እየተደረገ ያለው ይኸው ነው:: የዘር ማጥፋት እየደረሰባቸው ነው:: እነዚህ የወያኔ ሰለባ የሆኑ ወገኖቻቸን ዴሞክራሲን የሚናፍቁ ናቸው:: ብዙ ኢትዮጵያውያን ካለፍርድ በ እስር ይማቅቃሉ:: ፍርደ ገምድሉ ሥር ዓት በፍትህ ላይ ቀልደዋል:: በነዚህ ሚሊዮኖች ውስጥ ሁሉ የአርበኞች ግንቦት 7 መንፈስ አለ” ብለዋል::

“በኮንትሮባንድና በዘረፋ የተሰማሮ 90% የሕወሓት ጀነራሎች እና መኮንኖች ሃብታም በሆኑበት መከላከያ ሠራዊት ውስጥ… አርበኞች ግንቦት 7 አለ:: ሠራዊቱ በከንቱ የወያኔ ጣልቃ ገብነትና ወረራ ደማቸው ደመከልብ ለመሆን ችሏል:: ይህ ሠራዊት እኩልነትን የተጠማ ሠራዊት ነው::” በማለት አሁን ስላለው የሕወሓት/ኢሕ አዴግ ሠራዊት ስለሚደርስበት የዘር መድልዎ የጠቀሱት አቶ ነአምን የትግሉ መዳረሻ የት ነው? በሚለው ንግግራቸው አርበኞች ግንቦት 7 መዳረሻ ዴሞክራሲያዊ ሥር ዓት መገንባት እንደሆነ ገልጸዋል:: አሁን ያለው ሥርዓትም በኃይል የወጣ የመጨረሻው አምባገነን ሥርዓአት ይሆናል ብለዋል::

“ሁሉንም ፖለቲካ ሃይሎች ያካተተ የሽግግር ሂደት ይኖራል:: ከሁሉም ባለድርሻዎች ጋር ቁጭ ብለን የምንነጋገርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም” ያሉት አቶ ነአምን በ3ኛ ደረሻ ስለ ኤርትራ መንግስት አብራርተዋል::

“የኤርትራ መንግስት ከራሷ ጋር የታረቀች ጠንካራ ኢትዮጵያ እንድትመሰረት ይፈልጋል:: እንድትበታተን ይሰራል ብለን አናምንም:: ኢትዮጵያን የማዳከም ስልት ወይም ፖሊሲ ኤርትራ አላት ብለን አናምንም:: በጣም ጤናማ ስኬታማ ኢትዮጵያ እንድትኖር የኤርትራ መንግስት እንደሚፈልግ ነው የምናውቀው” በማለት የተናገሩት አቶ ነአምን አርበኞች ግንቦት 7 ከኤርትራ መንግስት ጋር ኢትዮጵያን በሚመለከት ስትራቴጂካዊ በሆኑ ጉዳዮች; በወደብ ጥያቄ ለመደራደር ምንም ዓይነት ስልጣን እንደሌለው እንዲሰመርበት እፈልጋለሁ ብለዋል::



“የወደብ ጥያቄን በተመለከተም ወደፊት በድርድር/በሰጥቶ መቀበል የሚፈታ ይሆናል እንጂ አሁን የትግሉ አጀንዳ መሆን የለበትም” ያሉት አቶ ነአምን በ4ኛ ደረጃ በውጭ ከሚገኘው ኢትዮጵያዊ ይህ የነፃነት ትግል ምን እንደሚጠብቅ አብራርተዋል:: በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ይህን ትግል በዲፕሎማሲው; በቁሳቁስ እና በገንዘብ ሊደግፍ እንደሚገባ ያስታወቁት የንቅናቄው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ “በውጭ ያለው ኃይል በየከተማው ያሉትን ሴናተሮችን እና ኮንገረሶችን ስለኢትዮጵያ መንግስት ጥፋቶች ሊነግሩ ይገባል:: በየከተማው ባሉ ሚዲያዎች እየወጡ በመጻፍና በመናገር የዲፖሎማሲው አካል በመሆን ትግሉን ማገዝ ይገባቸዋል:: የህክምና ሙያ ላይ የተሰማሩ ሰዎችም እንዲሁ በመድሃኒት አቅርቦት ላይ ብዙ ይጠበቅባቸዋል” ያሉት አቶ ነአምን አርበኞች ግንቦት 7 ጠላትን በተመለከተ ትልቅ የመረጃ ማሰባሰቢያ ኔትወርክ እንዳለው ጠቁመው ሁሉም ኢትዮጵያዊ መረጃዎችን ለድርጅቱ በተዘራጋው መዋቅር በኩል እንዲያስተላለፍ ጠይቀዋል:: “የመረጃ ትንሽ የለውም… መረጃ አይናቅም” ያሉት አቶ ነአምን በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ በስር ዓቱ ላይ እስካሁን እያሳየ ያለውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት እንዲቀጥል አበክረው ጠይቀዋል::

ከነመሪዎቹ አስመራ ለሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 መርጃ የተደረገው ጨረታ ላይ የግንባሩ ሴት ታጋዮች ምስል ቀርቦ 20 ዶላር ከተሸጠ በኋላ ወደ ጥያቄና መልስ ተገብቷል::

ፖስትሮድ የሚገኙ የኤርፖርት ታክሲ ሾፌሮች 10 ሺህ ዶላር አዋጥተው ሰጥተዋል::

በስፍራው “የፈራ ይመለስ” የሚል ቲሸርትና ህፃናትን ሳይቀር ያሳተፈ የገንዘብ ልገዛ ለግንባሩ ተደርጓል::

ከተሰብሳቢውም በአሁኑ ወቅት የሕወሓት/ኢህአዴግ መንግስት በሃይማኖቶች ውስጥ ጣልቃ በመግባት በተለይ ተሃድሶ የሚባል ነገር በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ በመፍጠር ሕዝቡን ለማለያየት አውቆ እየሠራ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 እንዴት እንደሚመለከተው; ሞላ አስገዶም የትህዴን ሠራዊቱን ይዞ ወደ ወያኔ ሲገባ ከግንባሩ በቂ ምላሽ አልተሰጠም የሚል; አቶ ነአምን በቭኦኤ ላይ ቀርበው ስለአሜሪካዊ ዜግነት እንዳላቸው ሲጠየቁ ለምን መመለስ እንዳልፈለጉና ተመሳሳይ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል::

አቶ ነአምን አሁንም የአሜሪካዊ ዜጋ ስለመሆናቸውና ስላለመሆናቸው መናገር እንደማይፈልጉ ገልጸዋል:: ይልቁንም በቅርብ ጊዜ የሕወሓት አስተዳደር “የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ስለሆኑ እንከሳቸዋለን” ማለቱን ጠቅሰው “ይምጣና ይሞክረን:: እንደውም ክስ ቢመሰርቱብን ጥሩ ነው:: በክሱ ሂደት ምን ዓይነት ወንጀሎችን እንደሰሩ እናሳያቸዋለን” ብለዋል:: አቶ ነአምን አክለውም የሰሞኑ የወያኔ ድንፋታ የአሜሪካንን ሕግ ካለማወቅ የመጣ መሆኑን አስምረውበታል::


“… የወያኔ መሪዎች በዘር ማጥፋት ወንጀል መዘፈቃቸውን የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት በየጊዜው የሚያወጣውን ማስረጃ ማየት ነው። ይሄን ረስተው በአሜሪካ ፍርድ ቤት የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪዎችን እንከሳለን የሚሉት ፍርድ ቤቱን እነሱ እንደሚቆጣጠሩት አለመሆኑን ካለማወቅ ነው ።ሌላው ቀርቶ ፕሬዝዳንቱ ፍርድ ቤት የማዘዝ ስልጣን እንደሌለው አያውቁም…እኛ እነሱ በሐውዜን ያደረጉትን ድራማ አንሰራም”

በሞላ አስገዶም ዙሪያ ለሕወሓት መንግስት በቂ የሆነ ምላሽ አልተሰጠበትም ለሚለው ጥያቄም “በቂ ምላሽ ስለሰጠንበት እኮ ነው ዛሬ ይህን ሁሉ አዳራሽ ሙሉ ሰው ያያችሁት” ሲሉ መልሰዋል::

የአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰብ በተለይም የአቶ ነአምን ዘለቀ ንግግርን ማንኛውም ጋዜጠኛ እንዳይቀርጽ መከልከሉ ተሰብሳቢውን አሳዝኗል:: በተለይ አርበኞች ግንቦት 7 ለመናገር ነፃነት እታገላለሁ የሚል ድርጅት በመሆኑ እንዲህ ያለው የጋዜጠኛ ክልከላ ገና ከጅምሩ እንዲህ ከሆነ የወደፊቱ ያሳስበናል የሚሉ አስተያየቶችም ተደምጠዋል:: በአጠቃላይ ግን አርበኞች ግንቦት 7 በሚኒሶታ የተሳካ ገቢ ማሰባሰብ ማድረጉን በሙሉ አፍ መመስከር ይቻላል::

source : zehabesha

Monday, October 19, 2015

የአብዱ ኪያር “አልተለያየንም” ዘፈን በመንግስት ሚድያዎች እንዳይተላለፍ ታገደ

(ዘ-ሐበሻ)
 ድምፃዊ አብዱ ኪያር “አልተለያየንም” በሚል በአዲሱ የ”ጥቁር አንበሳ” ሲዲው ላይ ያቀረበው ዘፈን በመንግስታዊ ሚዲያዎች ላይ እንዳይተላለፍ ዕግድ መተላለፉን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከአዲስ አበባ አስታወቁ:: “በካርታ ብንለያየም – ኢትዮጵያም ኤርትራም አንድ ናቸው”… “አዲሱ ማንነቴን መቀበል አቃተኝ”… “በወላይታ ሙዚቃ ይጨፈራል በአስመራ”… የሚሉ መል ዕክቶች ያሉት በአንድነት ዙሪያ የሚያጠነጥነው ይኸው የአብዱ ኪያር ዘፈን በኢትዮጵያ ሁሉም ከተሞች ባሉ ሙዚቃ ቤቶች; በምሽት ክለቦችና መዝናኛ ቦታዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተደመጠ እንደሚገኝ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል:: መንግስታዊ ሚድያዎች እንዳያሰሙት የተከለከለው ይኸው “አልተለያየንም” የሚለውን ዘፈኑን ዘ-ሐበሻ እዚህ ጋብዛችኋለች:: ያድምጡት:: ለወዳጅ ዘመድዎም ያካፍሉት::


የአብዱ ኪያር “አልተለያየንም” ዘፈን በመንግስት ሚድያዎች እንዳይተላለፍ ታገደ

ሰበር ዜና ብሔራዊ መረጃ የተባለዉ ወንጀለኛ ቡድን ቴድሮስ አድሐኖም የተባለዉን እና ሬድዋን ሁሴንን ከተመረዘ ዉሃ አዳንኳቸዉ እያለ ነዉ ።

በቅርቡ የሹም ሽር ሲያደረግ የነበረዉ ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ ፓርላማ ስብሰባ ላይ በተገኙ የህወሓት አባላት ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገባቸዉ። እንደ ብሔራዊ መረጃ የዉስጥ አካላት ከፍተኛ ሚስጥር ተደረጎ የተያዘዉ ይህዉ የግድያ ሙከራ ያነጣጠረዉ ቴድሮስ አድሐኖም ላይ እና ሬድዋን ሁሴን የተባለዉ የድርጅቱ አባልት ላይ መሆኑን ያመላከትዉ መረጃ እንደሚጠቁመዉ ( Clostridium botulinum ) LD-50 of a substance ክሎስትሪደም ቧዉትሊም የተባለና
ሌዲ_50 ገዳይ ንጥረ ነገር የተዋሃደበት አደገኛ መረዝ ( the botulin toxin that causes botulism ) በስብሰባ ወቅት ላይ በሚሰጥ የመጠጥ ዉሃ ዉስጥ ማግኘቱን አረጋግጧል።
በወቅቱ የባለስልጣናቱን ፕሮቶኮል እና የማስተናገድ ስራ ሲሰሩ የነበሩ አንድ ግለሰብ ባጋጣሚ ሊጠቱት በቻሉት የታሸገ ዉሃ ምክንያት ግለሰቡ ድንገተኛ የእንቅልፍ መወሰድና እራስን የመሳት ብሎም የልብ መዳከም ህመም ላይ በመዉደቃቸዉ ምክንያት። በተደረገ ህክምና ሊታወቅ የቻለዉን የተመረዘ ዉሃ በተመለከተ ምርመራዉ በድብቅ እንዲያዝ ጌታቸዉ አሰፋ የተባለዉ የብሄራዊ መረጃ ዋና ዳይሬክተር የወሰነ ሲሆን ጉዳዩ በህወሃት ባለስልጣን ተብዬዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የእርስ በእርስ አለመተማመን ይፈጥራል የሚል ስጋት እንዳለዉ መረጃችን ያመለክታል።
እርስ በእርሱ ዉስጥ ለዉስጥ እየተበላላ 25 አመታትን በግፍ ሲገዛን የቆየዉ ህወሃት ከወደ ማብቂያዉ ዉድቀቱን እያፋጠነዉ ይገኛል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ጉድሽ ወያኔ

የእድሜ ልክ ፍርደኛዋ እንዳትማር ተከለከለች




በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
በ2004 ዓ.ም በኦሮሞ ነፃአውጭ ግንባር (ኦነግ) አባልነት ተጠርጥራ ከታሰረች በኋላ የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደባት አሊማ አብዲ መሃመድ እንዳትማር መከልከሏን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የምትገኘው አሊማ (ቢፍቱ) አብዲ ባለፉት አራት አመታት በማረሚያ ቤት እየተማረች እንደነበርና አምስተኛ ክፍልም መድረሷ ተገልፆአል፡፡
ይሁንና በዚህ አመት እንዳትማር የተከለከለች ሲሆን የተከለከለችበትን ምክንያት ስትጠይቅም ‹‹አንቺ መማር አይገባሽም!›› እንደተባለች የነገረ ኢትዮጵያ ታማኝ ምንጮች ገልፀዋል፡፡ አሊማ አብዲ መሃመድ የ23 አመት ወጣት ስትሆን በመደበኛ ጊዜ እንዳትጠየቅ በመከልከሏ ክፍለ ሀገር በሚኖሩት የተወሰኑ የቤተሰብ አባላት ብቻ ከ6፡00 እስከ 6፡30 ለሰላሳ ደቂቃ ብቻ እንደምትጠየቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ከኢትዮጵያ ህዝብ ኢንተርኔት የሚጠቀመው 1.7 በመቶ ብቻ ነው ተባለ፡፡









ኤርትራ ዝቅተኛ የኢንተርኔት ተጠቃሚ በመሆን አለምን ትመራለች፡፡

በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነው ከአጠቃላዩ ህዝብ 1.7 በመቶ የሚሆነው ብቻ ነው መባሉን የአሜሪካው የቢዝነስ መጽሄት ፎርቹን ዘገበ፡፡


ኢንተርኔት ላይቭ ስታትስ የተባለው አለማቀፍ ተቋም ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ እጅግ ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅርቦት ካላቸው አስር የአለማችን አገራት መካከል ስምንቱ በአፍሪካ አህጉር እንደሚገኙና ኢትዮጵያም አንዷ እንደሆነች በጥናት ተረጋግጧል፡፡

በኢንተርኔት አገልግሎት አቅርቦት ዝቅተኛነት ከአለማችን ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዘው ኤርትራ መሆኗን የጠቆመው ዘገባው፣ ከአገሪቱ ህዝብ የአገልግሎት ተጠቃሚ የሆነው 0.91 በመቶ ብቻ መሆኑን ገልጧል፡፡

ከአውስትራሊያ በስተሰሜን የምትገኘው ቲሞር ሌሴቴ ደሴት በ1 በመቶ፣ ማይንማር በ1.16 በመቶ፣ ብሩንዲ በ1.39 በመቶ እንዲሁም ሴራሊዮን በ1.49 በመቶ በኢንተርኔት አቅርቦት ዝቅተኛነት እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል ተብሏል፡፡ ሶማሊያ በ1.51 በመቶ፣ ኒጀር በ1.61 በመቶ፣ ኢትዮጵያና ጊኒ በ1.7 በመቶ እንዲሁም ኮንጎ በ1.92 በመቶ እንደሚከተሉም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡

ምንጭ፤- አዲስ አድማስ

Facebook will tell you if the government is spying on YOU


FACEBOOK will now send you a notification if it suspects you have been targeted by a nation-state






Facebook will only display the notification when it 'strongly' your system is compromised

Facebook has launched a new type of notification which warns social network users if there account has been targeted by hackers working for a nation-state.

The new notification, which was announced earlier this week, is not an indication that Facebook itself has been hacked.

Instead it is triggered by malware on the users' computer or smartphone that is being used to try and access your Facebook account.

Facebook Chief Security Officer Alex Stamos announced the news on the hugely successful social network's blog.

"While we have always taken steps to secure accounts that we believe to have been compromised, we decided to show this additional warning if we have a strong suspicion that an attack could be government-sponsored," he wrote.

"We do this because these types of attacks tend to be more advanced and dangerous than others, and we strongly encourage affected people to take the actions necessary to secure all of their online accounts."


The new Facebook notification which signals a nation-state hack to your system

Facebook has said it cannot reveal how it attributes whether the attack is coming from a nation-state.

But it has confirmed it will only roll-out the new notification "where the evidence strongly supports our conclusion."

In a nutshell, if you see this Facebook notification you should take it very seriously.



Facebook has started to roll out its new anti-malware notification, the Chief Security Officer said

"We hope that these warnings will assist those people in need of protection," Mr Stamos adds.

"And we will continue to improve our ability to prevent and detect attacks of all kinds against people on Facebook."

Users who receive the warning should rebuild or replace any computer system which may be infected by the malware, Facebook recommends.

Source
http://www.express.co.uk/life-style/science-technology/613261/Facebook-GCHQ-UK-US-Government-Spy-Hack

Saturday, October 17, 2015

በትግራይ ሽሬ አንዲት እናት በአንድ ጊዜ 4 ልጆችን በሰላም ተገላገለች








(ዘ-ሐበሻ) በትግራይ ክልል በሽሬ እንደስላሴ ቀበሌ 05 ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ኢልሃም ብርሃኑ በሽር በአንድ ጊዜ የአራት ልጆች እናት ሆነች::

የአራት ልጆች እናት የሆነችው ወ/ሮ ኢልሃም በሽር ከባለቤቷ ከማል አብዱልዋስ ጋር የጋብቻ ስነስርዓቷን የፈጸመችው ሰኔ 3 ቀን 2005ዓ.ም ነበር፡፡ ይህች ወጣት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን የተገላገለችው እዚያው ሽሬ እንደስላሴ ውስጥ በሚገኘው ሱኁል ሆስፒታል መሆኑንም ታውቋል::

ለዘ-ሐበሻ እንደደረሰው መረጃ እናት ወ/ሮ ኢልሃም አራት ልጆችን በአንድ ጊዜ ከተገላገለች በኋላ “በ እርግዝና ወቅት ምንም የተለየ የሚሰማኝ ስሜት አልነበረም; በጥሩ ሁኔታ በሰላም ተገላግያለሁ” ብላለች:: አራቱን ልጆች ያዋለዱት ዶ/ር እዮብ ገላን “ወ/ሮ ኢልሃምም ሆነ ልጆቿ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛሉ” ብለዋል::



Thursday, October 15, 2015

Ethiopia: Three girls and a kidnapping

By Abebe Gellaw
Angelina Jolie is doing a “favor” by lending her name to raise awareness on abduction, or rather kidnapping of girls in countries like Ethiopia. She is leveraging her star power to promote Difret, despite the twisted saga behind its production.
 The feature film, which is hitting the silver screen across the U.S. later this month, is based on the riveting story of Aberash Bekele, who was abducted, beaten and raped at the tender age of 14. She escaped after she shot and killed her abductor with his own gun. But she faced the wrath of her community and an unjust legal system in Ethiopia, which silently endorsed the kidnapping and rape of girls for the purpose of forced marriage.
The kidnapping that has made one British and two American girls from Texas to ask and act is a rare phenomenon. The victim isn’t one of the usual suspects but a fierce freedom fighter, who is in the forefront of the struggle to free the people of Ethiopia from injustice and tyranny. Andargachew Tsigie, 60, is an Ethiopian-born British citizen who was brazenly kidnapped at Sana’a International Airport while transiting via Yemen and taken to Ethiopia.
Hilawit
A daughter rising 

When Andargachew was kidnapped on June 23, 2014, his daughter Helawit was just fifteen. That same day she was having a good time at a friend’s birthday party in North London.
What can one expect a 15-year old girl to do when her beloved father is kidnaped by a brutal regime? Maybe she would lock her bedroom doors and cry her eyes out day and night. She may even get detached from the rest of the world, get depressed and withdrawn. She could feel helpless and hopeless.

Let alone a teenage girl, most stoic adults can easily resign themselves to such a heartbreaking reality. It is natural to feel desperately hopeless in the darkest hours of life. But such a reaction does not concern the exceptionally talented and courageous Helawit.
Instead of suffering from despondency, Helawit is fighting back and shining hope in the darkest hours of her family and others. She has become her father’s most authentic and vocal advocate. She needs his release sooner rather than later. She is campaigning, writing petitions, knocking on doors and using the power of words and creativity. Helawit is now an award-winning human rights activist whose campaigns and activism may not end with the release of her father from the dungeons of injustice.
She has created a new play, Ask, which vividly depicts her father’s plight and asks the hard questions why the British government is not doing enough to secure the freedom of their citizen facing the death penalty. Made in collaboration with the Royal Court of Theatre, Ask raises the thorny issues surrounding the abduction of her beloved father.
In partnership with her friends, she has made Ask from an idea conceived in her head to a reality on the stage. Her relentless effort is not in vain. She has recently graduated as an up-and-coming activist by winning Liberty’s 2015 Human Rights Awards.
Ask features her friends and herself from Islington Community Theatre, where she has been an active member for a while. Helawit’s extraordinary courage and creative activism has been noticed. Helawit was recognized with the Christine Jackson Young Person Award at London’s Southbank Center last month. Shortlisted for the award were Cardiff Law School Innocence Project and Tami Mwale, the founder of Get Outta the Gang, a group that tackles gang violence in London.
“I wish the reason behind this award wasn’t my dad’s abduction,” she said in her acceptance speech.
She took the opportunity to thank all those who have helped her to stay strong. One of the names she mentioned was the rock of her family, her mother Yemi Hailemariam. Yemi has proven to be a formidable fighter in her own right. A petition she has started online with Helawit and her twin boys, Menabe and Yilak, 7, to demand PM David Cameron to press for her husband’s freedom has already gathered nearly 130,000 signature.
The girls from Dallas
A few weeks ago, I travelled to Dallas, Texas, for a meeting and a fundraiser. What attracted my attention the most was an amazing handmade painting (above). It was a portrait of none other than Andargachew Tsigie. It looks so real that Andargachew seems gazing at the crowd emitting vision beyond the dark horizon. That painting was auctioned and raised $36,000 to the pro-freedom movement Andargachew has ignited.
PastedGraphic-1
- See more at: http://www.zehabesha.com/ethiopia-three-girls-and-a-kidnapping-by-abebe-gellaw/#sthash.9oW1xXug.dpuf

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ተባለ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ተባለ
የ18 ዓመት እስር ተበይኖበት ከ4 አመታት በፊት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የወረደው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አያያዝ አሳሳቢ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
‹‹እስክንድር ነጋ መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ ምንም አይነት መጽሐፍ እንዳያነብ ተከልክሏል፡፡ ከባለቤቱ ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል እናትና ከአንድ የቅርብ ዘመዱ ውጭ ማንም እንዳይጠይቀው ታግዷል፡፡ እስክንድር ከአንድ ሰፊ ግቢ ውስጥ ከአምስት ሰዎች ጋር ብቻ ነው የታሰረው፡፡ ማንም ጋር አይገናኝም፡፡ መቀመጫ ወንበሩ ተወስዶበት የቆሻሻና ውሃ ማጠራቀሚያ የነበረ ባልዲን ባፉ ደፍቶ ጨርቅ ደልድሎ ነው ለመቀመጫነት የሚጠቀመው›› ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የእስክንድር ነጋ የቅርብ ሰው ለቀለም ቀንድ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 21 በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብኣዊ መብታቸው የመጠበቅ መብት እንዳላቸውና ከትዳር ጓደኞቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው፣ ከሀይማኖት አማካሪዎቻቸው፣ ከሀኪማቸው፣ ከህግ አማካሪዎቻቸው ጋር ለመገናኘትና እንዲጎበኟቸውም መብት እንዳላቸው ይደነግጋል፡፡
(የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ቅጽ 3 ቁጥር 12)

የአውሮፓ ሕብረት አባሎች ወደ 160 ሽህ ስደተኞችን በአባል ሀገሮች ለማስፈር ተስማሙ


የአውሮፓ ሕብረት አባሎች ወደ 160 ሽህ ስደተኞችን በአባል ሀገሮች ለማስፈር ተስማሙ



የአውሮፓ ሕብረት 28 አባሎች ወደ 160 ሽህ የሚጠጉ ስደተኞችን ወደ ሌሎች አባል ሀገሮች ለማስፈር ተስማሙ። በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ከግሪክና ጣሊያን የስደተኞችና የፍልሰተኞች ማቆያ ስፍራዎች፤ ወደ ሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች የሚሰፍሩት፤ ጉዳያቸው ተቀባይነት ያገኘ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ስደተኞች ይሆናሉ።

ሜዲትራንያን ባህር ዳርቻ የሚገኙ የአውሮፓ ሀገሮች፤ በተለይ ጣሊያንና ግሪክ፤ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በርካታ ሰዎች የሚፈናቀሉበትና የሚፈልሱበት ዓለም አቀፍ ቀውስ ቀዳሚ ተቀባይ ሀገሮች ሆነዋል።

ከነዚህ የባህር ዳርቻ ሀገሮች የፍልሰተኞችና ስደተኞች ወደ ሌሎች ሐገሮች እንዲሰፍሩ፤ የአውሮፓ ህብረት አባላ ሀገሮችም ጉዳዩን በጋራ ሃላፊነት እንዲወጡት ተግባራዊ ጥረት ተጀምሯል። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) የደቡብ አውሮፓ ቃል አቀባይ ካርላታ ሳሚ (Carlotta Sami) ስደተኞችና ፍልሰተኞችን የማስፉር እቅድ በቅርብ ወራት ስምምነት ያገኘ እንደሆነ ገልጸዋል።

“በርካታ አባል ሀገሮች የተወሰኑ ስደተኞችን ተቀብለው ለማስፈር ተስማምተዋል። ሰፈራው የሜዲትራንያን ባህርን አቋርጠው ወደ ጣሊያንና ግሪክ የሚገቡትን ስደተኞች ይመለከታል” ካርላታ ሳሚ ብለዋል።
የተወሰነው160 ሽህ ስደተኞችን ለማስፈር ነው። ሆኖም ቁጥሩ አባይን በጭልፋ አይነት፤ ችግሩን የማይቀርፍ ነው።
የደቡብ አውሮፓ ቃል አቀባይ ካርላታ ሳሚ

ግሪካና ጣሊያን እንዲሁም ሌሎች የስደተኞችና ፍልሰተኞች ቀዳሚ መዳረሻ የአውሮፓ ሀገሮች፤ የህብረቱ አባላት እንዲያግዟቸው ጥሪ ሲያሳልፉ ቆይተዋል። ሆኖም የተቀናጀ የስደተኞችና ፍልሰተኞች አቀባበል ስልት እንዲሁም ስምምነት ስላልነበረ፤ አፈጻጸሙ ተጓቶ ሰንብቷል።

ባለፈው ሚያዝያ ወር የአውሮፓ ህብረት ሀገሮች አስቸኳይ ጉባዔ ጠርተው የስደትና ፍልሰትን ጉዳይ በ28ቱ አባል ሀገሮች መሪዎች ውይይት ተደርጎበት ባለ 10 ነጥብ የስምምነት ሰንድ ቀርቦ ነበር።

ከነዚህም መካከል አንዱ በባህር ላይ ፈልጎ የማዳን አቅምን ማጠናከር ሲሆን፣ ትሪተን (Triton) እና ፖሲዶን (Poseidon) ለሚባሉት በሜዲትራንያን ባህር ሰዎችን ፈልጎ የማዳን መርሃ ግብሮች፤ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት በጀታቸው በእጥፍ እንዲያድግ ተወስኗል።

ሌላኛው ጉዳይ የህገወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችን ንብረቶች፤ በተለይ ጀልባዎችን በመቀማት፤ ከጥቅም ውጭ እንዲሁኑ ማድረግ የሚል ነው። የብርታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካምሮን፤ በጉባዔው በር ላይ ባደረጉት ንግግር የዛሬው ስብሰባ አትኩሮት ህይወት ማዳን ሊሆን ይገባዋል ካሉ በኋላ ያደረጉት ንግግር ቀጥተኛ ነበር።
ህይወት ማዳን ማለት እነዚህን ችግረኞች መታደግ ነው። ከዚያም በተጨማሪ ወሮበላ አዘዋዋሪዎችን መደቆስና የአካባቢው ሃገሮች እንዲረጋጉ ማድረግ ነው።
የብርታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካምሮን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካምሮን በወቅቱ ኤች ኤም ኤስ ቡልዋርክ (HMS Bulwark) የተባለች የብርታንያ የጦር መርከብን በሜዲትራንያን ባህር እንደሚያሰማሩ ተናግረው ነበር። ሁለት ሄሊኮፐሮች፡ 67 መኪኖች፣ ሶስት አውቶማቲክ ማሳሪያዎችና ከ400 በላይ ወታደሮች የመጫን አቅም አላት ኤች ኤም ኤስ ቡልዋርክ (HMS Bulwark)።

አርብለት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በብርታንያ የቀረበውን ረቂቅ ውሳኔ አጽድቋል። በዚህም መሰረት የአውሮፓ የባህር ሀይል የህገወጥ አዘዋዋሪ ጀልባዎችና መርከቦች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወስዱ ስልጣን ሰጥቷል። መርከቦችን በዓለም አቀፍ የውሃ ክሎች መያዝ፣ መፈተሽና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ማስወገድን ያካትታል።

ሆኖም በሊቢያ የባህር ክልል እንዲሁም የባህር ዳርቻዎች የሚገኙ ጀልባዎችን ለማውደም በብርታንያና በአውሮፓ ህብረት የቀረበውን ሃሳብ፤ የመንግስታቱ ድርጅት አላጸደቀውም።

የአውሮፓ ህብረት በዓለም አቀፍ የባህር ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ህገወጥ አዘዋዋሪ ጀልባዎችን የሚቆጣጠር የባህር ሃይል አሰማርቷል። የአውሮፓ ህብረት ባለፈው ሮብ “ዘመቻ ሶፍያ” የተባለ ሶስት የአፈጻጸም እቅድ ያለው ወታደራዊ ትብብር ለማድረግ ከሊብያ ጋር ተስማምቷል። አላማውም ህይወትን ማዳን፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርንና የወሮበሎችን ስራ ማስቆም ነው።

ከተሰነይ ኤርትራ ተሰዶ ወደ አውሮፓ የገባ መሆኑን የገለጸው የ20 ዓመት ወጣት በጣሊያን ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢዎች የተሰደደበትን ምክንያት ሲያስረዳ “የኤርትራ መንግስት በአሁኑ ወቅት ወጣቶችን በመጨቆን በውትድርና ስለሚያሰልፍ” ከሀገሩ ለመውጣት መወሰኑን ገልጿል።

ባለፈው 10 ወራት ብቻ፤ 3,092 ሰዎች ለህይወት አደገኛ በሆነው የጀልባ ጉዞ በሜዲትራንያን ባህር ላይ ሰምጠው ሞተዋል። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ደግሞ ወደ አውሮፓ ለመሻገር በቅተዋል። የሚበዙት በግሪክና ጣሊያን ሰፍረው እንደሚገኙ የዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ገልጿል። የአውሮፓ ህብረት የሰዎች ፈልጎ ማዳን መርሃ ግብርም ከ100ሽህ በላይ ሰዎችን ህይወት እንዳተረፈ ተመዝግቧል።

ባለፈው አርብ የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በስደተኞችና ፍልሰተኞች ጉዳይ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ላይ ቬኔዙዌላ ተአቅቦ ስታድርግ ሌሎቹ 14 አባላት በሙሉ ድምጽ አጽድቀውታል።

ሳሌም ሰለሞንና ሄኖክ ሰማእግዜር አቀናብረው ያዘጋጁትን ሙሉ ዝርዝር የተያያዘውን የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።
የአውሮፓ ሕብረት አባሎች ወደ 160 ሽህ ስደተኞችን በአባል ሀገሮች ለማስፈር ተስማሙ/ርዝመት – 6ደ54ሰ/

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47364#sthash.vIJosbiQ.dpuf

Wednesday, October 14, 2015

የወያኔ ስራ በቤተክርስትያናት ላይ!! Government interference on Ethiopian church


የወያኔ ስራ በቤተክርስትያናት ላይ!! በዘመናችን ያለ የቤተክርስቲያን ትልቁ ፈተና – ጉዞ ወደ እናት ቤተክርስቲያን (እንቀላቀል) ለምን ትልቅ ፈተና ሆነ ስንል?



ከጌታቸው ካሳሁን

የእስከዛሬዎቹ ጥቃቶች የሚፈፀሙት ከቤተክርስቲያን ውጪ በሆኑ ሰዎችና ተመሳስለው በገቡ ማንነታችውን በደበቁ ሰዎች ሲሆን ይህኛው ግን ለየት የሚያደርገው የሃይማኖት ሽፋን ያለው እንዲሁም እውቅና በሰጠናችውና በፈቀድንላቸው ጥፋታቸውን እራሳቸውን ሳይደብቁ በግልፅ እያሳዩን እንኳን ዝም ብለን የተቀበልናቸው የቤተክርስቲያን አማሳኞች አባቶችና ምዕመናን የሚከናወን በመሆኑ ነው።እንግዲህ ወደ ጉዳዩ ስንገባ በመጀመሪያ ቤተክርስቲያን አንዲት ናት ርትዕት ናት በዶግማ ምንም ችግር የለባትም ነገር ግን በአስተዳደር ችግር ምክንያት ለሶስት ቦታ ተከፍላለች ። ልብ በሉ በዶግማ አላልኩም በአስተዳደር ምክንያት ነው ያልኩት።

በአስተዳደር ለ3 ( ሶስት) ቦታ የተከፈሉትን እንደዚህ እናያቸዋለን
በኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሚተዳደሩ
በአሜሪካን ሀገር ባለው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሚተዳደሩ ሲሆኑ፡
ገለልተኛ ቤተክርስቲያን፡-የሚባሉት ደግሞ በአሁን ግዜ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ሁለት ፓትርያርክ ስለሆነ ያላት ለየትኛውም ፓትርያርክ አንወግንም የሚሉና ገለልተኝነታቸው ከሁለቱ አባቶች እንጂ ከቤተክርስትያኒቱ ያልሆነ እንዲሁም እርቀ ሰላም ወርዶ አንድ ሲኖዶስ በቦታው እስኪመለስ ድረስ ለየትኛውም አንወግንም የሚሉ ናቸው።

ነገር ግን በሶስቱም አስተዳደር ስር ያሉት ቤተክርስቲያኖች መተዳደሪያ ደንባቸው በቅዱስ ሲኖዶስ የተዘጋጀው ቃለ ዓዋዲ ሳይሆን ከቤተክርስትያኑ አባላት በተውጣጡ ጥቂት ሰዎች በሚቀርጹት መተዳደሪያ ደንብ ነው። ቤተክርስቲያንነታቸው የአንዲት (እናት) ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲሆን፤ አንዱ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ሌላው ደግሞ እንጀራ ልጅ ሊባሉም አይችሉም። እንዲሁም ምእመኖቻቸው የአንዲት እናት የኢ/ ኦ/ተ ቤተክርስቲያን ልጆች ናቸው። ጊዜ ያመጣው ፖለቲካ አስተዳደሩን ለሶስት ከፈለው እንጂ ሁሉም አሃዱ አብ ቅዱስ ብለው የሚቀድሱ እና የሚያመሰግኑ ልዩነት የሌላቸው በአንድ አምላክ የሚያምኑ ናቸው።

በዚህ ጊዜ በአንድነት ስም ቤተክርስቲያንን መክፈል ያስፈለገበት ምክንያት

ሀገሪቱን እያስተዳደረ ያለው መንግስት ከጫካ ጀምሮ አንግቦ በመጣው የኢ/ኦ/ተ ቤተክርስቲያንን የማፍረስ ዓላማ በተለያዩ ጊዜያት ቤተክርስቲያንን ሲያቃጥል፣ ሲያስፈርስ፣ ሲያርስ፣ ታሪኳን በጠራራ ፀሀይ ሲያጠፋ የሀይማኖት ቦታዋን እየነጠቀ ለሌላ ሲሰጥ ስለ ቤተክርስቲያን ብሎ አንድም የተናገረላት አባትም ሆነ የበላይ አካል ዝም ብሎ ከማየት ወጭ ያደርጉት አስተዋፆ የለም። በትንሹ ቢሆን በየአካባቢው ያሉ ምእመናን አትንኩ ቤተክርስቲያኔን ሲሉ በአፀፋው እስር፣ እንግልት፣ መገደል ደርሶባቸዋል። በእኛ ዝምታ መንግስት ተግባራዊ አድርጎታል ነገር ግን በተቻለው ፍጥነት የማፍረስ ሂደቱ እንዳይከናወን ሁለት ነገሮችን ይፈራል።
ማህበረ ቅዱሳንን፡- ማህበሩን ለምን ይፈራዋል ስንል የቤተክርስቲያን የጀርባ አጥንት ነው በሎ ስለሚያስብ ስለዚህ ማህበሩን ለማፍረስ በተለያየ ጊዜ ብዙ ሙከራ ቢያደርግም አልሳካ በማለቱና ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ የሚደረገውን እሩጫ ማህበሩ ባያቆመውም ወደ ኋላ ስለጎተተበት እንዲሁም ውጤቱ እንዲያዘግም ስላደረገና መዋቅሩም በጣም ጥልቅና እስከ ታች ድረስ ዘልቆ ስለገባ ማፍረስ ባለመቻሉ በዚህ ጉዞ ወደ እናት ቤተክርስቲያን በሚል ከተቻለ ለማፍረስ አለበልዚያም ለማዳከም ነው።

ይህ አቅጣጫ እንዴት ማህበሩን ያፈርሳል ?



ጉዞ ወደ እናት ቤተክርስቲያን በሚል እውነትነት ያለው በሚመስል የሃይማኖት ሽፋን ነገር ግን ህዝብን ከህዝብ፤ ባልን ከሚስት፤ በአጠቃላይ የምእመናንን ልብ ለሁለት ከፍሎ እስከመለያየት የሚያደርሰውን አጀንዳ የማህበረ ቅዱሳን አጀንዳ አድርጎ በምእመን ዘንድ ሰርጾ እንዲገባ በማድረግ ማህበሩ በምእመናን እንዲጠላ ማድረግና ከተቻለ በዚህ አጋጣሚ ማህበሩን አፍራሽ አድርጎ በይፋ በማውጣት ማፍረስ ወይም ከምእመናን ልብ ውስጥ ማውጣትና ማዳከም ነው። እዚህ ጋር ግን የሚያሳዝነው የማህበሩ አባል በሆኑ ነገር ግን የማህበሩ ዓላማ ባልሆነው ነገር እነርሱን ከፊት በማሳየት መጠቀምና ተአማኒነትን ለማግኘት በመሞከር የማህበሩን ተልእኮ እያስፈፀሙ አስመስሎ በማሳየት በእነርሱ መጠቀም ነው።
ብዙ ህዝብ የተሰበሰበበት በዘር በጎሳ ያልትከፋፈለና ስርዓተ ቤተክርስቲያንን የጠበቀ አገልግሎት የሚሰጥበትን ቤተክርስቲያንን ፦ እነዚህን ለምን ይፈራል ስንል አንድነትን አጥብቆ ስለሚፈራ ለስልጣኔ ያሰጋኛል ስለሚል። እንደዚህ ዓይነት ቤተክርስቲያኖች የሚገኙት ደግሞ በገለልተኛ ቤተክርስቲያን ስር ያሉት ጋር ነው። እነዚህ ቤተክርስቲያኖች አንድነታቸውን ጠብቀው ፍፁም ኢትዮጵያዊነት ስለሚታይባቸውና በቂ ባይሆንም ቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን አደጋ በመግለጫም ቢሆን በጥቂቱ ይቃወማሉ። እንዲሁም በሰው ኃይል፣ በፋይናንስ እና ከእዳ ነፃ የሆነ ቤተክርስቲያን ባለቤትና በአገልግሎትም ጠንካራ ስለሆኑ መንግስት በስጋት ያያቸዋል። ይህን ቤተክርስቲያንን የመክፈል (የማዳከም) ስራ ማን ይስራው

እንግዲህ በአሁን ግዜ በቤተክርስትያኒቱ ውስጥ ሁለት አይነት ሰዎች ዲያቆናት፣ካህናትና እንዲሁም ጳጳሳት ከታች እስከ ላይ በተዋረድ ከስር አጥቢያ ቤተክርስትያን አንስቶ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ድረስ አሉ። እነርሱም፦

1. የመጀመሪያዎቹ ፡- በመንግስት ተመልምለው ለዚህ ለቤተክርስቲያን የማፍረስና የማዳካም ስራ ስልጠና ወስደው ከድቁና እስከ ጵጵስና ደረጃ ተምረው ወይም የነበሩትን በዘር፣ በስልጣን፣ በጥቅማ ጥቅም ተደልለው ቤተ ክርስቲያኒቱን ከአጥቢያ ቤተክርስትያን እስከ ቤተክህነት እንዲሁም ጵጵስና ደረጃ የያዙት ሲሆኑ

2.ሁለተኞቹ፡- ደግሞ በታማኝነት፣ በፍፁም ፍቅር ፣በፍጹም እምነት በቤተክርስቲያኒቱ ያደጉና ለቤተክርስቲያኒቱ ዘብ የሚቆሙ ህመሟ ህመማቸው የሆነ ችግሯ ችግራቸው የሆኑ ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን እስከ ጵጵስና ያሉ ሲሆኑ እነዚህኞቹ ግን በአጥፊዎቹ ተውጠው በፍፁም እንዳይንቀስቀሱና ድምፃቸው ወደ ውጭ እንዳይወጣ ታፍነው የተያዙ ናቸው። እንግዲህ ይህን ያህል ካልን ይህን የማፍረስ ስራ በበላይነት እንዲመሩ የተመረጡት ደግሞ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ናቸው።

ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ማትያስ፦ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን እንደዚህ ሳትከፋፈል በአንድ አስተዳደር ስር በነበችበት ግዜ ማለትም ሲኖዶስ አንድ መንጋውም እረኛውም አንድ በነበረበት ወቅት አቡነ ማትያስና አቡነ ጳውሎስ በገለልተኛ ቤተ ክርስቲያን ሆነው አሁን ለአለው መንግስት ገንዘብ እየሰበስቡ ይረዱ የነበሩ፤ እንዲሁም በአሁን ጊዜ በስርዓት ቤተክርስቲያን ያልተሾሙና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የፕትርክና አሿሿም ስርዓትና ደንብ ያልተሾሙ በመንግስት ፊት አውራሪነት ስራዬን ይሰሩልኛል ብሎ በመንግስት ፈቃደኝነት የተሾሙ ፓትሪያርክ ሲሆኑ ይህን ደግሞ የቤተክርስትያኒቱ ፍትሃነገስት እንደሚቃወም ኤጲስቆጶሳት አንቀጽ 5 ቁጥር 175 ረስጠብ 21<< በዚህ አለም መኳንንት ቢረዳ ከእነርሱም ዘንድ ለቤተክርስትያን ቢሾም ይሻር እርሱና ግብረአበሮቹ ሁሉ ይለዩ ብሎ ይነግረናል>> ቤተክርስቲያንን የማፍረሻ (የመክፈያ) ዋና አጀንዳቸው ደግሞ ስርዓት ቤተ ክርስቲያን ፈርሷል የሚል ነው

ስለ ስርዓት ከመነሳቱ በፊት የቤተክርስቲያንን ስርዓቶችና እና አገልግሎቶች በጥቂቱ እንመልከት
ሠዓታት መቆም
ማህሌት መቆም
ቅዳሴ መቀደስ
ስብከት ወንጌል ካሉት ግልጋሎቶች በጥቂቱ እነዚህን ስናይ

እንግዲህ እነዚህ አማሳኞች የሚጠቀሙት አንዱን ቅዳሴን በማጉላት (በማዉጣት) ሌላው አገልግሎት ላይ ሥርዓት እንደሌለ በማድረግ ያውም የፓትርያርክ ስም አለመጥራትን እንድ ትልቅ ክህደት (ዶግማ) የተጣሰ ያህል በማራገብ ቤተክርስቲያን መክፈልን ተያይዘውታል። እነርሱን የሚያስጨንቃቸው የፓትርያርክ ስም መጠራት አለመጠራቱን እንጂ የቤተክርስቲያኒቱ አገልግሎቶች ሰዓታቱ፣ ማህሌቱ፣ ስብከተ ወንጌሉ ፣ ቀኖናው፤ዶግማው ስርዓት የጠበቁ አገልግሎቶች መሆናቸው ላይ ግድ የላቸውም። ይህ ማለት በቅዳሴ ጊዜ ስም አለመጥራት ችግር አይደለም ሥርዓት አልፈረሰም ማለት አይደለም። ነገር ግን በቅዳሴ ጊዜ ስም መጥራት የቤተክርስትያኒቱን ስርአት ሙሉ ያደርገዋል ማለት አይደለም የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም የማይጠራበት ምክንያት እልባት ቢያገኝ የቤተክርስትያኒቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮችና የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥርዓትና አገልግሎቶች ሙሉና አንድ ወጥ ይሆናሉ። የቤተክርስቲያኒቱ ሰላም አንድነት እንዲሁም አስተዳደር አንድ ይሆናል። አባቶች በቅዳሴ ጊዜ የፓትርያርክ ስም እንዲጠራ ሲደነግጉ በስርዓተ ቤተ ክርስቲያን የተሾመ ስርአቷንና ዶግማዋን ቀኖናዋን ጠብቀው የተሾሙ የፓትርያርክ ስም እንዲጠራ እንጂ ከቤተክርስትያን የፓትርያርክ አሿሿም ስርዓት ውጭ ማለትም በመንግስት የተሾሙትን እንዲጠራ የሚል አይደለም ስርዓት ከተባለ ደግሞ አንድ ፓትርያርክ ፓትርያርክ ሊባል የሚችለው የቤተክርስቲያን ስርዓትዋንና ደንቧን የጠበቀ የእግዚአብሔርን ህዝብ በስርዓት የሚጠብቁ ኃይማኖቷን ቀኖናዋን ዶግማዋን ተከትሎ በእኩል የእግዚአብሔርን ህዝብ የሚመሩ አባትን እንጂ ከእግዚአብሔር ህዝብ ጡንቻ ያለውን መንግስት የሚያስቀድምን አባት አይደለም።ለዚህ ፍትሃ ነገስቱ ኤጲስቆጶስ አንቀጽ 5 ቁጥር 175 ረስጠብ 21 <<በዚህ አለም መኳንንት ቢረዳ ከነርሱም ዘንድ ለቤተክርስትያን ቢሾም ይሻር እርሱና ግብራበሮቹ ሁሉ ይለዩ >>ነው የሚለው።

ለአብነት ያህል የኤርትራውን ፓትርያርክ እንመልከት። የኤርትራው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ አንቶኒዮስ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጥር 13/ 2006 ዓ.ም. ጀምሮ ከመንበራቸው አንስቶ የቁም እስረኛ ያደረጋቸው የኤርትራው መንግስት ነው። ምክንያቱም ደግሞ መንግስት ገዝቱ ያላቸውን 3000 ምእመናን አልገዝትም በማለታቸውና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ በመጠየቃቸው ሲሆን እርሳቸውም ከመንግስት ጡንቻ የእግዚአብሔር ይበልጣል በማለት አስካሁን በቁም እስር ላይ ይገኛሉ። መንግስትም አሳቸውን አስሮ በምትካቸው የመንደፈራውን አቡነ ዲዩስቆሮስን መሾሙ ይታወቃል።ይህን መረጃ በድሬቲዩብ January 22 2015 ላይ ተገልጾ እናገኛለን ልብ በሉ እውነት አሁን አባቶች ሥርዓቱን ሲሰሩ በቅዳሴ ሰዓት በመንግስት የተሾሙትን የአቡነ ዲዮስቆሮስ ስም እንዲጠራ ነውን? አይደለም። ትክክለኛው ስርዓት በእስር ላይ ያሉት የአቡነ አንቶኒዮስ ስም እንዲጠራ እንጂ በመንግስት የተሾሙትን አለመጥራት እንደውም ስርዓትን መጠበቅ ነው።በመንግስት እንደተሾሙ እየታወቀ መጥራት ስርአት ማፍረስ ነው። እንደ ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ቀኖና መሰረት በአሁን ሰአት ቤተክርስትያን ፓትርያርክ የላትም ምክንያቱም ፓትርያርክ ይሰደዳል መንበር ግን አይሰደድም በስደት ላይ ያለው ሲኖዶስ ግን መንበር አቋቁሟል እንዲሁም የሃገር ውስጥ ሲኖዶስም በመንግስት በተሾመ ፓትርያርክ ተሰይሟል ቀኖና ቤተክርስትያን ደግሞ በመንግስት የተሾመ ይሻር ይላል እኔ ሳልሆን ቀኖናው ይሽራል ስለዚህ የትኛው ስም ይጠራ ?

እነዚህ አማሳኞች እውነት አንድነት ከሆነ ዓላማቸው ለምን ቃለ አዋዲውን አይቀበሉም? ለዚህ የሚመልሱት ደግሞ ከአሜሪካን ሀገር ጋር የማይስማማ ስላለው ነው ባይሎ የምንቀርፀው ይላሉ። ምክንያቱም የተነሱበት ዓላማ ያ ስላልሆነ ነው፤ እንጂ ከአሜሪካን ሃገር ጋር የማይስማማ ቢሆን እንኳን ጥያቄ ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርበው ቅዱስ ሲኖዶስ ከአሜሪካ ሃገር ህግ ጋር የሚስማማ ሊያወጣላቸው ይገባል እንጂ ማንም ሰው ተነስቶ ቃለ አዋዲውን ሊያሻሽል አይችልም። ምክንያቱም የማሻሻልም ሆነ የማስተካከል ስልጣን ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ስለሆነ ። እንዲሁም እነዚህ በኢትዮጵያ ስር ነን ብለው ቃለ አዋዲውን የማይቀበሉት አንድ ባይሎ(መተዳደሪያ) እንኳን የላቸውም። ለምሳሌ በአንድ እስቴት ውስጥ 10 ቤተክርስቲያን ቢኖር እንኳን 10 የተለያየ ባይሎ(መተዳደሪያ) ነው ያላቸው እንጂ ለአስሩ እንኳን አንድ ባይሎ(መተዳደሪያ) የላቸውም ምክንያቱም ዓላማው መለያየት ስለሆነ ባይሎው አንድ ከሆነ አንድነትን ስለሚያመጣ አያስፈልግም። ይህን ደግሞ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ፓትርያርኩን ጨምሮ በማፍረስ ስራ ላይ የተሰማሩት አንድም ምእመናንን በመከፋፈል በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት እድሜ ማራዘም ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የራሳቸውን የወደፊት መውደቂያ እያመቻቹ ነው። መንግስት ተቀይሮ ወይም በሆነ ምክንያት የቤተክርስቲያን አንድነት ቢመለስ እነዚህን ቤተክርስቲያኖች ገለልተኛ ለማድረግና ሸሽተው መጥተው በቁጥጥራቸው ስር አድርገው የቤተክርስቲያናችን ትንሳኤ እንደገና ወደ ኋላ ለመጎተት የታለመ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ምእመን ሆይ ይህ ሁሉ ደባ በቤተክርስቲያን ላይ ሲሰራ ከዚህ ነገር ላይ ጥቂት ተጠቃሚዎች ካህናትና ግለሰቦች ስላሉ ጉዳዩን በደንብ አጢነን ዝም ብለን ከምንከተል ተው ልንላቸው ይገባል።

ይህ የአስተዳደር ችግር በምእመን የሚፈታ ችግር አይደለም የጀመሩትም አባቶች ናቸው የሚፈቱትም አባቶች ናቸው። ሁለቱ አባቶች ከፈለጉ አንድ ያደርጉታል ከፈለጉ እንደበተኗት ያስቀሯታል። ሁለቱ ከታረቁ ሁሉም መንጋውም ግን እረኛውም አንድ ይሆናል። ምእመን ቤተክርስትያንን አንድ እናድርግ ቢል ግን ሁከትና እረብሻ ነው የሚፈጠረው ምክንያቱም አባቶች አይፈልጉማ። አንድነት እንዳይመጣ እጃቸውን ያስገባሉ። ስለዚህ እኛ ምእመናን ግን ስደተኛ ገለልተኛ በኢትዮጵያ ሳንል አንድነታችንን ጠብቀን በያለንበት ቤ/ተክርስትያን እየተገለገልን በፍጹም ወንድማማችነት መፍትሔ እስኪመጣ ድረስ እግዚአብሔርን እየጠየቁ መኖር ያስፈልጋል።

እነዚህ አማሳኞች በተለያዩ ቦታዎች ከሰሯቸው የማፍረስ ስራዎች ውስጥ ለኣብነት ያህል በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስቲያን ያደረጉትን እንመልከት

በመጀመሪያ የሜኒሶታ ደ/ሰ/መ/ቤተክርስትያን ማን ናት?በሜንሶታ ካሉ አብያተክርስቲያናት አንዱ ላይ ያዉም ደብረሰላም መድኃንያለም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ለምንተመረጠ?

ደብረሰላም መድኃኒዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ከተመሰረች ከ1993 እ. ኤ. አ.በገለልተኝነት የምትታወቅ ሲሆን በተለያዩ ጳጳሳት የተባረከችና በአሁን ጊዜም የተለያዩ ጳጳሳትና የቤተክርስትያን ታላላቅ አባቶች ከኢትዮጵያ ድረስ በመምጣት ምክር ትምህርትና ቡራኬ ያልተለያት እንዲሁም በአሜሪካን ሀገር አሉ ከሚባሉት ታላላቅ አድባራት በአሁን ሰዓት ግንባር ቀደም ናት ቢባል ማጋነን አይሆንም በአሁን ግዜ አገልግሎቷን በማስፋት በአመት 365 ቀናት ማለትም አመቱን በሙሉ ለተገልጋዮች ክፍት በመሆን የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት ብቸኛዋ ቤተክርሰትያን ናት ቢባል ማጋነን አይደለም።

በደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የሚሰጡ አገልግሎቶች
(1)ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 6am – 10am ለጸሎት ክፍት ሆኖ የእጣን ጸሎት እና የኪዳን ጸሎት ይደረጋል።
(2)ዘወትር እሁድ የሰንበት ቅዳሴ ከነግህ ጸሎት ጋር ከንጋቱ 5am ጀምሮ ይሰጣል።
(3)ዘወትር የአዘቦት ቅዳሴ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ባሉት ቀናት ወር በገባ የሚካኤል ፣ ፣ የኪዳነምህረት፣ የገብርኤል

የማርያም እና የመድኃኒዓለም ቀን ይቀደሳል።
(4) በአመት 8 ግዜ አመታዊ በአለ ንግስ ይደረጋል።በሁሉም በዓላት የዋዜማ አገልግሎት ከ3pm ጀምሮ ይሰጣል።

እንዲሁም በበዓሉ ቀን በማህሌት ከ2am ጀምሮ እስከ በዓሉ ፍጻሜ በድምቀት ይከበራል። እንዲሁም ከዓመታዊ

በዓላት በተጨማሪ የጽጌ ፤ የደብረታቦር ፤የስብከት፤የኖላዊ፤የልደት፤ የጥምቀት፤የሆሳእና፤የትንሳኤ፤ የዳግማ ትንሳኤ እና የጰራቅሊጦስ ማህሌት ይቆማል።
(5)በዓብይ ጾም 5 ቀን ሙሉ ስርአተ ሰሙነህማማት ከጠዋቱ 6am ጀምሮ ይከናወናል።
(6)14 ቀን የፍስለታ ሱባኤ በለሊት ሰዓታት፤በውዳሴ ማርያም ትርጓሜ እና በቅዳሴ አገልግሎት ይሰጣል።
(7)የመስቀል በዓል በየዓመቱ ኢትዮጵያዊ በሆነ መልኩ በድምቀት ይከበርል።
(8)ዘወትር ሐሙሰ ከምሽቱ 5pm ጀምሮ የስብከተ ወንጌል ትምህርት ይሰጣል ።
(9)ዘወትር እሁድ ከቅዳሴ በሁዋላ ማህበረ ካህናቱ እና የሰንበት ት/ቤት መዘምራን በህበረት የየእለቱን እና የየባእላን ያሬዳዊ ዜማ (ወረብ) ይዘመራል።እንዲሁም ከአገልግሎት በሁዋላ የባእላቱ ቀለም ይጠናል።
(10)ዘወትር እሁድ ከቁርባን በሁዋላ ለህጻናትና ወጣቶች መንፈሳዊ እና የቋንቋ ትምህርት ይሰጣል።
(11)ለቤተክርስትያን ዓባላት መረዳጃ እድር ይሰጣል።
(12) በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተለያዩ አድባራትና ገዳማት በተለያዩ ጊዜያት ከፍተኛ የገንዘብ እርዳታ ያደርጋል።

