Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, September 2, 2016

ጋይንት ጨጨሆ ላይ በዚህ ሰአት 10ኦራል በህዝብ ተከቦ ቁሟል። ከትግራይ የተነሱ ወታደሮች በውጫሌ ዞረው ወደ ሰሜን ጎንደርና ጎጃም እያመሩ ነው



አንበሳው ጋይንት ጨጨሆ ላይ በዚህ ሰአት 10ኦራል በህዝብ ተከቦ ቁሟል ወደ ጋይንት ለማለፍ ፈልጎ ግን አልቻለም በጣም አሰጨናቂ ሁኔታ ነው ያለው የጨጨሆ ህዝብ እና የጋይንት ህዝብ አጋዜን አፋጠውታል ከባድ የተኩሰ ልውውጥ አለ አጋዜ ወደ ኋላ እንደሚያፈገፍግ ይጠበቃል ፡የመቄት እና ፍላቂት ህዝብም በዚህ ሰአት ወደ ጨጨሆ በመትመም ላይ ይገኛል ከተመለሰም ተቀብለው አምድ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል፡፡



ከትግራይ የተነሱ ወታደሮች በውጫሌ ዞረው ወደ ሰሜን ጎንደርና ጎጃም እያመሩ ነው። ከደቂቃዎች በፊት ውጫሌ ን አልፈዋል። ህዝቡ እንዲያስቆማቸው ከስፍራው ጥሪ ተደርጓል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ የጎጃም ወጣቶች - ለወሎ ወጣቶች የሚከተለውን አስቸኳይ መልዕክት አስተላልፈዋል፦

”አጋዚ እኛን ሊገድል ወሎን አሳብሮ ጎጃም እየገባ ነው ፤ ስለሆነም ከወሎ ወደ ጎጃም የሚያስገቡ ዋና ዋ ና መንገዶችን አለፍ አለፍ እያላችሁ በትላልቅ ግንዶችና ድንጋዮች ደህና አድርጋችሁ ዝጉልን።”
በዛሬው እለት የተለያዩ የአማራ ከተሞች ተጋድሎውን በተለያዬ ዘዴዎች ተያይዘውት ውለዋል ። ደባርቅ ፣ዳባት ፣ ጎንደር ከተማ፣ አዲስ ዘመን ፣እብናት ፣ወረታ ፣ ንፋስ መውጫ ፣ጋይንት፣ደብረታቦር ፣ሃሙሲት ፣ ዱርቤት ፣ ቲሊሊ ፣እንጅባራ ፣ሰከላ… ተጋድሎው አይሎባቸው የዋሉ የአማራ ከተሞች ናቸው። ከቤት ውስጥ ከመቀመጥ አድማ ጀምሮ አደባባይ ወጥቶ የህወሃትን አገዛዝ በከፍተኛ ሁኔታ እስከመቃወም ድረስ ተጋድሎው ቀጥሎ ውሏል ።
አባይ ባንክ ከካፍቴሪያ ከፍ ብሎ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካባቢ በህዝብ ላይ ሲተኩሱ በነበሩ የአጋዜ መከላከያወችን የጋይንት ፖሊሶች በድርጊታቸው በመበሳጨት መሳሪያቸውን ወደ መከላከያ በማዞር 7ቱን አጋዜወች ገለዋቸዋል ከህዝብ 11ሰው ሞቷል ከተገደሉት ውሰጥ የባንክቤት ዘበኞች እና አብዛኞቹም የመንግሰት ባለሟሎች መሆኑ ተገልጿል።
የጋይንት ፖሊሰ ሃይል በዚህ ድርጊታቸው ሊወደሱ ሊመሰገኑ ይገባል

No comments:

Post a Comment

wanted officials