ሰሞኑንን ከወደ ምእራብ አፍሪካዊቷ ናይጄሪያ የተሰማው አሰገራሚ ዜና በዙዎችን ወቸው ጉድ! ፣ምን አይነት ዘመን ላይ ደረሰን? ማለቱ አይቀረም። የአገሪቱ ጸረ -የአደንዛዥ እጽ እና የሀገወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪዎች ግበረ ሃይል ሰሞኑን ከመዲናይቱ ሌጎስ አይሮፕላን ጣቢያ አቅራቢያ ከሚገኝ አንድ ዘመናዊ ሆቴል ውስጥ ድንገተኛ አሰሳ ሲያደረግ ከሆቴሉ አንደኛው ክፍል ውስጥ የተሰባሰቡ ፣ እንግዳ እና ያለተለመደ በሆነ ሰራ ተጠምደው ከነበሩ ሰደስት ግለሰቦች ጋር ይፋጠጣል።
አንድ የወጪ ገንዘብ ምንዛሬ ቤሮ ሰራተኛ ( Burea De Change operator ) እና የሆቴል ቤቱ ዋና ሰራ አስኬያጅ ጨምሮ ሰደሰቱ ሰዎች ግምቱ 156 ሺህ ዶላር ወይም 32 ሜሊዮን ኒየራ(የአገሪቱ ሕጋዊ ገንዘብ ነው ) በኢትዮጵያ ብር ደግሞ( ወደ3 ሚሊዮን 120 ሺህ ብር) የሚገመት ገንዘብ እጅግ ፕሮፊሽናል በሆነ ሰው አማካኝነት በመጠቅለል እና በመዋጥ ከሆድ እቃቸው ውስጥ በማኖር በሁለት የ ብራዚል ዜግነት ባላቸው ተጠርጣሪዎች አቀናባሪነት ገንዘቡን ወደ ብራዚል ለማሸጋገር ሲጣደፉ “ደረሼባቸዋለሁ” ሲል ፖሊስ ተናግሯል።
እንደ መርማሪዎቹ ዘገባ ከሆነ አንደኛው ተጠርጣሪ ብቻውን 120 ሺህ ዶላር ወደ ሆድ እቃው ሰዷል። ሌላኛው ደግሞ 111ሺህ ዶላር ያካተቱ 74 ጥቅል ዶላሮችን እንደዋጠ እና ሶስተኛውም 45ሺህ ዶላር ለዚህ ስራ ተብሎ በመጣ በአንድ ፕሮፊሽናል የጌጣጌጥ ወረቀት ጠቅላይ ሰው አማካኝነት ውጠው ለብራዚል ጉዟቸው ሲሰናዱ እጅ ከፈንጅ ተይዘዋል።አንዳንድ የናይጄሪያዊያን ዘራፊዎች ከዚህ ቀደም የሚታወቁት ኢትዮጵያ አየር መንገድን ጭምሮ የተለያዩ ደንበሮችን እና የአየር ክልሎችን በመጠቀም አደንዛዥ አጾችን በሆድ እቃዎቻቸው እና በብልቶቻቸው ሳይቀር ሸሽገው ለማሸጋገር ሰሞክሩ በቁጥጥር ሰር ዋሉ መባላቸውን ነበር።
የናይጄሪያው አዲሱ ፕ/ት መሃመዱ ቡሃሪ በቅርቡ “ሙስናን ካልገደልነው ሙሰና እኛኑ ይገድለናል ።ማለታቸውን ተከተሎ በርካታ ወገኖች “ሙሰኞች እና ዘራፊዎች እንደ ቻይና፣ እንደ ህንድ እና እንደ ደ/አፍሪካ በሞት ይቀጡልን” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ከ 12 -15 ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት የ ናይጄሪያ መናገሻ ከተማ የሆነቸ ሊጎስ ብቻዋን አመታዊ ገቢዋ ወደ 50 ቢሊዮን ዶላር ሲገመት ይህም ሃብቷ ሌጎስ ከተማ አንድ የአፍሪካ አገር ብትሆን ሰባተኛዋ በኢኮነሚ የበለጸገች አፍሪካዊ አገር ትሆን ነበር። የሚያሳዝነው ግን የሌጎስ ከተማ ባለሰልጣናቶቹዋ ለቁጥር የሚከብድ ገንዘብ በሰበብ በአስባቡ የሚዘርፉባት መነሃሪያ መሆኗ ነው።ሰኞ እለት ኔዮርክ(አሜሪካ)ላይ በተካሄደው 70ኛው የተመድ ጉባኤ ላይ የተገኙት ፕ/ት ቡሃሪ “ከ አፍሪካ አሕጉራችን ተዘርፎ በምእራባዊያን ባንኮች ተደላድሎ የተከማቸው ግዙፍ ገንዘባችን ይመለሰልን ዘንድ ተባበሩን” ሲሉ የሙሰኞች እና የዘርፉት ገንዘብ መሸሸጊያ የሆኑት ከበርቴ እገሮችን በጽኑ ተማጽነዋል።
የዚህ ሙሰና ነገር ከተነሳ ኢትዮጵያም ቢሆን ፈርጣማ የሆኑ ሙሰኞች እና በጠራራ ጸሃይ የሕዝብ ሃብት ዘራፊዎች እያቆጠቆጡባት እንደመጡ የተለያዩ ዘገባዎች የናገራሉ “ጥርስ አልባው አንበሳ” የሚሉት የጸረ ሙስና መ/ቤት ሳይቀር በመግለጫዋቹ አልፎ አልፎ ይነግረናል።ታዲያ እኛስ ብንሆን ሙስናን ቀይ ምንጣፍ አንጥፈን እንቀበለው?፣ወይስ እንደ ሰሞኑ የናይጄሪያው የጸረ አደንዛዥእጽ እና ሕገወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪ ግብረሃይል ዘርፊዎችን የዋጡትን የሕዝብ ገንዘብ አንዲተፉት አናድርጋቸው? አሊያም የኮሚኒስት ቻይና ተሞክሮን አ/አ(ኢትዮጵያ) ላይ ተግባራዊ እናደርገው? ለነገሩ ሙስናን የሚዋጋ ሃሞት ያለው አገዛዝ ጠፋ እንጂ ሁለመናችን ቻይናዊ ከሆነ ውሎ አድሮ የለ?!።
No comments:
Post a Comment