ኤርትራ ዝቅተኛ የኢንተርኔት ተጠቃሚ በመሆን አለምን ትመራለች፡፡
በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ የሆነው ከአጠቃላዩ ህዝብ 1.7 በመቶ የሚሆነው ብቻ ነው መባሉን የአሜሪካው የቢዝነስ መጽሄት ፎርቹን ዘገበ፡፡
ኢንተርኔት ላይቭ ስታትስ የተባለው አለማቀፍ ተቋም ያወጣውን መረጃ ጠቅሶ ዘገባው እንዳለው፣ እጅግ ዝቅተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት አቅርቦት ካላቸው አስር የአለማችን አገራት መካከል ስምንቱ በአፍሪካ አህጉር እንደሚገኙና ኢትዮጵያም አንዷ እንደሆነች በጥናት ተረጋግጧል፡፡
በኢንተርኔት አገልግሎት አቅርቦት ዝቅተኛነት ከአለማችን ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዘው ኤርትራ መሆኗን የጠቆመው ዘገባው፣ ከአገሪቱ ህዝብ የአገልግሎት ተጠቃሚ የሆነው 0.91 በመቶ ብቻ መሆኑን ገልጧል፡፡
ከአውስትራሊያ በስተሰሜን የምትገኘው ቲሞር ሌሴቴ ደሴት በ1 በመቶ፣ ማይንማር በ1.16 በመቶ፣ ብሩንዲ በ1.39 በመቶ እንዲሁም ሴራሊዮን በ1.49 በመቶ በኢንተርኔት አቅርቦት ዝቅተኛነት እስከ አምስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል ተብሏል፡፡ ሶማሊያ በ1.51 በመቶ፣ ኒጀር በ1.61 በመቶ፣ ኢትዮጵያና ጊኒ በ1.7 በመቶ እንዲሁም ኮንጎ በ1.92 በመቶ እንደሚከተሉም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡
ምንጭ፤- አዲስ አድማስ
No comments:
Post a Comment