Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, October 5, 2015

ድምፃዊ ቡዝአየሁ ደምሴ በካናዳ በጠርሙስ ተፈንክቶ አዳጋ ደርሶበታል።







ድምፃዊ ቡዝአየሁ ደምሴ በካናዳ በጠርሙስ ተፈንክቶ አዳጋ ደርሶበታል። «ወደ መድረክ ለመምጣት ዘገየህ» በሚል ከአንድ ታዳሚ በተወረወረ ጠርሙስ የተፈነከተው ቡዜ ዝግጁትን በማቋረጥ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ እንዲታከም ተደረጓል። ደም በከፍተኛ መጠን ፈሶታል፣ ጉዳቱም አስከፊ ነበር። ከዚህ ቀደም ቴዲ አፍሮ በእስራኤል «ለምን ዘገየህ» በሚል ተመሳሳይ ተቃውሞ እንደገጠመው ይታወሳል። ድምፃዊያኑ ከተመልካቹ ጋር ቅራኔ ውስጥ የሚከቱት አዘጋጆች ናቸው።

 ተመልካች በብዛት እስኪመጣ ሰዓቱን ያዘገያሉ። ተጨማሪ ገንዘብ ለመሰብሰብ በሚል… ታዳሚው ደግሞ ከድምፃዊያኑ ጋር ፀብ ውስጥ ይገባል። የተፈጠረው ነገር ያሳዝናል። ብዝአየሁ ደምሴን በቅርብ አውቀዋለሁ። ሲበዛ ጨዋ፣ ሲናገር በዝግታና ሰው አክባሪ እንዲሁም ትሁት ነው። በጭራሽ ለዱላ የምታስበው አይደለም። ደግሞስ በሰለጠነ ሀገር ተቀምጦ መፈንከትን ምን አመጣው?..መቼ ይሆን ስልጣኔ የሚገባን!?.. በአደጋው ምክንያት የአውስትራሊያ ዝግጅቱን መሰረዙን ሰምቻለሁ።

እየሩሳለም አርአያ

No comments:

Post a Comment

wanted officials