Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, October 15, 2015

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ተባለ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ተባለ
የ18 ዓመት እስር ተበይኖበት ከ4 አመታት በፊት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የወረደው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ አያያዝ አሳሳቢ መሆኑ እየተነገረ ነው፡፡
‹‹እስክንድር ነጋ መጽሐፍ ቅዱስን ጨምሮ ምንም አይነት መጽሐፍ እንዳያነብ ተከልክሏል፡፡ ከባለቤቱ ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል እናትና ከአንድ የቅርብ ዘመዱ ውጭ ማንም እንዳይጠይቀው ታግዷል፡፡ እስክንድር ከአንድ ሰፊ ግቢ ውስጥ ከአምስት ሰዎች ጋር ብቻ ነው የታሰረው፡፡ ማንም ጋር አይገናኝም፡፡ መቀመጫ ወንበሩ ተወስዶበት የቆሻሻና ውሃ ማጠራቀሚያ የነበረ ባልዲን ባፉ ደፍቶ ጨርቅ ደልድሎ ነው ለመቀመጫነት የሚጠቀመው›› ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የእስክንድር ነጋ የቅርብ ሰው ለቀለም ቀንድ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 21 በጥበቃ ሥር ያሉና በፍርድ የታሰሩ ሰዎች ሰብኣዊ መብታቸው የመጠበቅ መብት እንዳላቸውና ከትዳር ጓደኞቻቸው፣ ከቅርብ ዘመዶቻቸው፣ ከጓደኞቻቸው፣ ከሀይማኖት አማካሪዎቻቸው፣ ከሀኪማቸው፣ ከህግ አማካሪዎቻቸው ጋር ለመገናኘትና እንዲጎበኟቸውም መብት እንዳላቸው ይደነግጋል፡፡
(የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ቅጽ 3 ቁጥር 12)

No comments:

Post a Comment

wanted officials