Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, October 14, 2015

ሰበር ዜና የወያኔ ሰራዊት ለበተንቸሮ ላይ በግፍ ታረደ!!







ሰበር ዜና
የወያኔ ሰራዊት ለበተንቸሮ ላይ በግፍ ታረደ!!
የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት መንግስትን የገንዘብ ጥማት ለማርካት ሲባል ብቻ ወደ ሶማሌያ የተላከዉ የወያኔ ሰራዊት ከሳምንት በፊት ልዩ ስሙ ለበተንቸሮ ተብሎ በሚጠራዉ ከአሚሶም ወይም ከአፍሪህብረት ተብዬዉ ሰራዊት ክልል ዉጭ ጥቃት ለማድረስ ተንቀሳቅሶ የነበረ ሲሆን ከሰራዊቱ መካከል በተማረኩት 3 ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችን ላይ አሰቃቂ ግድያ ተፈጸመባቸዉ።
አልሸባብ እየተባለ የሚጠራዉ ቡድንና የወያኔ ቡድን በሚያደርጉት በዚህ ጦርነት ዉስጥ ጭቁኑ የህዝብ ልጅ! የኢትዮጵያ ትዉልድ! እንደበግ እየታረደና በመኪና እየተጎተተ የመኪና ጎማ ስር ተንጋሎ ደሙ እንደ አልባሌ ሲወርድ ማየት ያሳዝናል!! ሲሉ መረጃዉን የላኩልን የኮነሬል የማነ ግ/ማርያም ዉስጥ አዋቂ ምንጫችን ገልጸዋል፤፤
በለበተንቸሮ ተደርጎ በነበረ የማጥቃት እርምጃ ወቅት ኪሳራ የደረሰበት ወያኔ ከተማረኩት ወታደሮች መካከል ሁለቱ አንገታቸዉን ተቀልተዉ ከተገደሉ በኋላ በመኪና እየተጨፈለቁ ለሌሎች ትእይንት የተደረጉ ሲሆን ሌላ አንድ የ24 አመት ምርኮኛ ከነህይወቱ በመኪና እየተጎተተ ስጋዉ እስኪላቀቅና አጥንቱ እስኪደቅ በስቃይ እንዲሞት ሆኗል።
የህዝብና የሐገራችን ጠላት የሆነዉ ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት በየወቅቱና በየጊዜዉ ባገኘዉ አጋጣሚ ሁሉ ወገኖቻችንን በማስጨረስ የሰራዉን እና እየሰራ ያለዉን ግፍ ለመበቀል መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ከህዝብ አብራክ የወጣህዉ የመከላከያ ሰራዊት ከህዝብ ጎን በመቆም በአንድነት በወያነ ጎጠኛ ቡድን ላይ አፈ ሙዙን እንዲያዞር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!
ወያኔ ይዉደም!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

ጉድሽ ወያኔ

No comments:

Post a Comment

wanted officials