Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, October 7, 2015

ሰራተኞቻቸውን ለማባረር የተስባሰቡ ባለሰልጣናት በሰራተኞቻቸው “እርቃናቸውን” ተባረሩ









ከታምሩ ገዳ

በአለማችን ላይ በከፍተኛ ደረጃ እየጨረ የመጣውን የነዳጅ ፍጆታ ፣ አለም አቀፍ ውድድር መቋቋም የተሳነው እና በተለያዩ የሰራ አድማዎች ሲናጥ የነበረው የ ፈረንሳዪ አየር መንገድ (Air France) በመጪው ሁለት አመታት ውስጥ 1700 ግራውንድ ስታፎች፣ 900 ካቢን ክሮዋች እና 300 ፓይለቶችን ጨምሮ ወደ 2900 የሚሆኑ ሰራተኞቹን ለማባረር መወሰኑን ይፋ ያደርጋል።ታዲያ የ ማንጅመንቱ አባላት ሰኞ እለት ከፓሪስ ከተማ አቅራቢያ ከሚገኘው የቻርልስ ደጎል አለማቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ ካለው የድርጅቱ ዋና ጽፈት ቤ/ት ተሰባሰበው ሰለ መጪው ጊዚያት ሰመክሩ እና ሲወያዩ ሳለ የመባረሩ ዜናው ያሰቆጣቸው በ 100 የሚቆጠሩ የሰራተኛ ማህበር ሃላፊዎች እና አባላት ከሰብሰባው አዳራሽ ዘልቀው በመግባት ዋናው ሰራ አስኪያጁ ፈሪዲሪክ ጋጂይ ሲያመልጡ ዛቪየር ብሮስቲያ የተባሉት የሰራተኞች ቅጥር ዋና ሃላፊውን ጨምሮ የተወሰኑ የማናጅመንት ሃላፊዎችን እየተከታተሉ መቃወም ፣መጥለፍ እና መጎነታተል ይጀምራሉ። ታዲያ እኛ በሰራተኞቻቸው መገፈታተር እና ጃኬቶቸው እና ሸሚዞቻቸው መቦጫጨቅ ያሰጋቸው ዛቪየር እና ጓደኞቻቸው እግሬ አውጪኝ በማለት በ ትልቅ አጥር ላይ ተንጠልጥለው ለማምለጥ ቢሞክሩም ያ ቀይ ምንጣፍ እና ተሽከራክሪ ወንበርን የለመደ ሰውነታቸው አሻፈረኝ በማለቱ በጠባቂዎቻቸው እገዛ (አጥሩን ዘለው ) ለጊዜው ሕይወታቸውን አተርፈዋል፡፡ ከሁኔታው አደገኛነት ሳቢያ ባለሰልጣናቱ መሮጣቸው በጀ እንጂ ሕይወታቸውን ጭምር ያጡ ነበር ተብሏል ።ከዚሁ ቁጣ ጋር በተያያዘ ከሰባት በላይ ሰዎች( የጥበቃ አባላትን ጨምሮ ) ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ሁኔታው ያሰደነገጣቸው የፈረንሳይ መንግስት ባለሰልጣናትም አይር መንገዱ ከፈተኛ አደጋ ውስጥ መሆኑን ጠቅሰው እርምጃውን በማውገዝ ድርጊቱን የፈጸሙ ግለሰቦች ምንም አይነት የሕግ ከለላ(ተቀባይነት) አንደማይኖራቸው የገለጹ ሲሆን ጉዳዩ ተጣርቶ ተጠረጣሪዎቹ ባስቸኳይ ለፈርድ ይቀርቡ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል። በ1933አኤአ የተቋቋመወ የፈረንሳይ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት ከ 52 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ይህ እድሜ ጠገብ እና ገናና አይር መንገድ ብዙ ኪሳራዎች ሰለበዙበት ከሆላንዱ (KLM) አይር መንገድ ጋር በመቀናጀት በአለም 5ኛው ትልቁ አይር መንገድ ለመሆን ቢቋምጥም አመርቂ መፍትሄ በመጥፋቱ ከገበያ ውስጥ ለመቆየት ሲባል 5 የበረራ መሰመሮቹን ለመዝጋት እና 14 ግዙፍ እና አሕጉር አቋራጭ አውሮፕላኖቹን ለመሸጥ እቅድ አውጥቷል።
በነገራችን ላይ በፈረንሳይ ውስጥ በሰራተኞች እና በማናጅመንቱ መካከል ችግሮች ሲከሰቱ ከፍተኛ አለቆችን በመያዣነት አገቶ መደራደር የተለመደ(French Style) ነው ቢባልም ብዙዎቹ የመንግስት ባለስልጣናት(ፕ/ት ሆላንዴ ጨምሮ) ግን የአገሪቱ ሰንደቅ አላማን በአለም ላይ በሚያውለበልበው የፈረንሳይ አየር መንገድ (Air France )ከፍተኛ ባለሰልጣናት ላይ የተፈጸመው የሰሞኑ ድርጊት እና የብዙ ጋዜጦች የፈት ለፊት ዜና ማጣፈጫቸው መሆኑ “ብሄራዊ ውረደታችን ነው” ብለውታል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials