Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, October 28, 2015

5 ብሔር ተኮር ነፃ አውጪ ግምባሮች በጋራ የነፃነት እና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መሠረቱ



(ዘ-ሐበሻ) በኦስሎ ኖርዌይ ከኦክቶበር 22 እስከ ኦክቶበር 23, 2015 ዓ.ም በተደረገ የጋራ ጉባኤ 5 የኢትዮጵያ የብሄር ድርጅቶች በጋራ ለመታገል አዲስ ንቅናቄ መመስረታቸውን ለዘ-ሐበሻ በላኩት መግለጫ አስታወቁ::

ጥምረቱን የመሰረቱት የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የጋምቤላ ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግምባር; የኦሮሞ ነፃነት ግምባርና የሲዳማ ብሔራዊ ነፃነት ግምባር ሲሆኑ የኢትዮጵያ ያለውን ስርዓት በጋራ ጥለው የሁሉንም ብሄሮች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት የሚያከብርና የአንድን ቡድን የበላይነት እንዲያበቃ የሚያደርግ ስርዓት ለመፍጠር እንደሚታገሉ በመስራች ጉባኤያቸው መጨረሻ ላይ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል::



ሃገሪቱን ወደ ተሻለ የፖለቲካ ሽግግር ቀርጸው ለመንቀሳቀስ የተሰማሙት እነዚሁ 5 ድርጅቶች የአዲሱ ጥምረታቸው መጠሪያ የሕዝቦች ጥምረት ለነፃነትና ለዴሞክራሲ (Peoples Alliance for Freedom and Democracy (PAFD) ተብሎ ተሰይሟል::

(በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተሰጠውን መግለጫውን ለማንብብ እዚህ ይጫኑ)

አርበኞች ግንቦት በቅርቡ ከአማራው ንቅናቋ; ከአፋር ንቅናቄና ከትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጋር በጋራ ለመታገል ጥምረት መፍጠሩ ይታወሳል:: ትናንት በኖርዌይ ጥምረታቸውን ያወጁት የቤኒሻንጉል ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የጋምቤላ ነፃ አውጪ ንቅናቄ; የኦጋዴን ነፃ አውጪ ግምባር; የኦሮሞ ነፃነት ግምባርና የሲዳማ ብሔራዊ ነፃነት ግምባር ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ወደፊት ስለሚፈጥሩት የጋራ ጥምረት ወይም ግንኙነት ይኑራቸው አይኑራቸው የተገለጸ ነገር ባይኖርም በቅርቡ ወደ ሚኒሶታ የመጡት የንቅናቄው የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ነአምን ዘለቀ “ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንዳለች እስካመኑ ድረስ ከሁሉም ጋር በጋራ ለመስራት እንችላለን::” ማለታቸውን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::

No comments:

Post a Comment

wanted officials