በተጨማሪም ቤተክርስትያኒቱ ከእዳ ነጻ ፤የዘር፤የጎሳ፤ልዩነት ሳይኖራት ከሁሉም አይነት የብሄር ተዋጽኦ በእኩል ፍጹም ኢትዮጵያዊነትን በተሞላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ህጉዋን፣ ስርአቷን፣ ቀኖናዋንና ዶግማዋን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት እስከ አሁን ድረስ በመድኃኒዓለም ሃይል ያለች እና ወደፊትም የምትኖር በተጓዳኝም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የህንጻ ዲዛይን አሰራር መሰረት በእዚህ በሜንሶታ ለቤተክርስቲያኒቱና ለሃገራችን እንዲሁም ለተተኪ ትውልድ አሻራ ጥሎ ለማለፍ ባለ 3 ጉልላት ያለው የተለያዩ የአገልግሎት ዘርፍ መስጠት የሚችል ካቴድራል ለመገንባት እንዲሁም ቤተክርስትያኒቱን በውጭው ዓለም ከፍ አድርጎ ሊያሳይ የሚችል እና ዶግማዋና ቀኖናዋ ተጠበቆ ሳይበረዝ ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚደረገው ርብርብ ለቤተክርስትያኒቱ እጅግ ጠቃሚና ለመንግስት ደግሞ እራስ ምታት ስለሆነበት የመንግስት አይን አረፈበት ።

እስቲ ልብ በሉ ይህን ሁሉ አገልግሎት እና ስርአት ጠብቃ የያዘች ቤተክርስትያን ልትደገፍና ልትበረታታ ይገባታል እንጂ ይህንን ሁሉ ስርአተ ቤተክርስትያንን እና አገልገሎትን ወደጎን ትቶ የአቡነ ማትያስን ስም አልተጠራም ተብሎ በአንድ ቀን ቤተክርስትያንን አፍርሶ መሔድ ባልተገባ ነበር። ይሁን ስህተት እንኳ ተገኝቶም ከሆነ በምክር በትምህርት መስተካከል ሲችል በክፉ መተያየትን እና መለያየትን ባላመጣን ነበር። እዚህ ጋ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የተናገሩትን ጠቅሼ ልለፍ [በዘልማድ ሆኖ ገለልተኞች ብለው ፈረጇቸው እንጂ በሀገረ ስብከትም እንተዳደራለን የሚሉ የራሳቸውን ባይሎ ቀርጸው የሚተዳደሩ እንጂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቃለ አዋዲን አንድም የሚተገብር ቤተክርስቲያን በመላው አሜሪካ አለ ብዬ አልጠብቅም………እንዲሁ ገለልተኛ ብሎ ማራቅ ለቤተ ክርስቲያን ጉዳት እንጂ ጥቅም የለውም በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ያልተወገዙና ያልተለዩ አካላት መሆናቸው እየታወቀገለልተኛ ብሎ ማራቅ አይገባም። ልዩነት ሊኖር ይችላል ይህን አምነን መቀበል አለብን። የአስተዳደር እንጂ የሀይማኖት ልዩነት የለንም ሁሉም በስርዓት የሚቀድሱ ማህሌት የሚቆሙ ክርስትና እየተነሳባቸው ሰው እየተዳረባቸው ፍታት እየተፈታባቸው አስፈላጊው መንፍሳዊ ነገር ሁሉ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን እየተፈጸመባቸው እየታወቀ ገለልተኛ ብሎ መጥራት ምን ማለት ነው? ሊታረም የሚገባው ነው……..ወግድ ብሎ ማራቁ ክርስቲያናዊ ተግባር አይደለም ። በቅዳሴ ላይ የፓትርያርክ ስም አለመጠራቱ ችግር አይደለም አልልም ችግር ነው። ነገር ግን በዚህ ምክንያት ሊለያየን አይገባም ብዬ አምናለሁ] እኚህ አባት ይህንን ያሉት ጁን 12,2012 ላይ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ ነው።

በተጨማሪም በፋይናነስ በአካውንት ውስጥ ሚሊየን ዶላር አለ የሚባል ነገር ሲመጣማ በጣም ትኩረት ተሰጠው ስለዚህ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድበት ከመንግስት ትእዛዝ ተላለፈበት ።

መንግስትም ይሰሩልኛል ብሎ ባስቀመጣቸው አባት መሪነትና በተላላኪዎቻቸው አንድ ተብሎ ተጀመረ ይህንንም የማፍርስ ስራም እንዲሰሩ ሰዎች ተመለመሉ።

የተመለመሉት እነማን ናቸው?
ብጹዕ አቡነ ዘካርያስ የኒወርክና አካባቢው ሀገረስብከት ጳጳስ፦ የጎጃም ሃገረስበከት ጳጳስ የነበሩና የፓትርያርክ የበላይ ቅዱስ ሲኖዶስ ሆኖ ሳለ ነገርግን አቡነ ጳውሎስ ከቅዱስ ሲኖዶስ በላይ በመሆን ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝና ፍቃድ በአቡነ ጳውሎስ ትእዛዝ ለኒዎርክና አካባቢው ሃገረ ሰብከት የተዘዋወሩና በፍትሃነገስት ላይ ኤጲስቆጶሳት አንቀጽ 5 ቁጥር 158 ኒቅያ 77<<ኤጲስቆጶስ በአገሩ መስፋትና መጥበብ በህዝቡ ማነስና መብዛት ምክንያት ኤጲስቆጶስነት ከተሾመበት አገር ወጥቶ ወደ ሌላ አገር አይሂድ ስለዚህም ከእርሷ የሚሻለውን ሊፈልግ አይገባውም ይህ ለእርሱ አይገባውምና።ለሰው ሁሉ ድርሻው ከእግዚአብሄር ተሰጥቶታል እንጂ ይህ ከህዝባውያን ወገን ሚስት ያገቡ ሰዎችን ይመስላል ያለዝሙት ምክንያት ሰው ከሚስቱ ቢሰነካከል ከእርሷ በምትበልጥ ሊለውጣት ቢፈልግ እርሱ በጣም በደለኛ ነው።ከአገራቸው የተሻለ አገርን የሚፈልጉ ኤጲስቆጶሳትም ካህናትም እንደዚሁ ናቸው ስለዚህም አውግዘን ለየናቸው ።ይህ ልማድ መጥፎ ነውና ።>>የሚለውን በመተላለፍ የተሾሙበትን ሃገረ ስብከት ትተው የመጡ ፤ ኤጲስቆጶሳት አንቀጽ 5 ቁጥር 167 ድስቅ 30<<ከነውር ወገን አንዲቱ ነውር በኤጲስቆጶስ ላይ ብትታወቅ ከመዓርጉ የሚዋረድበትን ከሹመቱ የሚሻርበትን ምክንያት ይናገራል።>>ይህንን በመተላለፍ እምነት ያጎደሉ እንዲሁም በኤጲስቆጶስ አንቀጽ 5 ቁጥር 172<<አንድ ሊቀጳጳስ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ አልመጣም አይበል የታወቀ ምክንያት ካላገኘው በቀር ወደኋላ አይበል የቀረበትንም ምክንያት ይጻፍ ፈቃድም ይቀበል>> የሚለውን በመተላለፍ እዚህ ሀገር ከገቡ ጀምሮ ከ10 ግዜ በላይ አንድም ስብሰባ ያልተካፈሉ እንዲሁም እንደ ቤተክርስትያን ቀኖና ህግና ስርአት ቅዱስ ሲኖዶሱ የማያውቃቸውና ጵጵስናቸው የተሻረ አባት ናቸው።እንዲሁም በፓትርያርክ ቀብርም ሆነ ሹመት ላይ ያልተገኙ አባት ናቸው።ለዚህ ስራ ሲመረጡ ስልጣናቸውን ተገን በማድረግና በመጠቀም በማውገዝና በማስፈራራት ከቀኖና ውጭ በሆነ መንገድ እንዲያስፈጽሙ ማድረግ ነው።
በእዚህ በሚንሶታ እስቴት ውስጥ የሚገኙ በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን ስር ነን የሚሉ ነገር ግን ያይደሉ ከመንግስት ጋር በቅርበት የሚሰሩ ካህናትና ግለሰቦች ናቸው።
በዛው በደብረሰላም መድሃንያለም ለብዙ ግዜ አገልጋይ የነበሩ እንዲሁም ተገልጋይ የነበሩ ካህናትና ዲያቆናት ቤተክርስትያኒቱ የነበረባቸውን ስጋዊ ችግር በገንዘብም ሆነ በተለያየ ነገር የቀረፈችላቸው በችግራቸው ግዜ የቀረቧት ዛሬ ደግሞ ሲሞላላቸውና ጊዜ ፊቷን ዞር ስታደርግላቸው የተነሱባት የእናት ጡት ነካሾችና እንዲሁም ለዚህ ስራ የተመረጡ ጥቂት የቤተክርስትያን ተቆርቁዋሪ መስለው ቤተክርስትያን የማፍረስን ስራ የሚሰሩ ግለሰቦችና እግዚአብሄርን የማያውቁ ነገር ግን የእግዚአብሄር አገልጋዮች የነበሩ የሰንበት ት/ቤት አገልጋዮች ናቸው።

እነዚህ ከላይያየናቸው አማሳኞች ለስራቸው መጀመሪያ የተቀበሉዋቸው ሁለት መመሪያዎች
አንደኛው በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ ቤተክርስትያኒቱን ከነሙሉ ንብረቷ በመንግስት ቁጥጥር ስር ማዋል ይሄኛው በጣም አዋጭ ሲሆን ብዙ ጊዜ ፤ገንዘብና ጉልበት ቆጣቢ እንዲሁም በአጭር ጊዜ የሚጠናቀቅ ነው።
ሁለተኛው ደግሞ ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ያችን ትልቅ የኢ/ ኦ/ተ/ቤተክርስትያንን ዶግማዋንና ቀኖናዋን እንዲሁም ስርዓተ ቤተክርስትያን ጠብቃ የምትሄደውን ለሁለት ከፍሎ ከተቻለ ማጥፋት ካልሆነም ማዳከም የሚል ነው ይህ ደግሞ ግዜ ይወስዳል። እንግዲህ እነዚህ አማሳኞች በመመሪያቸው መሰረት ኔትወርካቸውን ዘርግተው ከኢትዮጵያ ድረስ መመሪያ ሲያስፈልግ በይፋ በቡራኬ መልክ አይዟችሁ በርቱ ከጎናችሁ ነን በማለት እንደየ አስፈላጊነቱ ደግሞ ከሃገረስብከቱና ከቅዱስ ፓትርያርኩ በሚመጡ ፍጹም መንፈሳዊነት በሌላቸው ቤተክርስትያንን የሚከፍሉና የሚበትኑ መልእክቶችን በመጻጻፍ የክርስቲያኑንና የቤተክርስትያኑን ክብር ያላገናዘበና የኢትዮጵያን ኦ/ተ/ቤ አማኙን አንገት ያስደፋ እንዲሁም የሚያሸማቅቅ ደብዳቤዎችን በመላላክና ግልጽ በሆነና በድብቅ የስልክ ግንኙነቶች በማድረግ ቤተክርስቲያኒቱ ላይ ጥቃታቸውን ቀጠሉ።



የአጀንዳቸው መሠረት ስርአተ ቤተክርስቲያን ፈርሷል

እንግዲህ እነዚህ ለማፍረስ በተመለመሉ ኅይሎች አማካኝነት ከ20 ዓመት በላይ ቤተክርስትያኒቱ ሰላሙዋንና አንድነቷን ጠብቃ የኖረችበትን አቋሟን ወደጎን በመተው የቤተክርስትያን አገልግሎት ቅዳሴ ብቻ በማስመሰል ስርአተ ቤተክርስትያን ተጥሷል በማለት በቅዳሴ ግዜ የፓትርያርክ ስም አልተጠራም መጠራት አለበት በሚል በሰፊው ማራገብ ጀመሩ ።ጥያቄአቸውንም አቀረቡ ጥያቄአቸውም አግባብ፤ተገቢና መብታቸውም ስለሆነ መልስ መሰጠት አለበት በሚል በቤተክርስትያኒቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት ተደረገ በአብዛኛው አባላት ከጠቅላላ አባላቱ ከ50+1 በላይ የሆነው አባል አንድነቷ ተጠብቆ በአለችበት አቋሟ እንድትቀጥል የሚል ውሳኔ ተሰጠ። እነርሱ ግን አላማቸው ሌላ ነበርና ተስማምተው ድምጽ የሰጡበትን በማጠፍ ጠቅላላ ጉባኤ አልተሟላም አሉ እሺ ካልተስማማች እንደገና ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራ ሲባሉ በፍጹም እኛ በመረጥነው መንገድ ብቻ ነው መሆን ያለበት አሉ።

እነዚህ አማሳኞች በመጀመሪያ ደረጃ ያስቀመጡት አልሳካ ሲላቸው ሁለተኛ አማራጫቸውን በመጠምዘዝ በሁከትና በረብሻ ቤተክርስትያኒቱን ማወክ ተያያዙት ጠቅላላ ጉባኤ ይጠራና አባላቱ ይወስንበት ሲባሉ በህጋዊና በሰላማዊ መንገድ እንደማይሆንላቸው ስላወቁት በፍጹም ጠቅላላ ጉባኤ ሳይጠራ እኛ የፈለግነውን ነገር ብቻ ካልተደረገ አሉ ። ይህን ግዜ ነበር ህግ ያለበት ሀገር ስለሆነ በህግ እንዲዳኝ ወደ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ያመራው ። ጉዳዩም በፍርድ ቤት እያለ በዘረጉት ኔትዎርክ በመታገዝ እንዲያስታርቁ ሳይሆን ከተቻለ አስፈራርተውም ሆነ አውግዘው ወደ እራሳቸው አላማ ማለትም መንግስት ወደ ሚቆጣጠራት ቤተክርስትያን የማስገባት ስራ እንዲሰሩላቸው ካልሆነም የተፈለገውን የመክፈል ሰራ እንዲሰሩላቸው ሁለት ጳጳሳትን አመጡ
አቡነ ማርቆስን ከኢትዮጵያ
አቡነ ዘካርያስን ከአሜሪካን

