Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, October 5, 2015

የጅቡቲ ፐሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ኤርትራን ኤርትራን ከሰሱ


67782785-1095-4D77-8A1C-68A778F608D4_w640_r1_s
ሰሎሞን አባተ – ኒው ዮርክ
የጅቡቲ ፐሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ኤርትራን ባልተገባ ባሕርይና በነገረኛነት ከስሰዋል፡፡ ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር ፕሬዚዳንቱ ይህንን ክሣቸውን ያሰሙት ፕሬዚዳንት ጌሌ “ኤርትራ ለአካባቢውና በአጠቃላይም ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ አደጋ ነች” ብለዋል፡፡
በአውሮፓ አቆጣጠር ከ2008 ዓ.ም አንስቶ የኤርትራ ወታደሮች የሰሜናዊ ግዛቶቻቸውን አንዳንድ አካባቢዎች ያለአግባብ ከተቆጣጠሩ በኋላ በዚህም ዓመት ውጥረትና ውዝግቡ መቀጠሉን የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ተናግረዋል፡፡ የመንግሥታቸው ባለሥልጣናትና እራሳቸውም በተደጋጌሚ ጉዳዩን ለማስረዳት ወደ ኒው ዮርክ መመላለሳቸውን አመልክተዋል፡፡
የኤርትራና የጅቡቲ ካርታሃገራቸው በሰላም፣ በሽምግልናና በድርድር እንደምታምን የተናገሩት ፕሬዚዳንት ጌሌ “የተክለ ግዛታችን የማይደፈር መሆን ግን ለድርድር የሚቀርብ አይደለም” ብለዋል፡፡ የኤርትራ መንግሥት ቀደም ሲል ባወጣው መግለጫ “የአካባቢው ብቸኛና ዋነኛ ያለመረጋጋት ምክንያት የኤርትራን ሉዓላዊ ግዛቶች በኃይል ይዛ ያለችው ኢትዮጵያ ናት” ብሏል፡፡ ከጅቡቲ ጋር የገቡበት የድንበር ውዝግብ ጉዳይ በጋራ ለተስማሙባቸው ሦስተኛ ወገን አካላት የቀረበ መሆኑን የኤርትራ መንግሥት ባለፈው የካቲት መጀመሪያ አውጥቶት በነበረ መግለጫ ተናግሮ የነበረ ሲሆን ንግግሩ በጥሩ ሁኔታ ተይዞ እያለ ብስለት የሌለውና በጎ መንፈስ የራቀው የጅቡቲ አቋም ለማስረዳት አስቸጋሪ ነው ብሏል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰባኛ ጠቅላላ ጉባዔ ያደረጉትን ንግግር ለመስማት ከዚህ ሥር ያለውን ማገናኛ ተጭነው ይከተሉ፡፡
Source -VOA

No comments:

Post a Comment

wanted officials