በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ ዛሬ ሊነጋጋ ሲል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ታህሳስ 16፣ 2009 ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ።
አደጋው የደረሰው ሾፌሩን ጨምሮ 14 ሰዎችን አሳፍሮ ከባቱ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሽ ተሽከርካሪ ቦራ ወረዳ ሶሪ ዶሌሳ ቀበሌ ሲደርስ ከቢሾፍቱ ከተማ ወደ ባቱ ከተማ ከሚጓዝ ሲኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው።
የዞኑ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ምክትል ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ እንደገለፁት፥ በአደጋው በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ሾፌሩን ጨምሮ በሙሉ ህይወታቸው አልፏል።
የሟቾች አስከሬን ወደ አዳማ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን፥ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው ከፍጥነት በላይ እየተጓዘ እያለ ሲኖ ትራኩ መንገዱን ስቶ እንደገባበት ምክትል ኮማንደር አስቻለው ጠቁሟል።
ሆኖም ለተጨማሪ ምርመራ የሲኖ ትራኩ አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ እየተጣራ ነው ብለዋል።
በኦሮሚያ ክልል የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ሌሊት እንዳይጓዙ የተከለከለ ቢሆንም ትርፍ
ሰው ለመጫን ሲሉ ተደብቀው በሚያደርጉት የሌሊት ጉዞ መንገደኛውን ለአደጋ እያጋለጡት በመሆኑ የትራፊክ ፖሊሶች የሌሊት ቁጥጥራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ምክትል ኮማንደሩ ጠቁመዋል።
ሰው ለመጫን ሲሉ ተደብቀው በሚያደርጉት የሌሊት ጉዞ መንገደኛውን ለአደጋ እያጋለጡት በመሆኑ የትራፊክ ፖሊሶች የሌሊት ቁጥጥራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ምክትል ኮማንደሩ ጠቁመዋል።
ህብረተሰቡም የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ከፖሊስ ጋር በመተባበር የቁጥጥሩን ስራ እንዲያግዝ ምክትል ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ አመልክተዋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ
No comments:
Post a Comment