በማስመጣት በአዳራሽ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ያውም በአርምሞ ሱባኤ በሚያዝበት በታላቁ አብይ ጾም ህዝብን ከሚመራ ጳጳስ የማይጠበቅ የስድብ አፍ በቤተክርስትያኒቱ፤በንዋያተ ቅዱሳቱ፤አላማቸውን በማይደግፉት ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም ምእመናን ላይ ሲሳደቡ፤ሲሳለቁና ሲስቁ ውለው እና አድረው እንዲሁም በማግስቱ የመጋቢት መድኃኒዓለም በዓለ ንግስ ላይ በአቡነ ማትያስ እየተመሩ የመጡት ልዑካን ከነግብራበሮቻቸው በጣም ከአቅም በላይ የሆነ ትእግስት እና እልህ አስጨራሽ ትእይንት በቤተክርስትያኑ ዓውደ ምህርት ላይ በማሳየታቸው ምእመኑ ከአቅሙ በላይ ስለሆነበት አግባብ ያልሆነ ስድብ በጳጳሳቶቹ ላይ እንዲሳደብ አድርገውታል የእነርሱም አላማ በአውደምህረቱ ላይ ያልተገባ ትእይንት በማድረግ ምእመኑን ንዴት ውስጥ በመክተት ያልሆነ ቃል እንዲናገር ማድረገ ነበረና እነዚህ አፍራሽ ሃይሎች ይህችን አጋጣሚ በመጠቀም ጳጳሳቶች ተሰደቡ እያሉ ምእመኑ ላይ ተጽእኖ ለመፍጠር ሞክረዋል ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ማንነታቸው ተጋለጠ። እዚህ ጋር አንድ ልብ ልንለው የሚገባ ነገር አለ ጳጳስ ይሰደባል ግን አይሳደብም ፣ይመታል ግን አይማታም፣ይገደላል ግን አይገድልም፣ያስታርቃል ግን አያጣላም፣ ምእመንን ይሰበስባል ግን አይበትንም ፣ፍቅርን ይዘራል ግን ጥላቻን አያበቅልም እንዲሁም አንድ ጳጳስ ገና ሲመነኩስ እንደሞተ (የሞተ)ስለሆነ በቁሙ ተስካሩን ያወጣል የጵጵስናውን አስኬማ ሲደፋ ደግሞ ለሃይማኖቱ፣ለህዝቡ፣ለተበደለ፣ለተገፋ፣ፍትህ ላጣ ፣ለተጨቆነ ፣ለቤተክርስትያን ለመሳሰሉት ሊሰደብ፣ሊገረፍ፣ሊታረዝ፣ሊታሰር፣ ብሎም ሞትም ከአስፈለገ ሊሞት ነው እንጂ ሹመቱ እንደ አለማዊ ሹመት አይደለም። እነዚህ ጳጳሳት ግን እንደነርሱ ፍላጎት ከፍለውት ነው የሄዱት ሆኖም ግን በመድኃኒዓለም ቸርነት ምእመኑ ለቤተክርስትያኑ ጠንክሮ እንዲቆም ነው ያደረጉት ቆሞም ተገኘ ።ከዛም ጳጳሳቶቹ ለአፍራሽ ካህኖቻቸው መመሪያ ሰጥተው የአቡነ ማትያስን ስም ሳትጠሩ ከእንግዲህ እንዳትቀድሱ ብለዋቸው ለሰሩት ሁከትና ብጥብጥ ተመራርቀው እና ተመሰጋግነው ጳጳሳቶቹም ወደ መጡበት ተመለሱ።

እለተ ሆሳዕና፦

እነዚህ አማሳኞች የሆሳዕና በዓል ከመደረሱ ከቀናት በፊት አንድ ቤተክርስትያኒቱን በእጃቸው የሚያስገቡበት የመሰላቸውን ተንኮል(ዘዴ) ቀይሰው ያች ቀን እስክትደርስ መጠባበቅ ጀመሩ። ድንጋዮች ያመሰገኑበት ሻጮችና ለዋጮች በጅራፍ እየተገረፉ ከቤተመቅደስ የወጡበት ክርስቶስ ቤቱን ያጸዳበት ቀን እለተ ሆሳህና በታላቋ የምስጋና ቀን ሆሳህና በ2006 በሚንሶታ በደብረ ሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስትያን አሳዛኝ ነገር ተከሰተ።

የሚገርመው ደግሞ እርስ በእርሳቸው ስለማይተማመኑ እንዳይካካዱ ተፈራርመው በሌሊት ወደ ተከበረችው የእግዚአብሄር ቅዱስ ስጋው እና ክቡር ደሙ ወደ ሚፈተትበት ቅድስት መቅደስ ገቡ። ህዝበ ክርስትያኑ ለአገልግሎት መጡ ነው ያለው እነርሱ ግን ለአሰቡት አላማ ነው የመጡት እቅዳቸውም ከቅዳሴ በፊት የሚከናወኑ ስርአቶች ከተከናወኑ በሁዋላ በቅዳሴ ጊዜ የአቡነ ማትያስ ስም ከተጠራ እንቀድሳለን ካልተጠራ አንቀድስም ብለው አቋማቸውን በፊርማቸው በይፋ አሳወቁ በዚህን ግዜ በሆሳዕና እለት ድንጋዮች በአመሰገኑበት ዕለት እኛ ካልቀደስን እንዲሁም የሰንበት ተማሪዎች ካልዘመሩ ቤተክርስትያኑ ይዘጋል ሳይወዱ በግዳቸው የእኛን ፍላጎት ያሟላሉ ብለው የእግዚአብሄር ቤት መሆኑን እረስተው የትዕቢት ስራን ሰሩ። በዚህን ጊዜ ነበር መድኃኒዓለም ጅራፉን ያነሳው መድኃኒዓለም ከተነሳ ያውም በሆሳዕና ዕለት እስከ መጨረሻው ካላጸዳ አይመለስም እናም የማጽዳቱን ስራም ጀመረ።

እነሆ ከወደ ቤተመቅደስ አንድ ድምጽ ተሰማ “ እባካችሁ በዚህ በታላቅ ቀን በሆሳዕና ድንጋዮች ባመሰገኑበት ቀን የጳጳስ ስም ካልተጠራ ብለን የእግዚአብሔርን ስም አንጠራም አይባልም እውነት ከእግዚአብሔር ምስጋና የሰው ምስጋና ይበልጣልን ? በረከት ያስወስድብናል በጅራፍም ያስገርፈናል ከቤቱም ያስባርረነናል አሁን ምእመኑን ከምንበትን ቤተክርስትያኑንም ከምንዘጋ እስከዛሬ ድረስ ለብዙ ዘመን የጳጳስ ስም ሳንጠራ የቀደስንበትን ቤተክርስትያን አንቀድስም ከምንል እንቀድስና ጥፋትም ሆኖ ቢገኝ እንኳን ይቅርታ እንጠይቅበት’’ የሚል ቃል መጣ እነርሱ ግን ከበላይ ነው የታዘዝነው ብንቀድስ ክህነታችን ይያዛል መቀደስ አንችልም ብለው አቋማቸውን ገለጹ በዚህን ግዜ ነበር መድኃኒዓለም ያዘጋጃቸው ካህናትና ዲያቆናት ቅዳሴ መቀደስ ሲጀምሩ የአማሳኞቹ ካህናትና ዲያቆናት ተከታይ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች እንዲሁም ጥቂት የእነርሱ አጀንዳ የእውነት የቤተክርስትያን አንድነት የመሰላቸው ወደ 50 የሚጠጉ ንጹሃን የቤተክርስትያን ምእመን አንድ በአንድ በየተራ ቤተመቅደሱን ለቀው ወደ ፓርክ በማመራት የሆሳእና እለት እግዚአብሔር መድኃኒዓለም በእየሩሳሌም ለቤቱ አልታዘዝ ያሉትን ጠራርጎ እንዳስወጣ ሁሉ በዳግማዊቷ እየሩሳሌም በሚንሶታ ደብረ ሰላም መድኃኒዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ ተደገመ። እግዚአብሔር በቤተመቅደሱ ተመሰገነ ከበረ ተወደሰ አቡነ ማትያስ በፓርክ ተመሰገኑ ከበሩ ተወደሱ ።

ከሁሉም በጣም ለየትና ግርም የሚለው ደግሞ እሁድ እሁድ ሁልጊዜ ከቅዳሴ በሁዋላ የዕለቱ ያሬዳዊ ዜማ (ወረብ) ይወረባል (ይዘመራል) ያን ግዜ ግን ሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች በሙሉ ወጥተው ፓርክ ሄደው ስለነበር ማን ሊዘምር ነው ሲባል ለካ እግዚአበሔር እኛ ስናምጽ ለራሱ የሆነ ሰው ለቤቱ ያዘጋጃል፤ ከምእመን እርሱ መረጠ አንድ አንድ እያሉ አውደ ምህረቱን ሞሉት እግዚአብሔር እንዲያመሰግኑት ከመረጣቸው መካከል አንዲት ልትወልድ የደረሰች እህት የመድኃኒዓለምን ድምጽ በሰማች ግዜ ከተቀመጠችበት ብድግ ብላ ልታገለግል ልትዘምርለት መጣች የአምላካችን ስራው ድንቅ ነው ።አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ትዝ አለኝ በሉቃስ ወንጌል ላይ ምዕ 1 ቁጥ 41 እንዲህ የሚል ቃል አለ “ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ግዜ ጽነሱ በማህጸኗ ውስጥ ዘለለ በኤልሳቤጥም መንፈስቅዱሰ ሞላባት ………… ኤልሳቤጥም እነሆ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ግዜ ጽንሱ በመሃጸኔ በደስታ ዘሏልና’’ ብላ እንዳመሰገነች አንዲት ልትወልድ የደረሰች ነብሰጡር የመድኃንያለምን ድምጽ በሰማች ግዜ ከተቀመጠችበት በድግ ብላ መቁዋሚያውንና ጽናጽሉን አነሳች በዚህን ግዜ በማህጸኗ የነበረው ጽንስ ዘለለ ፤ሰገደ፤አመሰገነ እግዚአብሄር በሆሳዕና እለት በድንጋዮችና በህጻናት ተመሰገነ ማለት ይህ አይደል።

እንግዲህ ምእመናን እሺ ብንል ለእግዚአብሔር ብንታዘዝ የምንከብረው የምንባረከው እኛው ነን እምቢ ብንል ደግሞ የምንጎዳው እኛው ነን እግዚአብሔር እንደው ምንም የሚጎልበት አንዳች ነገር የለውም ቢፈልግ በመሃጸን ያሉትን ያስነሳል ቢፈልግ ህጻናትን ያስነሳል ቢፈልግ ድንጋዮችን ያስነሳል ይህንንም ደግሞ በሚንሶታ ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አይተነዋል ።

የአውጋዡንና የተከታዮቹን ማንነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ውግዘት አውጋዡም ሆነ ተከታዮቹ በእውነት የኢ/ኦ/ተ ቤተክርስትያን አማኞች ናቸውን?

እዚህ ጋር ተከታዮቹ ብዬ የገለጽኩት ይህንን ተግባር ተቀብለው የሚያስፈጽሙትን እንጂ ምዕመኑን አይወክልም ምክንያቱም ምዕመኑ በንጹህ ልቡ የእውነት አንድነት መስሎት ስለሚከተል በበመጀመሪያ በኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ቀኖና መሰረት ስልጣኑ የተሻረ አባት ሊያወግዝም ሆነ ሊለይ አይችልም የተወገዘ እንዴት ያወግዛል ሲቀጥል በሰሞነ ሕማማት ማለትም ከሆሳእና እስከ ትንሳኤ ባሉት ቀናት ውስጥ እንኳን ማውገዝ ፤ማሰርና መለየት ቀርቶ መፍታት እንኳን በማይቻልበት ቀን አቡነ ዘካርያስ የደብረሰላም መድኃንያለም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ካህናት ፤ዲያቆናት እንዲሁም ምእመንን በፍትሐነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 600 <<በሰሞነ ሕማማት ክርስትና ማንሳት፤ ክህነት መስጠት፤ለሞቱ ሰዎች መጸለይ አይገባም በእነዚህም ቀኖች ውስጥ ፈጽሞ ማገልገል ይገባል እንጂ በሰሞነ ሕማማት ስለሚሞቱት ሰዎች የሙታን ግንዘትና የሃዋርያት ስራ ወንጌላት የሙታን ፍታት በሆሳዕና በዓል ይነበብ እንጂ በጸሎተ ሐሙስ ጸሎተ ተአምኆ እግዚአ ሕያዋን የቡራኬ ጸሎት አይባልም(አይጸለይም)ቅዳሜ ግን እግዚአ ሕያዋን ይባላል ፍትሃት ይፈታል ከመሳለም በቀር ጸሎተ እጣንም ይጸለያል በእለተ እሁድ ግንዘት ማድረግ በፋሲካ ቀንም ማልቀስ አይገባም >> የሚለውን በመተላለፍ በሰሞነ ሕማማት ቀኖናውን ጥሰው አናገለግልም ብለው የወጡትን ምንም ሳይሉ ቀኖናውን ጠብቀው ምንም ሳያጉዋድሉ ያገለገሉትን በሙሉ በጸሎተ ኅሙስ ካህናቱና ዲያቆናቱ ቅዳሴ ቀድሰው ሲወጡ እነዚህ አማሳኞች ከአቡነ ዘካርያስ የመጣ የውግዘት ደብዳቤ ነው ተቀበሉ ብለው ፎቶና ቪዲዮ ደግነው ደብዳቤውን ለመስጠት ሞከሩ የተቀበለውም ተቀበለ ያልተቀበለም አልቀበልም ብሎ ወደ ቤቱ ሄደ።የተላለፈውንም ውግዘት እንደሚከተለው እናያለን፦
ቤተክርስትያኒቱ ፦ከተመሰረተች ከ20 ዓመት በላይ የሆናት በጳጳሳት ተባርካ ብዙ ክርስትያን የተጠመቀባት ፤የቆረበባት ፣የተዳረባት ፣ሰው ሲሞት ፍትሃት የተደረገባት፣ብዙ መንፈሳዊና ሚስጥራዊ ግልጋሎት የተሰጠባት ቤተክርስትያን እግዚአብሔር አምላክ የምእመኑን ጸሎት የተቀበለባትና የፈጸመባት ቤተክርስትያንን ከዛሬ ጀምሮ አሮጌ ህንጻና የአሳማ(የከብቶች) ማርቢያ ትሁን ብለው በህንጻ ቤተክርስትያኒቱ ላይ እንዲሁም በንዋያተ ቅድሳቱ ላይ የውግዘት ቃል ተላለፈ።
ካህናቱና ዲያቆናቱ ፦ከሆሳዕና ቀን ጀምሮ በደብረ ሰላም ቤተክርስትያን ብቻ የአቡነ ማትያሰን ስም ሳይጠሩ የቀደሱ ካህናትና ዲያቆናት ተወገዙ ልብ በሉ በሌላ ቤተክርስትያን ስም ሳይጠሩ መቀደስ ግን አያስወግዝም ቤተክርስትያን ሁሉንም በእኩል የሚዳኝ አንድ አይነት ህግ ያላት እንጂ አንዱን የሚኮንን አንዱን የሚያጸድቅ ህግ የላትም አለመጥራት የሚያስወግዝ ቢሆን እንኳን አይደለም እንጂ በዓለም ላይ ያሉት ገለልተኞች በሙሉ በተወገዙ ነበር ። ነገር ግን አላማው ጠንካራና ስርአተ ቤተክርስትያንን የጠበቁ ቤተክርስትያንን እየተከታተሉ የማጥፋት ዘመቻ ስለሆነ በደብረሰላም ብቻ ያሉት ተወገዙ ።
ምእመኑ(ህዝበ ክርስትያኑ)፦በዚህች ቤተክርስትያን ውስጥ ቅዳሴ ያስቀደሰ ፣የቆረበ ፣ክርስትና ያስነሳ፣የተዳረ፣ቤተክርስትያን ውስጥ አገልግሎት የሰጠውን ካህን መስቀል የተሳለመ እንዲሁም ማንኛውንም አገልግሎት የተገለገለ በሙሉ ተወገዘ ።

እንግዲህ በኢ/ኦ/ተ/ቤ ስርዓትና ደንብ ውግዘት እንዲሁ በቀላሉ የሚመጣ ነገር አይደለም በጣም ከባድ ነገር ነው እንደው በአሁን ግዜ ግን በጣም ያሳዝናል ። እንደ አንድ ኢ/ኦ/ተ/ቤ ምእመን ሆኜ ስመለከተው አንገቴን እንድደፋ አድርጎኛል። ስለውግዘት በፍትሃነገስት ላይ አንድ ካህን ስለ ሁለት ነገር ይወገዛል እርሱም ቢሆን ተመክሮ አልመለስ ሲል ነው።
በነውር ምክንያት 2. በምንፍቅና (በሃይማኖት ክህደት) ናቸው

እዚህ ግን የሆነው የሊቀጳጳሱን ፍላጎት ስላላሟሉ ለምን ቀደሳችሁ ተብለው ነው የተወገዙት መወገዝ ከነበረባቸውም አንቀድስም ብለው የሄዱት ነበር መወገዝ የነበረባቸው እንዲሁም በፍትሃነገስት ላይ ኤጲስቆጶስ ምዕራፍ 5 ቁጥር 184 ረስጠብ 24<< አንድ ሊቀጳጳስ በቂም በበቀል ቢያወግዝ ከሹመቱ ይሻር በተጓዳኝ የተወገዘው ካህንም ይቋቋመው ነው የሚለው >>።ደግሞ ካህናቱ አጥፍተው ተወገዙ ቢባል እንኩዋን ቤተክርስትያኒቱንና መዕመኑ በምን ጥፋታቸው ነው የሚወገዙት ቤተ ክርስትያን በሄደ ፣ በቆረበ ፣ በአመሰገነ መቼም ይህንን ለቤተክርስትያኒቱ ትልቅ ውርደት ስለሆነ አንድ ሊባል ይገባዋል።



ስቅለት(ዕለተ አርብ)

እነዚህ አማሳኞች ቤተክርስትያኒቱ ተወግዛለች አንሄድም እንዳትሄዱ ብለው ለምእመኑ ቤት ለቤት በመሄድና በስልክ እየደወሉ ይናገሩ ጀመር እዚህ ጋር ልብ ልንለው የሚገባው ነገር በእለተ ሃሙስ ከቅዳሴ በሁዋላ ለካህናቱና ለዲያቆናቱ በደበዳቤ ነው ውግዘቱ የደረሳቸው ታድያ ምነው በዕለተ ዓርብ መጥተው አገለገሉ ። ዕለተ ዓርብ ውግዘቱ ተነስቶ ነበር ወይስ ለእነርሱ የማፍረስ ስራ ሲሆን እንዳይሰራ ቤተክርስትያንን የሚያንጽ ሲሆን ውግዘቱን እንዲሰራ ተደረጎ ነው የተወገዘው ነገሩ እንዲህ ነው ጸሎተ ሃሙስ ዕለት ወደ 300 የሚሆኑ የቤተክርስትያኒቱ አባላቶች እነዚህ አፍራሽ ካህናትና ዲያቆናት በራሳቸው ግዜ በዕለተ ሆሳዕና ስራቸውን እረግጠው ስለወጡ ከዛሬ ጀምሮ የቤተክርስትያናችን አገልጋዮች አይደሉም የሚል በፊረማ የተደገፈ ወረቀት ለዳኛው ስለተሰጠው የአሜሪካን ህግ ደግሞ ተፈጻሚ እንደሚሆን ስለሚያውቁት ሌላ ነገር መፈለግ ነበረባቸው እርሱም፦
ሌላ ቤተክርስትያን
ለቤተክርስትያኑ መገለገያ የሚሆን ነዋያተ ቅድሳት

ስለዚህ አዳራሽ ተከራይተው የትንሳኤን በዓል በአዳራሽ ብለው አወጁ በቤተክርስትያኒቱም ምንም አይነት አገልግሎት አይሰጥም ብለው ምእመኑን ለማወናበድ ሞከሩ እንዲሁም ለእኛ ወፈ ግዝት ለእነርሱ ደግሞ ግዝት የሆነውን ተላልፈው ቤተክርስትያን መጥተው ንዋያተ ቅድሳቱን ዘርፈው ከእንደገና ውግዘቱን አውጀው ላይመለሱ ወጥተው ሄዱ።ከዚህም ቀን ጀምሮ በድምጽም በሁከትም እንደማይሆንላቸው እንዲሁም በመድኃኒዓለም ቸርነትና በምእመኑ ያላሰለሰ ጥረትና ብርታት እንዳልተሳካላቸው ስላወቁት ቤተክርስትያን ለመክፈት አንድ ብለው ጀመሩ።

ሜይ 11 ወሳኙና አሳዛኙ ቀን

ለቤተክርስትያኒቱ በጣም አሳዛኝ ነበር ፤ የፍርድ ቤቱ ዳኛ በተገኙበት ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ ድምጽ ተሰጥቶ የቤተክርስትያኒቱ አቋም የተገለጸበት ቀን ነበር። እዚህ ጋ ሳልጠቅሰው የማላልፈው ነገር ትላንት አባቶች ጳጳሳት ተሰደቡ ብለው ሲናገሩ የነበሩ በዚህ ቀን ከ8 አመት በላይ የማይጠገበውን የቤተ ክርስቲያንን ያሬዳዊ ዜማ ያስተማሯቸውን፣ንስቸውን የተቀበሏቸውን ፣ በእጃቸው የተባረኩት እና የቆረቡትን አባት በአደባባይ መሳደብ የማይረሳና አሳዛኝ ትእይንት ነበር። ይህች ቀን ለአማሳኞቹ የደስታ ቀን ነበር ምክንያቱም ከሆነላቸው ቤተክርስትያኒቱን ከነ ሙሉ ንብረቷ መረከብ ካልሆነላቸው ደግሞ ለሁለት መክፈል ሁለቱም ውጤት ለእነርሱ የአሸናፊነት ነው ። ለቤተክርስትያኒቱ ምዕመን ግን የሃዘን ቀን ነበር ምክንያቱም ሁለቱም ውጤት የሃዘን ነበር ውጤቱ አፍራሾች ቢወስዱት በመንግስት ቁጥጥር ስር አውለው ቤተክርስትያኒቱን ባለቤት አልባ አድርገው የመንግስት ፍላጎት ማስፈጸሚያ ሊያደርጉአት ስለሆነ ውጤቱ በ ተቃራኒውም ቢሆን ከእህት ከወንድሞቻቸው በመለየታቸው ምክንያት የሃዘን ቀን ነበር ያም ሆነ ይህ ውጤቱ የመድኃንያለምና የምዕመኑ ሆነ ቤተክርትያኒቱ በነበረችበት አቋሟ እንድትቀጥል ሆነ ።ቤተክርስቲያኔ ብለው ደፋ ቀና እንዳላሉባት በአፋቸው ሞልተው ለመጥራት እንኳን የሚሳሱላትን ቤተክርስቲያንን ከዚህች ቀን ጀምሮ እንደ ቤተክርስትያን ሳይሆን 4401 ሕንጻ እያሉ የእግዚአብሔርን ቤት ማዋረዳቸውን ቀጠሉ።



ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ለሁለት ተከፈለች ፦ አብዛኛው ምእመን ደብረሰላም መድኃኒዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያንን ይዘው እንደበፊታቸው ሲቀጥሉ በሌላው ወገን ያሉት ደግሞ ጽርሃርያም ቅድስት ስላሴ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ብለው ሌላ ቤተክርስትያን መክፈታቸውን በይፋ አወጁ ሁለቱም በየአሉበት አገልግሎታቸውን ማከናወን ጀመሩ።

ከተከፈሉ በሁዋላ ደብረሰላምን የማዳከሙ ሂደት

ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ከተከፈለችበት ጊዜ ጀምሮ የመድኃኒዓለም ጥበቃ ያልተለያት ቤተ ክርስቲያን በመሆኗ እግዚአብሔር ለራሴ የሚለውን እራሱ በፍቃዱ እያመጣ አገልግሎቱ ከዱሮ በበለጠ እየሰፋ በመሄዱ መንግስት በፖለቲካው ይጠቀምበት የነበረውን አሰራር ማለትም ለመንግስቴ ያሰጉኛል የሚላቸውን ጠንካራ ተቃዋሚዎችን የሚያዳክምበትን አሰራር በቤተክርስትያን ውስጥ በእነዚህ አፍራሽ ሃይሎች አማካኝነት እየተጠቀመበት እንዳለ እናያለን። እስቲ የሚንሶታ ደብረሰላም መድኃኒዓለምን ለሁለት ከተከፈለ በኋላ ለማዳከም የተጠቀሙበትንና እየተጠቀሙበት ያለውን ነገር በዝርዝር እንመልከት
የሚንሶታው ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ቤተክርስትያኒቱ ከተመሰረተች ጀምሮ ላለፉት 19 ዓመት የነበረውና ያለው የሰንበት ትምህርት ቤት መጠሪያ ስም ቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት ነው። አሁን ደግሞ ጽርአርያም ቅድስት ስላሴ ስደተኛው ቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት በማለት ሰይመውታል በጣም የሚገርመው ጽርአርያም ስላሴ ከተመሰረተ ገና አንደኛ አመቱ ሆኖ ሳለ እነርሱ ግን ጽርአርያም ስላሴ ስደተኛው ቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት አስራ ዘጠነኛ አመት ብለው ለሰሚው ግራ የሆነ ዓመታዊ በዓል አክብረዋል እዚህ ጋር ስሙ ላይ ችግር የለበኝም እውነት ለሃይማኖት ከሆነ ቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤት አንደኛ አመት ነበር መባል የነበረበት። ለዚህ ደግሞ የሚሰጡት ምክንያት አብላጫዎቹ ዘማሪዎች ከቤተክርስትያን ስለወጣን ነው ይላሉ ልብ በሉ አብላጫዎቹ ምእመናን አይደለም ያሉት ምእመንም ቢባል እንኳን ስህተት ነው ሰንበት ት/ቤት ከመቼ ወዲህ ነው የግለሰቦች ሆና የምታውቀው ቤተክርስትያን ከ2000 ዘመን በላይ በኖረችበት በታሪኳ የዚህ አይነት ውርደት የቤተክርስትያን ልጆች ነን በሚሉት ልጆቿ ሰንበት ት/ቤት የኛ የተወሰንን ሰዎች ነው የሚል የተነሳባት የመጀመሪያዎቹ ናቸው ቢባል ማጋነን አይሆንም ። የሰንበት ት/ቤቱ ባለቤቶች ነን የሚሉት ደግሞ ሰንበት ት/ቤቱ በደብረሰላም መድኃንያለም ቤተክርስትያን ሲመሰረት እንኩዋን ያልንበሩ ናቸው።ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም ይባል የለ አባቶች ካላችሁ ስደተኛ ሰንበት ት/ቤት በሚንሶታ የተጀመረው በሌላውም እንዳይስፋፋ አንድ ልትሉ ይገባል ጅብ በቀደደው እንዳይሆን ስል የእኔን ሃሳብ እናገራለሁ።የሲኖዶስ መቀመጫ ኢትዮጵያ እንደሆነ ሁሉ የሰንበት ት/ቤቶችም መቀመጫቸው የተመሰረቱበት ቤተክርስትያን ነው የቤዛ ኩሉ ሰንበት ት/ቤትም መቀመጫ በተመሰረተበት ደብረሰላም ቤተክርስትያን ነው እንጂ በሌላ ሊሆን አይችልም።ሰው ይመጣል ይሄዳል እንጂ ሰንበት ት/ቤት ሰው ተከትሎ አይሄድም እንዲሁም ታሪክ ታሪክ የሚባለው ጊዜን እና ቦታን ሲገልጽ እንጂ የሰውን የሙቀት መጠን እየተለካ አይደለም የሚመለከተው አካል ካለ ኅይማኖታዊ ማስተካከያ ሊሰጠው ይገባል።
ደብረሰላም ቤተክርስትያን ውስጥ ያሉት ታቦታት (ሀ)የመድኃኒዓለም (ለ)የኪዳነምህረት (ሓ)የሚካኤል (መ)የገብርኤል ሲሆኑ እነዚህ አማሳኞች የመድኃኒዓለምን ታቦት በማስመጣት ሁለቱ ቤተክርስትያኖች ተለያይተው እንዲቀሩ ምዕመን ከምዕመን እንዳይገናኝ የማድረግ ስራ ሰርተዋል ለቤተክርስትያኒቱና ለህዝበ ክርስትያኑ ቢያስቡ ኖሮ በአንድ ከተማ ውስጥ ያለን ታቦት ባላስመጡ ነበር ። የሌለውን ነበር ማምጣት የነበረባቸው እግዚአብሔርም በአንድነትና በፍቅር እንዲከብር በተደረገ ነበር ። እነዚህ ሰዎች ለስርዓት የሚጨነቁ በማስመሰል በሃይማኖት ሽፋን ነበር ቤተክርስቲያኗን ለሁለት የከፈሏት እነርሱ ግን ዶግማውን እስከማፍረስ ሲደርሱ ተው ያላቸውም የለም ምክንያቱም ደግሞ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን አስተምሮ ስላሴ ማለት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለት ነው መድኃኒዓለም ማለት ወልድ ነው። ሁለቱም አንድ ናቸው ብላ ነው የምታስተምረው እንደ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በስላሴ ታቦት ላይ የመድኃኒዓለም ታቦት አይገባም ምክንያቱም ሁለቱም አንድ ናቸውና በስላሴ ላይ እመቤታችን ፤ጻድቃን፤ ቅዱሳንሰ ናቸው የሚገቡት እንጂ በየትኛውም አስተምሮ መድኃኒዓለም አይገባም እነዚህ አማሳኞች አላማቸው ስለስርአት ጥሰት ሳይሆን የመንግስትን አላማ ማስፈጸም ስለሆነ አስገብተውታል።አራት መለኮት ሊባል ይሆን እግዚአብሔር ይሰውረን አንድ ሊቀ ጳጳስ እንደተናገሩት “እንደዚህ አይነት ድርጊት አራት አምላክ አለ ብለን እንደ ማመን ነው የሚቆጠረው ይህ አይነት ድርጊት በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ ቢቀርብ እና ቢታይ ጵጵስናን እስከ ማሻር እንደሚደርስ” ገልጸዋል ። በመቀጠልም ለምእመኑ ለገብርኤል ንግስ መድኃኒዓለም ሄደው እንዳያነግሱ ከዚህ በፊት ዞር ብለው አይተውት የማያውቁትን የኤርትራ ገብርኤል ቤተክርስትያን ሄዳችሁ አንግሱ ብለው ለህዝቡ አስታወቁ ሔደውም አንግሰው ጥሩ ቀን እንዳሳለፉ ገለጹ እውነት ንግሱን ፈልገው ቢሆን ችግር አልነበረውም ነገር ግን ደብረሰላም መድኃኒዓለምን ለማዳከም የተደረገ ነው። እንጂ የሚደረገው ስራ አሁንም አላቆመም የቤተክርስቲያኗ አባት ከኢትዮጵያ የሚካኤልንም ታቦት ይዘው መጥተዋል። የሚቀራቸው የገብረኤል እና የኪዳነምህረትን ታቦት ነው ወደፊት ምን እንደሚሆን እናያለን፤ ስለዚህ ምእመናን ሆይ ይህ አስተምሮ የኢ/ኦ/ተ/ቤ አስተምሮ እንዳልሆነ ልንገነዘብ ይገባል ዝም ብለን ተከታዮች ከምነሆን ቆም ብለን ልናስብ ይገባናል በተለይ ደግሞ ጉዞ ወደ እናት ቤተ ክርስትያን(እንቀላቀል) የሚለው ስሙ እና ከእላዩ ሲታይ መልካም የሚመስለልና የሃይማኖት ሽፋን ያለው ውስጡ ግን ዶግማውን የሚንድ የዘመናችን የቤተክርስትያን ፈተና አስተምሮው የቤተክርስትያን ያልሆነ የመንግስትና የእነርሱን ተልኮ ለማስፈጸም የሚሮሯሯጡ ሰዎች ያስገቡብን ስለሆነ በእውነተኞቹ የቤተክርስትያን አባቶች እርምት ሊወሰድበት ይገባል። ምዕመናንም ማንም ተነስቶ ቤተክርስትያንን አንድ ላደርግ ነው ተከተሉኝ ቢል ልንከተለው አይገባም የበላይ አካል የሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠውን መመሪያ ብቻ ነው መከተል ያለበን። የቤተክርስቲያንም ክብር ሊጠበቅ ይገባል።

3 ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን ለምዕመኖቿ ወንጌልን ለማስፋፋት በምታደርገው መምህራንንና ዘማርያን ከተለያዩ ደብራት የምትጋብዛቸውን እየተከታተሉ ደብረሰላም መድኃኒዓለም ብትሄዱና ወንጌልን ብታስተምሩም ሆነ ብትዘምሩ ትወገዛላችሁ በማለት በማስፈራራት እንዲሁም አቡነ ዘካርያስ እዚያ ቤተክርስትያን አወግዝሃለሁ በሚል ማስፈራርያ ለመምጣት የአየር ትኬት ከተቆረጠላቸው በሁዋላ በዛቻው ምክንያት የሰረዙ መምህራን እንዳሉ በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ ለዚህ ደግሞ ኤጲስቆጶስ አንቀጽ 5 ቁጥር 182 እንዲህ ይለናል <<ፈጽሞ ቂመኛ የሆነ ወይም በየጊዜው ሁሉን እስከማሰርና እስከ ማውገዝ ድረስ ፈጥኖ ለማውገዝ ቂሙን የማይረሳ ቢሆን ይሻር >> ይለናል እንዲሁም ምንም እንኳን ቤትክርስትያን የሰጠቻችሁ ሃላፊነት ቢሆንም ይህንን ሁሉ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ተቋቁማችሁ ሃይማኖታዊ ግዴታችሁን ለተወጣችሁ ሰባክያንና ዘማርያን በሃያሉ በመድኃኒዓለም ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ሽልማት

እንግዲህ እንደሚታወቀው ከዋልድባና ከመሳሰሉት ታላላቅ ገዳማትና አድባራት የመጡ አባቶች ተገፍተው፤ ተበድለው፤ፍትህ አጥተው፤ ቤተክርስትያን ሲቃጠልባቸው፣ ሲፈርስባቸው አቤት ለማለትና ለማሳወቅ በአሁን ግዜ ወደ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቢሮ ለመግባት በፍጹም ዝግ በሆነበትና በማይቻልበት ሁኔታ እንዲሁም ደግሞ በሌላ በኩል የመንግስት ጉዳይ አስፈጻሚዎች የቤተክርስትያን አፍራሽ ሃይሎች ለእነርሱ ደግሞ ክፍት ሆኖ እንደፈለጉ የሚወጡበትና የሚገቡበት በሆነበት በአሁን ጊዜ የሚንሶታው ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አፍራሽ ሃይሎች እንደ ፈለጉ ሲወጡና ሲገቡ እንዲሁም ላደረጉት(ላበረከቱት) ቤተክርስትያንን የመክፈል ስራ ሽልማታቸውን ከአቡነ ማትያስ ጋር ፎቶ በመነሳት አሳይተውናል።

ማጠቃለያ

እንግዲህ ይህ ሁሉ ሲፈጸም እነዚህ ቤተክርስትያንን በማፍረስ(በመክፈል) ላይ የሚገኙ አማሳኞች እራሳቸውን ንጹህ፣ ቅዱስ ፣ጻድቃን ፣ሃይማኖተኞች በማድረግ ሌላውን ለማዳከምና ለማፍረስ የሚፈልጉትን ቤተክርስትያንና ምእመናንን ፖለቲከኛ ፣ሃጥያተኛ ፣ በማድረግ በድፍረት የናገራሉ እንዲሁም ከእነርሱ ጋር የሚሰሩትን ጳጳሳት ትክክለኛ ናቸው ሲሉ የእነርሱን ሃሳብ የማይደግፉትን ፣የሚያስታርቁትን፤የሚመክሩትን ያውም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑትን እውነተኛ አባቶችን ይሳደባሉ፤ያንቋሽሻሉ ትክክለኛ አባት እንዳልሆኑ ለደጋፊዎቻቸውና ለምእመን ይናገራሉ ደግሞ ልዩ መለያቸው ዓይን ያወጣ ውሸት ነው ።ይህን ደግሞ በሚንሶታ ደብረሰላም መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን አይተነዋል።

እንግዲህ ውድ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን ምዕመን ሆይ አንድ ልናጤነው የሚገባ በአሜሪካን አገር በሲኖዶስ ስር ነን የሚሉት በሙሉ በስም ብቻ በሲኖዶስ ስር ነን ይላሉ እንጂ አንድም ቅዱስ ሲኖዶስ የአዘጋጀውን መመሪያ ማለትም ቃለ ዓዋዲ ተግባራዊ የሚያደርግ የለም የሲኖዶሱን መመሪያ ተግባራዊ ሳያደርጉ (በሲኖዶስ ማዕቀፍ) ውስጥ ሳይገቡ ሌላውን መወንጀል ከፈረሱ ጋሪውን ማስቀደም ነው እንዲሁም ለግለሰቦች መጠቀሚያ መሆን እንጂ ለቤተክርስትያኒቱ የሚያስገኘው ነገር ስለሌለ እርምት ሊወሰድበት ይገባል። ደግሞም ቅዱስ ሲኖዶሱ ከስርአት ውጭ ነው ብሎ ምንም አይነት ተግሳጽም ሆነ ውግዘት ያላደረገበትን ቤተክርስትያን እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔን የሚጠይቅ ጉዳይ አንድ ጳጳስ በግሉ ተነስቶ ሊለየው (ሊያወግዘው) አይችልም ተቀባይነትም አይኖረውም እንደውም ቅዱስ ሲኖዶሱ ስርአትን በመጠበቃቸው የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያንን ቀኖናና ዶግማ በመከተላቸው ህዝበ ክርስትያኑን በደንብ በስርአትና በኃይማኖት መምራት ይችላሉ ብሎ፦
አቡነ ዳንኤልን ከሚንሶታው ደብረሰላም መድኃኒዓለም ገለልተኛ ቤተክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶሱ ለጵጵስና ሲሾማቸው እንዲሁም
አቡነ ፋኑኤልን ከዲሲ ሚካኤል ገለልተኛ ቤተክርስትያን ያን ቅዱስ ሲኖዶሱ ለጵጵስና ሲሾማቸው እነዚህ ስርአት አስከባሪዎቹ የት ነበሩ ?

ቅዱስ ሲኖዶስ ከገለልተኛ ቤተክርስትያን እየጠራ ሹመትን ሰጣቸው እንጂ አልለያቸውም ቅዱስ ሲኖዶስ ሲሾም ሌላው የቅዱስ ሲኖዶስ የበላይ ሆኖ ሊያወግዝም ሆነ ሊለይ እንደማይችል ለመግለጽ እወዳለሁኝ ስለዚህ በአሁን ግዜ እንደወረርሽኝ እየተስፋፋ የመጣውን ጉዞወደ እናት ቤተክርስትያን(እንቀላቀል)የሚለው የተሞከረባቸውን የተለያዩ አብያተ ክርስትያናትና ምእመናን ላይ ያስከተላቸውን ችገሮች ስንመለከት እንኩዋን አንድነትን ሊያመጣያ ቀርቶ በአንድነት የነበሩትን ምእመናን የበተነ፣ዘመዳማቾችን የለያየ ፣ባልና ሚስትን ያለያየ ፣በኢኮኖሚና በማህበራዊ ምዕመኑን ያቃወሰ እነዲሁም ስለቤተክርስትያን በጋራ ሆኖ ይሰራና ይነጋገር የነበረውን እንዳይሰራና እንዳይነጋገር ያደረገ ነው። ስለዚህ ማንኛውም የኢ/ኦ/ተ/ ቤተክርስትያን አማኝ ሊያደርገው የሚገባው ጥንቃቄ ማንም ተነስቶ እንቀላቀል ቢል ቤተክርስትያንን የሚያፈርሱና የሚያዳክሙ አማሳኞች መሆናቸውን ማወቅ አለብን ይህ ጉዳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የሚጠይቅ ስለሆነና ማንም ጳጳስም ሆነ ፓትርያርክ በግል የሚጽፉት ደብዳቤም ሆነ መልእክት የቤተክርስትያን ድምጽ አለመሆኑን በማወቅ ልንቃወመው ይገባል የቤተክርስትያን የበላይ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ ከቅዱስ ሲኖዶስ የሚመጡት መልእክቶች ብቻ የቤተክርስትያን ድምጽ መሆናቸውን መረዳት ይኖርብናል ።

በመጨረሻም በመንግስት የምትመኩ ፤በዘርና በጎሳ የተመካችሁ፤ በስልጣን ጥማት የሰከራችሁ፤በፍቅረ ነዋይ የታወራችሁ፤ክርስቶስን የማታውቁ ግን የክርስቶስ አገልጋዮች ነን የምትሉ በሙሉ ቤተክርስትያንን በማወክና ሰላሟን በማደፍረስ በመክፈል እንዲሁም በማዳከም ላይ የተሰማራችሁ ጳጳሳት ፤ካህናት፤ዲያቆናት ፤ግለሰቦች እስቲ ለአንድ ሰከንድ ቆም ብላችሁ የተሰቀለውን ክርስቶስን አስቡት ያን ግዜ እውነትን ታይዋታላችሁ እውነት ደግሞ የተሰቀለው ክርስቶስ እንጂ መንግስት አይደለም መንግስትም ይቀየራል፤ስልጣንም ይቀራል፤ገንዘብም ይጠፋል ሁሉም ያልፋል የማያልፈው እውነት ብቻ ስለሆነ ስለ እውነትን መስክራችሁ ሰማእት ለመሆን ሞክሩ።ከቻላችሁ እውነትን ተናገሩ ካልቻላችሁ ሃሰትን አትናገሩ ይህንንም ካልቻላችሁ ዝም በሉ።

ስለ እውነት ምንነት ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ ከጻፉት ላይ በማቅረብ ጽሁፌን ልደምድም

እውነት ማለት የኔ ልጅ

እውነት ጽድቅ እንዳይመስልሽ ኩነኔ ነው እውነት ያማል

አይታከሙት ደዌ ያከሳል ያጎሳቁላል

ሁሌ አያስከብርሽም አንድ አንዴ ህይወት ያስከፍላል

ልጄ እውነት ከህይወት ይከብዳል

በመኖር ከህይወት ተገኝቶ መልሶ ህይወት ይበላል ።

__

<< እግዚአብሄር አምላክ ፍቅርን ይስጠን >>


wanted officials