Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, October 7, 2015

የኃይለማርያም ካቤኔ አባላት ታወቁ * ሬድዋን ወደ ወጣቶች እና ስፖርት ሚ/ር ተገፉ * ሶፍያን አህመድ ተሰናበቱ * ሕወሓት አሁንም የአንበሳውን ድርሻ ይዟል

የሕዝብ ተወካዮች የሌሉበት የኢህ አዴግ ፓርላማ ዛሬ ተሰብስቦ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ያቀረቡትን የካቢኔ አባላት አጸደቀ:: በዚህ ካቢኔ ውስጥ አሁንም ሕወሓት ዋና ዋና የስልጣን ቦታዎችን ይዟል:: የውጭ ጉዳይ ሚኒስተርነቱ; ኢኮኖሚው በሕወሓት ስር እንዲቆይ ሲደረግ አሁን ደግሞ በተጨማሪም አቶ ሬድዋን ሁሴን ይመሩት የነበረውን የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር ቦታም ወስዷል:: በዚህም ቦታ ላይ የሕወሓቶ አቶ ጌታቸው ረዳ ተሹመዋል:: ለረዥም ጊዜ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ሁነው ሲሰሩ የቆዩት አቶ ሶፍያን አህመድ በአቶ አብዱላዚዝ መሀመድ ተተክተዋል::

የሕወሓቱን የካዛንቺሱን መንግስት የሚላላኩት የካቤኔ አባላቱ ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል::
አቶ ደመቀ መኮንን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ
ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል – በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
ወይዘሮ አስቴር ማሞ – በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ እና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር
አቶ ሲራጅ ፈጌሳ – የመከላከያ ሚኒስትር
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም – የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
አቶ ካሳ ተክለብርሃን – የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር አካባቢ ልማት ሚኒስትር
አቶ ጌታቸው አምባዬ – የፍትህ ሚኒስትር
አቶ አብዱላዚዝ መሀመድ – የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር
አቶ ተፈራ ደርበው – የእርሻ እና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሚኒስትር
አቶ ስለሺ ጌታሁን – የእንሰሳትና የዓሳ ሀብት ልማት ሚኒስትር
አቶ አህመድ አብተው – የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
አቶ ያዕቆብ ያላ – የንግድ ሚኒስትር
አቶ አብይ አህመድ – የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
አቶ ወርቅነህ ገበየሁ – የትራንስፖርት ሚኒስትር
አቶ ሙኩሪያ ሀይሌ – የከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስትር
ዶክተር አምባቸው መኮንን – የኮንስትራክሽን ሚኒስትር
አቶ ሞቱማ መቃሳ – የውሃ፣ መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር
አቶ ሽፈራው ሽጉጤ – የትምህርት ሚኒስትር
አቶ ቶሎሳ ሻጊ – የማዕድን፣ የነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትር
ዶክተር ከሰተብርሀን አድማሱ – የጤና ጥበቃ ሚኒስትር
አቶ አብዱልፈታህ አብዱላሂ – የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
ኢንጂነር አይሻ መሀመድ – የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
ወይዘሮ ዘነቡ ታደሰ -የሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ሚኒስትር
ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም – የአካባቢ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር
አቶ ሬድዋን ሁሴን – የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስትር
ወይዘሮ ደሚቱ ሀምቢሳ – የመንግስት የልማት ድርጅቶች ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚኒስትር ማዕረግ የካቢኒ አባል የሆኑ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ሹመትን ለምክር ቤቱ አቅርበው አስፀድቀዋል።
በዚህም መሰረት
አቶ በከር ሻሌ – የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬከተር
አቶ ጌታቸው ረዳ – የመንግስት ኮሙዩንኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ ሚኒስትር
አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ – የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
ዶክተር ይናገር ደሴ – የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials